Aysaqiitii Magaalah xiinissok Qadli Ku /Buxa

Aysaqiitii Magaalah xiinissok Qadli Ku /Buxa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aysaqiitii Magaalah xiinissok Qadli Ku /Buxa, Legal, Asaita.

የፍትሕ ሚኒስቴር                 MINISTRY OF JUSTICE                        የፕሬስ መግለጫአዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታ...
07/06/2026

የፍትሕ ሚኒስቴር
MINISTRY OF JUSTICE

የፕሬስ መግለጫ

አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ ህዝብ እና ባለድርሻ አካላት በትዕግስት እንዲጠባበቁ የተሰጠ መግለጫ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት አገልግሎት ላይ ውሎ የቆየውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማፅደቁ ይታወቃል። በዚህ መሰረት የፀደቀው የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እና ወጥቶ ሙሉ በሙሉ ወደ ተፈፃሚነት እንዲገባ ለማስቻል የመጨረሻው የቃላት ማስተካከያ እና ሌሎች የሕግ እርማት ሥራዎች (Editorial Works) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል በጥንቃቄ እና ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል። ይህም አንዳንዶች መታዘብ እንደሚችሉት ሕጉ ለህዝብ በይፋ ባልተሰራጨበት ሁኔታ በተለያዩ ጊዜያት ሲዘጋጁ የነበሩ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ ረቂቆች ለተለያዩ ተቋማዊ አገልግሎቶች እና ስልጠናዎች በተለያዩ አካላት ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውሉ የጽሁፍ መረጃዎች መሆናቸው ተስተውሏል።

የመጨረሻው የአርትኦት ሥራ ሳይጠናቀቅ ማንኛውም ይፋዊ ያልሆነ ሰነድ ለሥራ ማስፈጸሚያነትም ሆነ ለሌሎች ተያያዥ ተግባራት መዋል በአፈጻጸም ላይ የቃላትና የአንቀጽ አለመጣጣም እንዲሁም ሌሎች በርካታ ችግሮች እንዲከሰቱ በመፍጠር በፍታሕ ሥርዓቱ ላይ መደናገር መፍጠር ስለሚችል ይፋዊ ያልሆነ ሰነድ እስኪወጣ ድረስ ከእንዲህ መሰሉ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የፍትሕ ሚኒስቴር በጥብቅ ያሳስባል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጨረሻው የአርትኦት ሥራ ሲጠናቀቅ ሕጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ለህዝብ ተደራሽ የሚሆን መሆኑን ከገለጸ በተጨማሪ በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይም ይፋዊው ሰነድ በይፋ ከወጣ በኋላ የሚሰራጭ መሆኑን እያረጋገጠ በፍታሕ ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ የሕግ ባለሙያዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ እና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ ያቀርባል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር
ግንቦት 30/2018 ዓ.ም

Unkaq meqe Qiid geyteenim inkih tan Qafar ummattak!!!Qadli Biirok saqalah yan Massakaxxale Qasker Macammad Qarfa Qiidih ...
26/05/2026

Unkaq meqe Qiid geyteenim inkih tan Qafar ummattak!!!
Qadli Biirok saqalah yan Massakaxxale Qasker Macammad Qarfa Qiidih Qaffayda wagsiisak unkaqqinó farmo tatruse!
ta farmol Qiid Amôgibdaay Qaafiyat leeh, gariiy garuh nek xuwaawak Akah nassakaxxe innah axcuk unkaqiino farmo inkih tan Muslimiiniiy, baxsaluk Qafar ummattah tatruse!!!
mubaarak

16/05/2026
Ayrok  06 /9 / 2018 I.L.L qafar agatih rakaakayih doolatak qadli biiro edde tan caddook taama maysaasa takku inkih Yan r...
15/05/2026

Ayrok 06 /9 / 2018 I.L.L qafar agatih rakaakayih doolatak qadli biiro edde tan caddook taama maysaasa takku inkih Yan rasittee Kee daqoritik abnisso duddih kusaaqih taama takkuh rubteh tan butta Awsi rasuk aysaqiitii Magalah Xiinisok Qadli ku/buxa taama bagul taamak abnissol Kulsaa kee qaku nee yaysaballoonu xiqen. temeeteh tan buttak assacossaa akaqquke meqennal numurruqeeh. Temeeteh tan buttah Gadda gacisna!!!!!

26/04/2026

በወንጀል አፈፃፀም ላይ ተካፋይ መሆን የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት
መግቢያ
ወንጀል ማለት አንድን አታድርግ የተባለ ድርጊት ወይም ተግባር ማድረግ (መፈፅም) (commission) ወይም አድርግ የተባለ ድርጊት አለማድረግ (አለመፈፀም) (omission) ነው፡፡ አንድ ወንጀል በአንድ ሰው የወንጀል ሀሳብ ጠንሳሽነት ተጀምሮ በዚሁ ሰው ፍጻሜ ሊያገኝ እንደሚችል ሁሉ በአንድ የወንጀል ተግባር ላይ ወንጀሉን በአካል ከሚፈጽመው ሰው በተጨማሪ ሌሎች ሰዎች ከአጀማመሩ እስከ ፍጻሜው ባለው ሂደት ወይም ከዚያ በኃላ በተለያየ ደረጃዎች ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጽሁፍም የወንጀል ተካፋይነትን በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ መሆን (አንቀጽ 32)
በወንጀል ህግ አንቀጽ 32 መሰረት አንድ ሰው በሶስት ሁኔታዎች በዋና ወንጀል አድርጊነት ተካፋይ እንደሆነ ተቆጥሮ እንደሚቀጣ የደነገገ ሲሆን ይኸውም
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 32(1)(ሀ) መሰረት በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር በተለይም በእንስሳ ወይም በተፈጥሮ ኃይል አማካይነት ወንጀሉን አድርጐ እንደሆነ በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንደፈፀመ ተደንግጓል፡፡ በእጀ አዙር ሲባል ለምሳሌ በሰው አካል እና ጤና ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በእብድ ውሻ ሰውን ማስነከስ ወይም የተፈጥሮ ሀይልን እንደ ውሃ፣ እሳት በመጠቀም በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ እንደ ዋና ወንጀል አድራጊ ተቆጥሮ የሚቀጣ ይሆናል፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀፅ 32(1)(ለ) መሰረት ወንጀሉን እሱ ራሱ በቀጥታ ባያደርግም እንኳን በመላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊቱና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደርገ ሲሆን ነው፡፡ ይህም ከድርጊቱና ውጤቱ ጋር የተሟላ የሀሳብ ውህደት ያለው ማለትም በቀጥታ በአካል ወንጀሉን የሚፈፅመውን ሰው ሙሉ በሙሉ የመደገፍና የድርጊቱን ውጤት እንደ እራስ ድርጊትና ውጤት አድርጎ መቁጠር ነው፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀፅ 32(1)(ሐ) መሰረት ሕፃንን ወይም አእምሮው ያልተስተካከለውን ወይም የአእምሮው ህመምተኞችን ማለትም ሁኔታውን የማያገናዝበውን ሰው ወንጀል ለማድረግ መሣሪያ ያደረገ ወይም ሌላውን ሰው ወንጀል እንዲያደርግ ያስገደደ ሲሆን እንደ ዋና ወንጀል አድራጊ ተቆጥሮ የሚቀጣ ይሆናል፡፡

በልዩ ወንጀል ተካፋይ መሆን (በወንጀል ህግ አንቀጽ 33)
አንዳንድ ወንጀሎች በባህሪያቸው በሁሉም ሰዎች ሊፈፀሙ የማይችሉ ዓይነት ተደርገው ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌም ወታራዊ ወንጀልን ለመፈፀም ወታደር መሆንን፣ በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀልን ለመፈፀም የመንግስት ሰራተኛ መሆንን እና ሴትን አስገድዶ ለመድፈር ወንድ መሆን በዋናነት ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ሰው ወንጀሉን ለመፈፀም የተለየ ጠባይ ያላቸውን ወንጀሎች ለመፈፀም የሚያስችለው ሁኔታ ባይኖረውም በመላ አሳቡ፣ በሙሉ ፈቃዱና በአድራጎቱ እነዚህን ወንጀሎች ለመፈፀም የተለየ ሁኔታ ካላቸው ሰዎች ጋር ከተባበረ በዋና ወንጀል አድራጊነት ሊጠየቅ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው የመንግስት ሰራተኛ ሣይሆን በሙሉ ሀሳብ እና ድርጊት ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የመንግስት ሥራ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ቢያደርግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ሊጠየቅ ይችላል፡፡

በህብረት ስለሚፈፀም ወንጀል (አንቀጽ 35)
ቁጥራቸው ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ወንጀል ተፈጽሟል ተብሎ ሲገመት እያንዳንዱ ሰው በመርህ ደረጃ በወንጀሉ ውስጥ የነበረው ወይም ያደረገው ተሳትፎ በማስረጃ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን እንደ አድማ እና አምባጓሮ በመሳሰሉት ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ በህብረቱ ውስጥ መገኘቱ የተረጋገጠበት ሰው ከቅጣ ነፃ የሚሆነው እራሱ በወንጀሉ ተካፋይ አለመሆኑን ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነው፡፡

ማነሳሳት
የወንጀል ህጉ በአንቀፅ 36(1) መሰረት ማንም ሰው ወንጀል እንዲደረግ አነሳሳ የሚባለው አስቦ ሌላውን ሰው በመጐትጐት፣ ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፣ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላ ዘዴ አንድ ወንጀል እንዲያደርግ ያግባባ እንደሆነ ነው፡፡ የማናሳሳት ድርጊት አንድ ሰው ወንጀል ፈፃሚውን ወንጀል እንዲፈፅም ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ እንዲደረስ ሲያደርገው ሲሆን በወንጀል የሚጠየቀው የወንጀል ህጉ አንቀፅ 36(2) መሠረት ዋና ወንጀል አድራጊው (ተነሳሺው) ቢያንስ ወንጀሉን የመፈፀም ሙከራ አድርጎ እንደሆነ ነው፡፡ ቅጣቱም የሚወሰነው ሊደረግ ለታሰበው ወንጀል ህጉ በተደነገገው ቅጣት ልክ ሲሆን በዋና ወንጀል አድራጊው የተፈፀመው ወንጀል አነሳሹ ከፈለገው በላይ በሆነ ጊዜ አነሳሹ የሚቀጣው እርሱ በፈለገው ወይም ይሆናል ብሎ ሊገምተው በሚችለው ወንጀል ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ዋና ወንጀል አድራጊው ላደረገው ከባድ ወንጀል እራሱ ብቻ ሀላፊ እንደሚሆን ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 36(4) መረዳት ይቻላል፡፡

አባሪነት
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 37(1) መሰረት ማንም ሰው በወንጀል ድርጊት አባሪ ነው ተብሎ የሚቆጠረው ዋና ወንጀል አድራጊው ወንጀል ከማድረጉ በፊትም ሆነ ወይም በሚያደርግበት ጊዜ ወሬ በማቀበል፣ በመምከር፣ ወንጀል የሚያደርግበትን ዘዴ ወይም መሣሪያ ወይም ግዙፋዊ እርዳታ በመስጠት ወይም ለወንጀሉ አፈፃፀም በሚጠቅም በማናቸውም ሌላ ዓይነት መንገድ አስቦ የረዳው እንደሆነ ነው፡፡
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 37(2) እና (3) መሰረት ታስቦ ለሚደረግ ወንጀል አባሪ መሆን ሁል ጊዜም የሚያስቀጣ ሲሆን አባሪው የሚቀጣው ወንጀሉ ቢያንስ የተሞከረ ሲሆን እንደሆነ ከህጉ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡

ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ወንጀለኛን መርዳት
አንድ ሰው ወንጀል ከፈፀመ በኃላ በዚሁ ወንጀል እንዳይከሰስ ወይም እንዳይቀጣ እርዳታ የሚሰጥ ሰው ወንጀለኛን በመርዳት ተጠያቂ እንደሚሆን ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 40 መረዳት ይቻላል፡፡ ወንጀለኛን መርዳት ከአባሪ ወይም አነሳሽነት የሚለየው በመርህ ደረጃ አባሪነትና አነሳሽነት ዋናው ወንጀል አድራጊ በሚከሰስበት የወንጀል ድንጋጌ የሚያስከስስና በዛው ድንጋጌ ላይ በተቀመጠው ቅጣት ልክ የሚያስቀጣ መሆኑ ነው፡፡ ወንጀለኛን መርዳት አስቀድሞ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ያደረገው አስተዋጽኦ ባለመኖሩ እራሱ ለፈፀመው የወንጀል ድርጊት ብቻ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል በተደነገገ አግባብነት ባለው ድንጋጌ የሚቀጣ ይሆናል፡፡

የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የወንጀል ተካፋይነት
የወንጀል ህጉ አንቀፅ 34 የህግ ሰውነት የተሰጠውን ድርጅት የመንግስት አስተዳደር አካላትን ሳይጨምር በህግ ላይ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት በወንጀል ሊቀጣ የሚችልበትን ሁኔታ በግልጽ ደንግጓል፡፡ ይኸውም ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ ቅጣት የሚጣልበት ከሀላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የድርጅቱን ጥቅም በህገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ሲፈፅም ነው፡፡ በዚህ መልኩ ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ድርጅት የሚቀጣው በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 90 መሰረት በሚጣል በመቀጮ ሲሆን አስፈላጊ በሆነ ጊዜም ድርጅቱ እንዲታገድ፣ እንዲዘጋ ወይም እንዲፈርስ ተጨማሪ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል፡፡

ማጠቃለያ
የወንጀል ህጉ በተለያየ ሁኔታ በወንጀል ተሳትፎ መገኘት የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት የደነገገ በመሆኑ ህብረተሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ መሰል ድርጊቶች ከሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት እራሱን ሊጠብቅ ይገባል፡፡

በንቃተ ሕግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

የፍትሕ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን እና ድረ-ገጽን ይቀላቀሉ
Website
https://www.justice.gov.et
Facebook
https://www.facebook.com/MOJEthiopia/
(x) Twitter
https://x.com/MOJEthiopia
YouTube channel
https://youtube.com/...3701 ...
LinkedIn
https://www.linkedin.com/.../ministry-of-justice.../about/
Telegram
https://t.me/fdreattorneyGeneral_externa

Awsi Rasuk Aysaqiiti Magaalah Xiinissok Qadli Kobox Ayrok 11 /08 /2018 i.l.l. 3 heele Rubqi Sanat   Kobox-luk Maacisseh ...
19/04/2026

Awsi Rasuk Aysaqiiti Magaalah Xiinissok Qadli Kobox Ayrok 11 /08 /2018 i.l.l. 3 heele Rubqi Sanat Kobox-luk Maacisseh Tanim Kee Ta Kobox Akah Faxxiimem Qadli Xagorti 3 Alsih Addat Tekkeh Tan Taama Kee Baxaabaxsale Taamay Abnek Maca Tekk Sukteemil Kobox Elle Abnekkel Baxaabaxsa Le Ammuntittel Baarleh Yan Walalal Siita Nuybulleek Gamadal Ellacabol Sugeh Yan Qaki Elle Massoowam Faxxinta Afkanitte Daffeysak Taamal Siita Akrayuk Siita Qokolak Siitallih Taamitaanam Faxxintaamal Sittingey Abneek Gamadal Afkanitte Elle Acayuk Walal Gudgud Meqe Gurral Yumurruqe.

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ...
15/04/2026

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018
በፀደቀው !!

አንቀፅ 20 የዐቃቤ ሕግ ተቋም ተግባርና ኃላፊነት

፩. የወንጀል ምርመራን በበላይነት ይመራል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም በራሱ ምርመራ ያከናውናል፡፡
፪. የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር፣ በፖሊስ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ የክትትል ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል፣ የወንጀል ምርመራ በሕግ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን ያረጋግጣል፣ በምርመራ መዝገብ ላይ አስፈላጊውን ትእዛዝ ይሰጣል፡፡
፮. ውጤታማ ስራ ያላከናወነ መርማሪ ፖሊስ በሌላ መርማሪ ፖሊስ እንዲተካ ያደርጋል፡፡

የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ *********************** የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ...
02/04/2026

የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
***********************

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ አቅርበዋል።

ረቂቅ ሕጉ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች ለማክበርና ለማስከበር የሕግ የበላይነት በማስፈን የአሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

የተቀላጠፈ የፍትሕ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እና ልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴን እንዲሁም ለተጎጂዎች ካሳ የሚከፈልበትን አግባብ ያካተተ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ ረቂቅ ሕግ እንደሆነ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ አያይዘው አስረድተዋል።

ረቂቅ ሕጉ ከኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ መርሆች እና እሴቶች እንዲሁም ከወንጀል ሕጉ ጋር የተጣጣመና ዘመናዊ በመሆኑ ጠቃሚ እንደሆነ ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።

ረቂቅ ሕጉ በሕገ-መንግሥቱ፣ በወንጀል ሕጉ፣ ዓለም አቀፍ ሕጎች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች የተረጋገጡ ልዩ ትኩረት ለሚያሻቸው ለሴቶች፣ ሕፃናት እና አካል ጉዳተኞች የተሰጣቸውን መብቶች ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ገልጸዋል።

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ረጅም ጊዜ የቆየና የዘገየ ቢሆንም በሕዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ወቅቱን የሚመጥን አዋጅ በመሆኑ የሕዝብን የፍትሕ ሥርዓቱን ለማስፈን እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር እና የፍትሕ ሥርዓቱን በማዘመን ወቅታዊ የአዋጅ አገልግሎት ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላት አመላክተዋል።

በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት ረቂቅ አዋጁ በአተገባበር ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ከፍትሕ አካላት ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ከምርመራ ሂደት እና ከዲጂታል አሠራሮች ጋር በተያያዘ ዜጎችን ሕገ-መንግሥታዊ መብትን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላቱ አስገንዝበው፤ በማረሚያ ቤት ቆይተው ፍርድ ቤት ነፃ የሚላቸው ዜጎች የካሳ ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማስቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 አድርጎ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።

📍 የአይሰኢታ ከተማ መስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት            ━━━━━━━━━━━━━━━⚠️ የህግ ማስጠንቀቂያ🛑 ህገወጥ የቤንዚን ንግድ ከዋጋ ጭምር እና መደበቅ ጋር ❗ ህገወጥ የቤንዚን ንግ...
02/04/2026

📍 የአይሰኢታ ከተማ መስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት
━━━━━━━━━━━━━━━
⚠️ የህግ ማስጠንቀቂያ
🛑 ህገወጥ የቤንዚን ንግድ ከዋጋ ጭምር እና መደበቅ ጋር ❗
ህገወጥ የቤንዚን ንግድ ከዋጋ ጭምር እና መደበቅ ጋር ተያይዞ
❌ ዋጋ ጭምር (በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ)
❌ ነዳጅ መደበቅ (ለዋጋ ማስጨመር ማከማቸት)
❌ ያለፈቃድ ንግድ
👉 በህግ በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው!

🚨 የሚወሰዱ እርምጃዎች
⛔ ንግድ መዘጋት
💰 የገንዘብ ቅጣት
⛓️ እስር
🛢️ ነዳጅ መውረስ
📢 ማስጠንቀቂያ
👉 ማንኛውም ግለሰብ በእነዚህ ህገወጥ ተግባራት የተሳተፈ ከሆነ በህግ ይጠየቃል!

የአይሰኢታ ከተማ መስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት እና ፖሊስ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በከተማው ውስጥ የቤንዚን ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር የህገወጥ የዋጋ ጭማሪ በተመለከተ ውይይት አካሂ...
31/03/2026

የአይሰኢታ ከተማ መስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት እና ፖሊስ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በከተማው ውስጥ የቤንዚን ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር የህገወጥ የዋጋ ጭማሪ በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት የነዳጅ ምርት በሕጋዊ ዋጋ መሸጥ የነጋዴዎች ሕጋዊ ግዴታ መሆኑ በግልፅ ተገልጿል፤ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ግን በሕግ የሚያስጠይቅ እና የህብረተሰብን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑ ተጠንቅቆ ተብራርቷል። እንዲሁም ነጋዴዎች ሕግን እንዲከበሩ እና የሚፈጠሩ ህገወጥ ድርጊቶችን እንዲቆጠቡ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ከዚህ በኋላ በከተማው ውስጥ የነዳጅ ገበያ ንብረት እንዲቆጣጠር በተደጋጋሚ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል፤ ሕግ የሚጣሱ ነጋዴዎች ላይ ግን አስፈላጊ የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠንቅቆ ተገልጿል።

ይህ ውይይት በከተማው ውስጥ የዋጋ መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ የህብረተሰቡን ጥቅም ለመጠበቅ እና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
በአጠቃላይ፣ ከዚህ በኋላ የቤንዚን ሽያጭ በህጋዊ መርሀ ግብር መሰረት እንዲካሄድ እና ህግ የሚጣሱ ነጋዴዎች ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ግልፅ ውሳኔ ተወስኗል።

Address

Asaita

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aysaqiitii Magaalah xiinissok Qadli Ku /Buxa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category