Ethio Africa-EA

Ethio Africa-EA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Africa-EA, Legal, Amhara Region.

25/03/2024

This version of Facebook uses less data and works in all network conditions.

ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትለው የነበረውን አሁን ለምን "ጦርነት" አለችው?ጦርነት የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ለረጅም ጊዜ ጥንቃቄ ሲያደርጉ የነበሩት ከፑቲን በተዋረድ ያሉት ባለስልጣናትም...
25/03/2024

ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትለው የነበረውን አሁን ለምን "ጦርነት" አለችው?

ጦርነት የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ለረጅም ጊዜ ጥንቃቄ ሲያደርጉ የነበሩት ከፑቲን በተዋረድ ያሉት ባለስልጣናትም አሁን ላይ ጦርነት እያሉ መናገር ጀምረዋል

ፕሬዝደንት ፑቲን

ሩሲያ ላለፉት ሁለት አመት በዩክሬን ያወጀችውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁን ላይ ምዕራባውያን እየተሳተፉ ስለሆነ "ጦርነት" የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች

ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትለው የነበረውን አሁን ለምን "ጦርነት" አለችው?

ሩሲያ ላለፉት ሁለት አመት በዩክሬን ያወጀችውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁን ላይ ምዕራባውያን እየተሳተፉ ስለሆነ "ጦርነት" የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች።

በሞስኮ ጥቃት የፈጸመው “አይኤስአይኤስ-ኬ” ማን ነው?

ሩሲያ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አወጀች

ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት ጦርነት ነው በማለት ሩሲያውያንን ለረጅም እና ለከባድ ጦርነት ለማዘጋጀት አስባለችም ተብሏል።

የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮፕ ባለፈው አርብ እለት የሰጡት አስተያየት ለዩክሬን እና ለምዕራባውያን ጆሮ የሚስብ ላይሆን ይችላል። ነገርግን ሩሲያ ውስጥ ላለፉት ሁለት አመታት ጦርነቱን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" እያሉ እንዲጠሩ ሲነገራቸው የነበሩት ሰዎች የግጭቱ ሁኔታ መቀየሩን እና ተጨማሪ መስዋትነት የሚጠበቅባቸው መሆኑን እንዲያውቁ ለማድረግ ነው።

"ጦርነት ውስጥ ነን። እውነት ነው፣ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ በሚል ነበር የተጀመረው ነገርግን አሁን ምዕራባውያን በዩክሬን በኩል እየተሳተፉ ስለሆነ ጦርነት ሆኗል"ሲሉ ፔስኮብ 'አርጉመንት ኤንድ ፋክት' ለተባለው የሩሲያ መጽሄት ተናግረዋል።

ፔስኮብ አክለውም "በዚህ አምናለሁ። ሁለም ሰው ይህን አውቆ መንቀሳቀስ አለበት"ብለዋል።

ፔስኮብ ይህን ያሉት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለተጨማሪ ስድስት አመት በስልጣን የሚያቆያቸውን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ካሸነፉ ከአምስት ቀናት በኋላ ነው።

ይህ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ከአሜሪካ እና ከአጋሮቿ ጋር ለረጅም ጊዜ የተካረረ ፍጥጫ ውስጥ እንደምትቆይ የሚያመለክት ነው ተብሏል።

የፑቲን እና የፔስኮቭ ንግግር የሩሲያ ባለስልጣናት ለጦርነት ተጨማሪ ምልመላ እንዲያርጉ ፍቃድ የሚሰጥ ነው።

ፔስኮቭ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ያለው ተግባር አሁንም ቢሆን በህግ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ተብሎ ነው የሚጠራው። ነገርግን ምዕራባውያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ስለሆነ ጦርነት ሆኗል ብለዋል ፔስኮቭ።

ጦርነት የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ለረጅም ጊዜ ጥንቃቄ ሲያደርጉ የነበሩት ከፑቲን በተዋረድ ያሉት ባለስልጣናትም አሁን ላይ ጦርነት እያሉ መናገር ጀምረዋል።

ሩሲያ በከፊል የወረረቻቸውን አራት የምራቅ ዩክሬን ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ለመጠቅለል ጦርነቱን እንደምትቀጥል ገልጻለች።
Reference አል-ዓይን

28/09/2023

የአለማችን አራት ህጻናት!
1 . በሶሪያ ጦርነት የቆሰለው ህፃን ለዶክተሩ «እኔ ወደ ፈጣሪ መሄዴ ነው የሆነውን ሁሉ እነግረዋለው»

2 . ኢራቅ ሞሱል ውስጥ ቆስላ እየሮጠች ካሜራማኑ ሲቀርፃት «አጎቴ እባክህ ቪዲዮ አትቅረጸኝ ምክንያቱም ሂጃብ አለበስኩም»

3. አንድ ህፃን በፍልስጤም እጅግ በጣም ይራብና «ፈጣሪ ሆይ እባክህ በቶሎ ወሰደኝ አንተ ከወሰድከኝ በገነት ውስጥ አልራብም እዛ እበላለሁ»

4. በአፍጋኒስታን ጦርነት እጁ ክፉኛ የቆሰለው ህፃን ለሕክምና ዶክተር ጋ ወስደውት ለዶክተሩ «ዶ/ር እጄን ስትቆርጠው ልብሴን አትቁረጠው ተጠንቀቅ ምክንያቱም እኔ ሌላ ልብስ የለኝም እና» አለው ።
የጦርነት አስከፊነትን እንማር።🙏

ጥያቄ መጨረሻንችን ምንድነው የሚለው ነው። ድሮ ድሮ ኢትዮጵያ ስትባል የሆነች ገደል ችጋራም ትንሽ አገር ትመስለኝ ነበር። የነቃ አፉን የፈታ ፖለቲካ የሚችል በሴራ የተካኑ አይመስለኝም ነበር።...
23/08/2022

ጥያቄ መጨረሻንችን ምንድነው የሚለው ነው። ድሮ ድሮ ኢትዮጵያ ስትባል የሆነች ገደል ችጋራም ትንሽ አገር ትመስለኝ ነበር። የነቃ አፉን የፈታ ፖለቲካ የሚችል በሴራ የተካኑ አይመስለኝም ነበር። አሁን ያለዉ የግብፅ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ የሚወሰን አይመስለኝም ነበር። የግብፅ ውሃ የመጠጣት የመልማት የመስራት መብት ከኢትዮጵያ የምትጠይቅበት ዘመን ይመጣል ብየ አላውቅም ነበር። 7.1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ያላት ግብፅ በኢትዮጵያ የውሃ ሀይል ጥያቄ ውስጥ ይገባል ያለ የለም ነበር።
አረቦች ወደ ኢትዮጵያ ይሰደዳሉ ወይስ ይለምናሉ ብሎ የገመተ የለም ነበር። በአማርኛ ኢትዮጵያን እንዲህ እናድርግ ይሄንን ያህል ውሃ ልቀቂልን ብለን መለመን ጀምረናል ማለት ነው። አሁን ናይል ታሪክ ሆኗል። ቁልፍ እየተሰራለት ነው። እስርቤት ውስጥ ያለ አንበሳ መሆን ወይስ ወንዝ መሻገር የማይችል አንበሳ መሆን የሚል ምርጫ መቶልናል። ሱዳን በኢትዮጵያ ልማት መቅናት ጀምራለች። ኢትዮጵያ ስንዴ ስዘራ ቀድማ ዜና የምትሰራው ሱዳን ናት። አብይ ግድቡን ሲጎበኝ ቀድማ ዜና የምትሰራው ሱዳን ናት ነው። መንገድ ከተመረቀ ወታደሩ ትርኢት ካሳየ በኢትዮጵያ ፍቅር የከኑ ሱዳኖች ዜናውን ይቀባበሉታል። የአረብ ዩኒት የሚል ቋንቋ ከናል ጋር ታሪክ ሆኗል። የኛ መጨረሻ ምን ይሆን .? እያለ ይጠይቃል። ኢትዮጵያን መለመን ለሷ መገዛት ወደሷ መሰሰደድ .? ግን መጨረሻችን ምን ይሆን ፣ እያለ ሀሳቡን ይቋጫል። ግብፃውዮ የፖለቲካ ተንታኝ ማህረድ ባስጥ

Source ሱሌማን አብደላ

2033 ምን እንሆናለን።ይህ ምርት ኢስት አፍሪካ ውስጥ ነው። ይህ ምርት ቱርክ ወይም ኮሪያ አሊያም ግብፅ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ከዘር ቆጠራ ወጣ ያለ ሀሳብ ይዘን ከሰራን እመሬት ...
21/08/2022

2033 ምን እንሆናለን።
ይህ ምርት ኢስት አፍሪካ ውስጥ ነው። ይህ ምርት ቱርክ ወይም ኮሪያ አሊያም ግብፅ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ከዘር ቆጠራ ወጣ ያለ ሀሳብ ይዘን ከሰራን እመሬት ላይ ያለውን ፍሬ እንዲህ አምርተን እናያዋለን።
የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አለምን በአንድ መረብ ገዙ። የእስራኤል ሳይንቲስቶች በረሀዋን እስራሌን አረንጓዴ አደረጉ። የማትደፈር እስራኤልን በ45 አመት ውስጥ ሰሩ። የፓክስታን ሳይንቲስቶች ጥላት መከላከያ መሳሪያ አምራች ሆኑ። የቻይና ሳይንቲስቶች ከአሜሪካም ከሩሲያም በልጠው አለምን በምርታቸው አጥለቀለቁ። የሩሲያ ሳይንቲስቶች ሀያል መሳሪያ ይዘው አለምን አኮሩ። የቱርክ (ዬ) ሳይንቲስቶች ድሮን ሰርተው ተከበሩ። የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ግን አንድም በእምነት ወይም በዘር ቆጠራ ላይ ተጠመድው ሺ አመት ሆነን ይላሉ።
አሁን ስለ ኢትዮጵያ ከፍታ ሲወራ ህልም የሚመስለው አለ። አዎ ልክ ነው። እኛ የያዝነውን መሬት ግን አረብ ኤምሬትስ ወይም ግብፅ ወይም እስራኤል ወይም ቻይና ብትይዘው የአለም ትልቁ የበላ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ለመሆን 20 አመት አይወስድባቸውም ነበር። 2033 ከሰራን ምን እንሆናለን ? ከማን ቀዳሜ አገር ሆነን የት ደረጃ ላይ እንደርሳለን .? ሀሳባችሁን አስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልኝ። እመለስበታለሁ።

ሱሌማን አብደላ

ሩሲያ ከባህር ላይ በተኮሰችው ሚሳዔል የዩክሬን ጦር መሳሪያ መጋዝን ማውደሟን አስታወቀች ካሊበር የተባለ ሚሳዔል ከባህር ላይ ሲተኮስከወደሙ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ የአሜሪካ ሂምራስ ሮኬትና ሌ...
21/08/2022

ሩሲያ ከባህር ላይ በተኮሰችው ሚሳዔል የዩክሬን ጦር መሳሪያ መጋዝን ማውደሟን አስታወቀች

ካሊበር የተባለ ሚሳዔል ከባህር ላይ ሲተኮስ
ከወደሙ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ የአሜሪካ ሂምራስ ሮኬትና ሌሎች ከምእራባውያን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ከባህር ላይ በተኮሰው ሚሳዔል በዩክሬን ኦዴሳ ክልል የሚገኝ ጦር መሳሪያ መጋዝን ማውደሙን አስታወቀ።

የሩሲያ ጦር ካሊበር የተባለ ሚሳዔል የተጠቀመ ሲሆን፤ በጥቃቱምበመጋዝኑ ውስጥ የነበረ አሜሪካ ሰራሹ ሂርማስ (HIMARS) የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶችን ማውደሙን አስታውቋል።

በተጨማሪም በመጋዘኑ ውስጥ የነበሩ እና ምዕራባውያን ለዩክሬን የለገሷቸው የፀረ አውሮፕላን መሳሪያዎችን ማውደሙንም አስታቋል።

በተጨማሪም በኬህርሶን ክልል በተካሄደ ውጊያ ሁለት M777 መድፎችን ማውደሙን ያስታወቀ ሲሆን፤ እንዲሁም በዛፖሪዝያ ክልል ደግሞ 100 ቶን ነዳጅ የያዘ ዲፖ ማውደሙን አስታቋል።

ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመለገስ ላይ ሲሆኑ፤ ሩሲያም የተለገሱትን የጦር መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆኗን ገልጻለች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሐምሌ 16 በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ አሜሪካ ሰራሽ "HIMARS" ሮኬቶችን ማውደሙን ማስታወቁ ይታወሳል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች ከተጀመረ 179 ቀናት ተቆጥረዋል

-Africa
#ዜና

21/08/2022

መከላኪያ ውስጥ እየተሰራ ያለው ስራ አንዳንዱ እዚህ ላለሁት ለኔም አይገባኝም።ከወታደራዊ እውቀቴ ልምዴ ከመረዳት አቅሜ በላይ ነው።

አንዳንዱ ደግሞ ይገባኝ እና ለሌላው ለማስረዳት እቸገራለው።ይህ የሚሆንበትም በሁለት ምክንያት ነው።አንድም የግሌ የመግለፅ አቅም ውስንነት ሁለትም ሚስጥር ከሆነስ የሚል ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ስጋት!

በአጭሩ ግን ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የከወነው ስራ እና እየሄድበት ያለውን ጎዳና ላስተዋለ ሰው ኢትዮጵያ በቅርቡ ፈፅሞ በታሪኳ አይታ የማታውቀው የብረት አጥር የሆነ ሰራዊት እንደሚኖራት ፈፅሞ አይጠራጠርም።እደግምልሀለው! 'ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀው ግዙፍ የታጠቀ የሰለጠነ ሰራዊት ባለቤት ትሆናለች።ልብ አድርግ!በታሪኳ ነው ያልኩህ!'

እሄ ወሬ ለማሞቅ እራስን ለማፅናናት ወይም ለተራ ፕርፖጋንዳ እየነገርኩህ ከመሰለህ በብዙ ትስታለህ ወንድሜ።

ተቋሙ አሁን እየደረሰበት ያለውን ዙሪያ መለስ አቅምን ሳይሽኮረመም በደንብ ቢገልፅ ትክክል ይመስለኛል።አንድም ለሀገር ወዳዱ ህዝባችን ተስፋን ያሰንቃል።ሁለትም የቅርብም የሩቅም ጠላቶቻችን በተሳሳተ ግምገማ ተነሳስተው እንዳያሳስቱን ውሳኒያቸውን ደግመው ደጋግመው እንዲያጤኑት ያደርጋል ባይ ነኝ።

በተረፈ ዳግም ህዋት ወደ ጦርነቱ ከገባች ለመከላኪያ ሰራዊት ክፍሎች ውጊያው የሚደርሰው በእጣ ነው!!ከኑማ!

ፎቶ አየር ወለድ ተራራው ኮርስ!

መቶ አለቃ ዘሪሁን አቦቴ

Ayantu tube

አባቶቻችን ያዩልንን ታላቋ ኢትዮጵያ ራዕይን  🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ወደ ድርጊት ቀይሮ አሻራ መጣል ያለበት ያሁኑ ትውልድ ነው ።
07/08/2022

አባቶቻችን ያዩልንን ታላቋ ኢትዮጵያ ራዕይን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወደ ድርጊት ቀይሮ አሻራ መጣል ያለበት ያሁኑ
ትውልድ ነው ።

07/08/2022

በ Federalism የፖለቲካ ስርዓት የክልሎች ቁጥር (the number of constituent units) እየጨመረ ሲሄድ የማእከላዊ መንግስት power እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት እየጨመረ ይመጣል። ይሄ የሚሆነውም በክልሎች መካከል Balance of Power ስለሚፈጠር ነው። ከዚህ በፊት ብቻቸውን ተጽዕኖ ይፈጥሩ የነበሩ ክልሎች በ balance of power እና factionalism ምከንያት ድምጻቸው ይዋጣል። ስለዚህ በርካታ number of constituent units ያለው የ Federal ስርዓት ውሰጥ የማእከላዊ መንግሥቱን challenge ለማድረግ የግድ በአንድነት ካልተንቀሳቀሱ በስተቀር ብቻውን አንድ ክልል በፌዴራል መንግሥቱ ላይ የሚፈጠረው የፖለቲካ ጫና አይኖርም። ይሄንን ኢሳይያስ ይዘን ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ አሁን ላይ የተጀመረው የአዳዲስ ክልሎች ምስረታ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል። በተለይም ከ balance of power አንጻር የጎላ ሚና አለው።

The political insiders

07/08/2022

Breaking New

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ ይሰጣል

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ መረጃ እንደሚያመለክተው ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

Let join us to take the truth thing in ethio
06/08/2022

Let join us to take the truth thing in ethio

Address

Amhara Region

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Africa-EA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category