22/08/2026
የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ምስረታ በስኬት ተጠናቀቀ
የሲዳማ ክልል የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በይርጋለም ከተማ ደራሮ አዳራሽ ሲያካሂድ የቆየው የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምስረታ መርሐግብር የአመራር ምርጫ በማካሄድ በስኬት ተጠናቋል።
በዚህም ወደ ኃላፊነት የመጡ ወጣቶች፤ ወጣት ናስር አብደላ ዋና ሰብሳቢ፣ ወጣት አብዱሰላም አህመድ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም ወጣት ዑመር ኡስማን ዋና ጸሐፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ ከእነዚህ ዋና ዋና ኃላፊዎች በተጨማሪ 11 አባላት ያሉት የዞኑ የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በይፋ ተመስርቷል።
በዕለቱ የተቋቋመው ይህ ካውንስል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የሚገኙ የሙስሊም ወጣቶችን አንድነት ለማጠናከር፣ በበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በንቃት ለማሳተፍ እና ለአካባቢው ሰላምና ልማት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ትልቅ መድረክ እንደሚሆን ተገልጿል። ጉባኤው አዳዲስ የተመረጡ አመራሮችንና የአስፈጻሚ አባላትን በማስተዋወቅ እንዲሁም ለቀጣይ የሥራ ዘመናቸው መልካም ምኞት በመግለጽ በደመቀ ሁኔታ ፍጻሜ አግኝቷል።
Voice of Sidaama