South Western Ethiopia Peoples Referendum Project office

South Western Ethiopia Peoples Referendum Project office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Western Ethiopia Peoples Referendum Project office, Legal, በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ግቢ በክልሉ ምክር ቤት ህንፃ በስተቀኝ 1ኛ ፎቅ ቢሮ 107 ቁጥር, Awassa.

It is under Government Organization for the aim of Designing and formulating Constitution, and other legal Frameworks,Preparation of ten year dev't roadmapComm mobilization and Advocacy of Referendum

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መቀመጫ ዋና ከተማ ማነው?፨፨፨፨፨፨፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨፨፨፨፨፨ደምኢህክ።።።።።።አዲሱ ክልል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በአዲስ የተስፋ ብርሐን ፈና ወጊ...
12/10/2021

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መቀመጫ ዋና ከተማ ማነው?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨፨፨፨፨፨ደምኢህክ።።።።።።
አዲሱ ክልል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በአዲስ የተስፋ ብርሐን ፈና ወጊ ክልል እንደሚሆን ይጠበቃል። በዚሁ ማዕቀፍ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ተፈቃቅደውና ተቻችለው የጋራ ቤታቸውን ይገነባሉ። ለመገንባትም ሚሊየኖች በህዝበ ውሳኔው ድምፅ አረጋግጠዋል። ስለሆነም የጋራ ቤታቸውን ተቀምጠው የሚገነቡበት ዋና ከተማ ያስፈልጋቸዋል። ይህንኑ ተከትሎ የመዋቅራችን ከተሞች በየማህበራዊ ሚዲያ እያስተዋወቁ ይገኛል። ከተሞች ያላቸውን አቅም ሀብት መነሻ በማድረግ እያስተዋወቁ መገኘቱ ክፋት የለውም ወደፊትም ፅዱ፣ ውብ ፣ለኑሮና ለኢንቨስትመን ምቹ መሆናቸውን እያስተዋወቁ የከተሞችን ብልፅግና ማሳካት እንደሚኖርባቸው ይታመናል። ይሁን እንጂ ክፋቱ ማስተዋወቁ ሳይሆን የምናስተዋውቅበት መንገድ ጤነኛ መሆን አለበት። ዋና ከተማ ለመሆን ሲባል አንዱን በማንኳሰስ እና በማጥላላት የሌላው ደግሞ በማጋነን መሆን የለበትም። ዋና ከተማም መቀመጫ የሚመረጠው የአንድ ብሔረሰብን ህዝብ ቁጥርን ወይም አንድ መዋቅርን ወይም አንድ ከተማ ህዝብን ብቻ ለማገልገል አይደለም። ሰላም ደህንነት ወዳለበት በመሄድና ባለመሄድም አይደለም ይልቁኑ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍን እንጂ ። ዋና ከተማ የሚሆነው ወይም የማይሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ስለተዋወቀና ወይም ስላልተዋወቀ አይደለም። የከተማ መረጣው በመርህ እና በእውነተኛ ምክንያት እና መረጃ ተመስርቶ ብቻ እና ብቻ ነው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክልል የምንመሰርትበት ዋናው ምክንያት ከዚህ ቀደም በዚህ ገፅ እና 'የህዝብ አብሮነትና አንድነት ለጋራ ክልል ምስረታ' በሚለው የህዝብ ግንኘነት ሰነድ ላይ ለማመላከት ሞክረናል።ውይይትም አድርገናል። በዚሁ መሠረት ሁለት ቁልፍ ነገሮች "የፓለቲካና የኢኮኖሚ ስብራታችንን" መጠገን የሚያስችለንን እንደሆነ ከዚህ ቀደም በሚገባ መግባባት ላይ ደርሰናል። ከዚህ አንፃር ፍታሐዊ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ብሎም የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በህይወት የመኖር እና የመጠበቅ መብታችንን በቅርበት የሚያስጠብቅ መንግስት በማቋቋም ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ እድገትና ብልፅግና የበኩላችንን ሚና መወጣት እንደሆነ ተግባብተናል ። ይሁን እንጂ በየማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች ይህንን በሚቃረን መልኩ እኔ እኔ ነኝ በሚል ስሜት በመዋቅሮች መካከል ውጥረትን ለመፍጠር ከመንቀሳቀስ መጠበቅና በጥንቃቄ መመራትም ወይም መያዝ ይኖርበታል ። በዚህ መሐል የለውጡ ውጤት የሆነው አዲሱ ክልል ስኬታማ እንዳይሆን ለፀረ -ህዝብ ሐይሎች ምቹ እንዲሆን ውጥረት መፍጠር የለብንም ።
፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨ደምኢህክ፨፨

ህዝባችንም ሆነ ሌሎች ወንድሞቻችን የዚህ ክልል ስኬትን በጉጉት የሚጠብቁ አካላት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ከተማ ማን ይሆን? በሚል ጥያቄው እየተንሸራሸረ ይገኛል። ዋና ከተማችን አንድ ከተማን በሚያፈረጥም ሌላውን በሚያዳክም መልኩ የሚመረጥ ከተማ ሳይሆን በመርህ እና በመስፈርት በስሜትና በዘፈቀደ ሳይሆን በእውነተኛ ምክንያታዊነት የሚፈፀም ነው። በህገ መንግስታችን ደረጃም ብዝሐ ዋና ከተሞች(Multicapital cities )ወይም ከአንድ ዋና ከተማ በላይ እንደሚኖረን እንጂ 'አንድ ዋና ከተማ ብቻ' የሚኖረን ባለመሆኑ በየመዋቅሮቻችን ያለው ህዝብ ሂደቱን በመረጋጋት መጠበቅ አለበት። ከአሉባልታና ለራስ ከሚገባ በላይ ባለ አመለካከት (ከOver expectation ego) ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል።
፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨ደምኢህክ፨፨፨ደምኢህክ፨፨

የአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና ከተሞች የሚመረጡት
1ኛ. የአለም አቀፍ ተሞክሮ ጥናት ተደርጎ የሚፈፀም ነው። ይህም በሂደት ላይ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል ።
2ኛ. ከኛ ተጨባጭ ሁኔታ መስፈርቶችን አንጥሮ በማውጣት በውይይት በማዳበርና መግባባት ላይ የሚደረስ መሆኑ
3ኛ. በመስፈርቱ መሠረት ለመስፈርቶቹ ግልፅ ሳይንሳዊ መመዘኛ ክብደት በመስጠት የሚከናወን በመሆኑ
4ኛ. ሁሉንም የዞን እና የልዮ ወረዳ መቀመጫ ዋና ከተሞች ወይም በመዋቅሮቻቸው የተለዮት የተሻሉ ከተሞች የውድድሩ አካል እንዲሆኑ በማደረግ እንዲመዘኑ ተደርጎ የሚፈፀም መሆኑ
5ኛ. ከተመረጡ ዋና ከተሞች ውጭ ያሉ ከተሞች እንዴት አብሮ ተሳስሮ እንዲሚያድጉ ብሎም ፍታሐዊ እና የተመጣጠነት እድገት እንዲያስመዘግቡ በሚያስችል መልኩ እንዴት ማደግ እንዳለባቸው የሚመሩበት የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት የሚፈፀም ይሆናል። ይህ ሁሉ ሲወሰን ሁላችንንም በፍትሐዊነት በሚጠቅም መልኩ በመፈቃቀድና በወንድማማችነት ወደ አንድ ክልል እንድንመጣ ካስገደዱን ገፊ ምክንያቶች ወይም ያጣነውን በሚያሰገኝ የጎደለብንን በሚሞላ መልኩ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ፣ፓለቲካዊና ስትራቴጂያዊ በሆነ መልኩ የሚመለስ ይሆናል።
ሰለሆነም ከአንድ ዋና ከተማ ይልቅ ባለብዙ ዋና ከተሞች ባለቤት የሆነ ክልል የሚመረጥ መሆኑን ህዝባችን ተንዝቦ ካላስፈላጊ ውጥረት እና አሉባልታ ራሱን በመከላከል በትዕግስት መጠባበቅ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ህዝበ ውሳኔው የጥቂቶች ሳይሆን የሚሊየኖች ነው!!፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሆነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ (ደምኢህ) ውስጥ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ህ...
25/09/2021

ህዝበ ውሳኔው የጥቂቶች ሳይሆን የሚሊየኖች ነው!!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሆነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ (ደምኢህ) ውስጥ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ድምፁን ለመስጠት ተዘጋጅቷል። ስለሆነም የህዝበ ውሳኔው የጥቂቶች ሳይሆን የሚሊየኖች ነው። ፈተናዎችን አልፋል መሳካቱም አይቀርም ።6ቱም መዋቅሮች በአንድነት ለመመስረት የወሰኑት በወንድማማችነት በእውነትና በእውቀት በመፈቃቀድና በመቻቻል መርህ ላይ ተመስርተው እንጂ ማንም አስገድዷቸው አይደለም። ወደ ኃላ የሚመለስ ነገር የለም። ላንጨርሰው አልጀመርንም። የጀመርነውን እንጨርሳለን የብልፅግና ራዕይም እውን ይሆናል። ለኢትዮጵያም ፋና ወጊ ክልል ሆኖ ይመሰርታል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የደምኢህ መመስረቱ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ስብራታችን ወይም ህመማችን ይጠገናልም ይፈወሳልም። የምንመሰርተው ክልል ዋናው ግባችን ሳይሆን ዋናውን ግባችን የምናሳካበት መሳሪያችን ነው ። በሂደቱም በውጤቱም የምንጠቀምበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓትም መሳራችንም ነው። ስለዚህ የምንመሠርተው ክልል በስሜት ሳይሆን በስሌት ነው። በእውነተኛ መንገድ በትክክለኛ ግዜ እና መዋቅሮች ነው።
በመሆኑም በ6ቱም መዋቅራችን ህዝበ ውሳኔያችን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአከባቢውን ደህንነት እና ሰላም በንቃት መከታተል። ከሚመለከታቸው የፀጥታ እና የአካባቢው መንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት በንቃት መጠበቅ አለበት።

'የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምስረታ በህዝቦች መፈቃቀድ በትክክለኛ ምክንያት እና እውነት ላይ የተመሠረተ ነው።'

25/09/2021
የህዝበ ውሳኔው ንቅናቄው ተቀጣጥሏል!፧፧፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨አምስት ቀን ብቻ የቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ የተለያዩ ፈተናዎችን አልፎ እውን ሊ...
24/09/2021

የህዝበ ውሳኔው ንቅናቄው ተቀጣጥሏል!
፧፧፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አምስት ቀን ብቻ የቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ የተለያዩ ፈተናዎችን አልፎ እውን ሊሆን ተቃርቧል። ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ከሆነው ህዝባችን ውስጥ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ህዝበችን የደቡብ ምዕራብና ኢትዮጵያን ለሁሉ መኖሪያ በመቻቻልና በመፈቃቀድ በወንድማማችነት ላይ የተመሠረች ለብልፅግና ተምሳሌት የምትሆን ክልል ለለመመስረት በሰሞኑም በምዕራብ ኦሞ በዳውሮ በካፋ በኮንታ በሸካ እና በቤንች ሸኮ ዞን በህዝባዊ ማዕበል የድጋፍ ሰልፍ በቡና ጠጡ ፕሮግራም ሲቀጣጠል ከርሟል።

ድምፃችንን እውን ለማድረግ 18 ቀን ቀረን!!ቆጣሪው እየፈጠነ ነው።
11/09/2021

ድምፃችንን እውን ለማድረግ 18 ቀን ቀረን!!ቆጣሪው እየፈጠነ ነው።

11/09/2021

የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ በምርጫ ቦርድ በሚዲያ ሽፋን ስለሚሰጥበት ሁኔታ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጷጉሜ 4 2013ዓ.ም ሀዋሳ

ወ/ሮ ሶሊያና ሽመልስ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሐላፊ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ አስፈፃሚ አቢይ ኮምቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ማስረሻ በላቸው ( በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማረግ ) ጋር በነበራቸው ውይይት ከእንቁጣጣሽ በኃላ ሀገራው፣ክልላዊና አካባቢያዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በምርጫ ቦርድ በኩል ስለ ሪፈረንደሙ ምንነት፣ምልክትና ድምፅ አሰጣጥ ሰፋ ያለ የሚዲያ ቅስቀሳና ገልፃ እንደሚያደርጉ መግባባት ላይ ተደርሷል። ህብረተሰቡንም በቀላሉ ለማግኘት በአቅራቢያው መጠቀም የሚንችላቸውን የ ሬዲዮና tv ጣቢያዎች የመለየት ስራ ሰርተዋል ፤ ደቡብ Tv&radio፣በFm፣ ፋና፣እንዲሁም ኢትዮጵያ radio&tv በኩል የሚተላፍ ይሆናል። በተጨማሪም የሪፈረንደም ፖስተርና በአድስ መልክ የተዘጋጀውን ድምፅ መስጫ ወረቀት ናሙና በቅርቡ እንደሚወርድም ተረጋግጧል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኘሮጀክት ፅ/ቤት

ቦርዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር አካሄደOn Sep 9, 2021  51አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ...
09/09/2021

ቦርዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር አካሄደ
On Sep 9, 2021 51
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሀዋሳ ምክክር አደረገ።
ቦርዱ መስከረም 20/2014 ዓ.ም. በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የጊዜ ሰሌዳ እና ምርጫውን በሰላም ማካሄድ በሚቻልበት ላይ ነዉ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ዉይይት ያካሄደዉ።
በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ዉሳኔ ሲካሄድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የታዩ እንዳንድ ችግሮች እንዳይደገሙ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት አንስተዋል።
ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃላፊነት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል ብለዋል የፓርቲዎቹ አመራሮች።
ገዢው ፓርቲም ለህዝበ ውሳኔው በሰላም መጠናቀቅ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩሉን መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳዉ እንዳሉት ምርጫውን ለማካሄድ የየአካባቢዎቹ ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ምርጫዉ የበለጠ ሰላማዊ ለማደርግ የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርትኳን ሚደቅሳ በበኩላቸው ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲካሄድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተሟሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ምርጫውን ፍትሐዊ፣ ግልፅና ሰላማዊ ለማድረግ ባለፈው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተገኙትን ልምዶች በመጠቀም ህዝቡ ድምፁን በነፃነት እንዲሰጥ ይደረጋል ብለዋል።
በቢቂላ ቱፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልልን ለመምረጥ ተዘጋጅተናልእርስዎስ?
07/09/2021

የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልልን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
እርስዎስ?

በምእራብ ኦሞ ዞን ድጋሚ የህዝበ ውሳኔ ምዝገባ የሚካሄድ በመሆኑ በዚህ ታሪካዊ ግዜ ለታሪካዊ ውሳኔ ይመዝገቡ!!
06/09/2021

በምእራብ ኦሞ ዞን ድጋሚ የህዝበ ውሳኔ ምዝገባ የሚካሄድ በመሆኑ በዚህ ታሪካዊ ግዜ ለታሪካዊ ውሳኔ ይመዝገቡ!!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጀግኒት የራስዋን    እድል በራስዋ ለመወሰን ቆርጣ ተነስታለች ማንስ ያስቆማታል??!!
01/09/2021

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጀግኒት የራስዋን እድል በራስዋ ለመወሰን ቆርጣ ተነስታለች ማንስ ያስቆማታል??!!

ለታሪካዊ ቀኖ ተመዝግበዋልን???!!!
01/09/2021

ለታሪካዊ ቀኖ ተመዝግበዋልን???!!!

Address

በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ግቢ በክልሉ ምክር ቤት ህንፃ በስተቀኝ 1ኛ ፎቅ ቢሮ 107 ቁጥር
Awassa

Telephone

+251964185389

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Western Ethiopia Peoples Referendum Project office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category