Gamo Zone Geressie Zuria woreda People's Council Office

Gamo Zone Geressie Zuria woreda   People's Council Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo Zone Geressie Zuria woreda People's Council Office, Arba Minch'.

የጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወርዳ ሕዝብ ምክር ቤት በዞናችን ሦስት ወረደዎች በጋጮ ባባ፣ በቦንኬ ወረዳና በካምባ ዙሪያ ወረዳ በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ ከ 52 ሰዎች በላይ ሕይወት ማለፉን ...
12/03/2026

የጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወርዳ ሕዝብ ምክር ቤት በዞናችን ሦስት ወረደዎች በጋጮ ባባ፣ በቦንኬ ወረዳና በካምባ ዙሪያ ወረዳ በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ ከ 52 ሰዎች በላይ ሕይወት ማለፉን በመስማታችን የገረሴ ዙሪያ ወረዳ የተሰማንን መሪር ሐዘን እንገልፃለን።

የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አየለ ቦላ ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለአደጋው ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የዞኑ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።

​መጋቢት 3/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት ኮሙዩኒኬሽን /ጽ/ቤት)

ጋሞ ዞን ገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል የ6ኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ክልል ም/ቤት 5ኛ ዓመት  የሥራ ዘመን የውክልና ሥራ ተወካዮች ከመረጠው ህዝብ ጋር ውይይት እያደርጉ ይገኛሉ።ገረሴ:30/7/2...
09/03/2026

ጋሞ ዞን ገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል የ6ኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ክልል ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የውክልና ሥራ ተወካዮች ከመረጠው ህዝብ ጋር ውይይት እያደርጉ ይገኛሉ።

ገረሴ:30/7/2018 ዓ.ም (የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝቡ ም/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳይ አገልግሎት)

የቦንከ -ገረሴ ምርጫ ክልል ተወካይ ፕሮፌሰር ይስኃቅ ካጫሮ፣የቦንከ-ገረሴ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ አቅመ አርዞ
የቦንከ ገረሴ ምርጫ ክልል የገረሴ ምርጫ ክልል የሁለቱ መዋቅር ዋና አፌ ጉባኤዎች፣የሀገር ሻማግለዎች፣ባጠቃላይ ሲቪል ሰርቫንት እና አከባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በምክክር መድረኩም የሁለቱ መዋቅር ከባለፈው ምርጫ ጊዜ ደምሮ እስከዚህ የተሠሩ የልማትና ከመልካም አስተዳደር ሥራዎች አኳያ የጋራ ውይይት እንደሚያካሄዱ ተገልፀዋል።

በመቀጠልም በሚቀጥለው ምርጫ ዙሪያ መሠራት ያለባቸውን ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ምክክር ለማድረግ መሆኑን ፕሮፌሰር ይስኃቅ ካጫሮ ተናግረዋል።

ዘገባው :- የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ም/ቤት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ነው።

የጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አፌ-ጉባኤ  የተከበሩ አቶ አየለ ቦላ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2018 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳ...
06/01/2026

የጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አፌ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አየለ ቦላ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2018 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
የተከበሩ አቶ አየለ ቦላ ባስተላለፉት መልዕክት የገና በዓል አምላክ ለሰው ልጅ ያለውን ወሰን የሌለው ፍቅርና ትህትና የገለጠበት፣ የጨለማው ዘመን አብቅቶ የብርሃን መውጣትና የድነት የምስራች የተሰማበት ታላቅ ዕለት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ በሃይማኖታዊ እሴቱ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቤተሰብ በፍቅር የሚሰባሰብበት፣ እንደ ገና ጨዋታ ያሉ ባህላዊ እሴቶች የሚንፀባረቁበትና አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት የሰላምና የደስታ ተምሳሌት መሆኑን አብራርተዋል።

የዘንድሮውን የገና በዓል ልዩ የሚያደርገው ኢትዮጵያ የነበረችበትን የፈተና ወቅት አልፋ በሉዓላዊነቷና በኢኮኖሚ ነጻነቷ ከፍታ ላይ በምትገኝበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ የምናከብረው በመሆኑ ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ ተጠቅመን ለሀገራዊ ከፍታችን በአንድነት የምንቆምበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም በዓሉ በታላቅ የድልና የልማት ብስራት የሚከበር እንደሆነ የገለፁት ስሆን ለሀገራዊ ስኬት መሰረቱ የወረዳችን ሁለንተናዊ እድገት መሆኑን በመጥቀስ ሰላምን በማስፈን፣ መሰረተ ልማት እንድታረጋግጥ ጥሬውን አስተላልፏል።

​ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Geressie Zuria woreda People's Council Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share