Adis Kasa - Law Office

Adis Kasa - Law Office Laws and all about laws

I've just reached 6K followers! Thank you for continuing support. I could never have made it without each one of you. 🙏🤗...
21/11/2025

I've just reached 6K followers! Thank you for continuing support. I could never have made it without each one of you. 🙏🤗🎉

Dorgommii Gargaaraa Abbaa Seeraa Mana Murtii Aanaa bahe kana warri ulaagaa guuttan dorgomaa.Baay'ina namoota 100(dhibba ...
22/08/2025

Dorgommii Gargaaraa Abbaa Seeraa Mana Murtii Aanaa bahe kana warri ulaagaa guuttan dorgomaa.

Baay'ina namoota 100(dhibba tokko) tu barbaadama.Carraa bal'aa kana fayyadamaa jenna.

Guyyaan galmee 19/12/2017_27/12/2017 yeroo hojii mootummaatti.

Please read it👇የዴሞክራት ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ ተቀብለው በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ የግብፅን ...
21/07/2024

Please read it👇

የዴሞክራት ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ ተቀብለው በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ የግብፅን አጀንዳ በማራመድና በሌሎች ክሶች ሐምሌ ጥፋተኛ ተባሉ።

በሴናተሩ ላይ የቀረቡትን ክሶች የተመለከተው የኒውዮርክ ፍ/ቤት በመጪው ጥቅምት ወር የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።

ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩበት ወቅት፣ ለዓመታት የግብፅን አጀንዳ በሴኔት ውስጥ ሲያራምዱ እንደነበር ለዚህም ከግብፅ መንግሥት ክፍያ ማግኘታቸውን ዓቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክሮችን በማቅረብ አረጋግጧል።

የሴናተር ሜኔንዴዝ ባለቤት የሆነችው ናዲኔ ሜኔንዴዝ እ.ኤ.አ. በማርች 2020 ገደማ ባለቤቷ ሴናተር ሜኔንዴዝ ከአንድ የግብፅ ጦር ጄኔራል ጋር እንዲገናኙ ፕሮግራም ማዘጋጀቷንና በፕሮግራሙ ላይም ሴናተሩ ከግብፅ ጄኔራል ጋር ተገናኝተው በወቅቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ይካሄድ ስለነበረው ድርድር መወያየታቸውን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

በወቅቱም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ ተደርጎ ይወሰድ እንደነበር የምርመራ ሰነዱ ይገልጻል።

ሴናተሩ ከግብፅ ጄኔራል ጋር በተገናኙ በቀጣዩ ወር ውስጥ (በኤፕሪል 2020 ወይም ገደማ)፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ለሚሳተፉት ለወቅቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ፀሐፊና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውን ያትታል።

በደብዳቤያቸው መግቢያ ላይም፣ " እኔ ይህንን ደብዳቤ የምጽፈው ግብፅ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ያደርጉት የነበረው ድርድር መቋረጥ እንዳሳሰበኝ ለመግለጽ ነው " ማለታቸውን ያስረዳል።

በማከልም፣ " የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በግድቡ ድርድር ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሳድግ እጠይቃለሁ "ማለታቸውን የምርመራ መዝገቡ ይጠቅሳል።

እ.ኤ.አ. በ2021 መገባደጃ ላይ የሴናተር ሜኔንዴዝ ባለቤት የሆነችው ናዲኔ ሜኔንዴዝ አዘውትራ ከምትገናኘው ከግብፅ ጄኔራል ጋር በመነጋገር እሷና ባለቤቷ ሜኔንዴዝ ወደ ግብፅ እንዲጓዙ ፕሮግራም ማመቻቸቷንና ጉዞውም በጥቅምት 2021 መደረጉን ያስረዳል።

በመጀመሪያ ጉዞው መደበኛ ያልሆነ ወይም ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቁጥጥር ውጭ እንዲካሄድ የታቀደ መሆኑን የሚያለክተው የምርመራ መዝገቡ፣ በኋላ ላይ አንድ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ባልደረባ በካይሮ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በማነጋገር ጉዞው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እውቅናና ቁጥጥር የሚደረግበት መደበኛ የኮንግረንስ ልዑክ የሥራ ጉብኝት እንዲሆን ማነጋገሩን ይጠቅሳል።

ነገር ግን ይህ ጥያቄ መቅረቡን ያወቀው የግብፅ ባለሥልጣን እንደዚያ ሊሆን እንደማይችል የሚገልጽ መልዕክት ለናዲን ሜኔንዴዝ መላኩንና ናዲን ሜኔንዴዝም ምልዕክቱን ለሴናተር ሜኔንዴዝ መላኳን በዚህም ምክንያት ሴናተሩና ባለቤታቸው ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እውቅና ውጪ እንደተካሄደ በምርመራ መዝገቡ ተጠቅሷል።

ሜኔንዴዝና ባለቤታቸው ወደ ግብፅ ከተጓዙ በኋላም በካይሮ ከበርካታ የግብፅ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተውና በአንድ ከፍተኛ የግብፅ የስለላ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን የግል መኖሪያ ቤት እራት መብላታቸውን ያስረዳል።

በእነዚህ ወቅቶችም ልዩ መለያ ቁጥር የተከተበባቸው ባለ አንድ ወቄት የሚመዝኑ 22 የወርቅ ባሮችን (አሞሌዎችን) ከግብፅ መንግሥት በክፍያ (በጉቦ) መልክ ማግኘታቸውን፣ በዚያ ወቅት የገበያ ዋጋ መሠረት አንዱ ወቄት የወርቅ ባር 1,800 ዶላር እንደነበርና ክስ ከተመሠረተ በኋላ በወጣ የፍርድ ቤት የብርበራ ማዘዣ ሁለት የወርቅ አሞሌዎች በመኖሪያ ቤታቸው መገኘቱን የምርምራ መዝገቡ ያስረዳል።

የአሜሪካ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደገለጸው፣ ሴናተር ሜኔንዴዝ በተለያዩ ጊዜያት ከግብፅ የስለላ ባለሥልጣናት ጋር መገናኘታቸውን፣ ከእነዚህም መካከል በአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ሚስጥራዊ ክትትል በተደረገበት በሞርተን ሬስቶራንት ውስጥ ከግብፅ የስለላ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እራት በመብላት ለግብፅ መረጃ አሳልፈው መስጠታቸውን እንዲሁም ለግብፅ ምቹ ወታደራዊ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ለማስገኘት ማሴራቸውን ይገልጻል።

ሜኔንዴዝ ለግብፅ መንግሥት ራሳቸው ደብዳቤ አዘጋጅተው ከሰጡ በኋላ ይህንኑ ደብዳቤ በመጠቀም በግብፅ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ሌሎች የኮንግረስ አባላት ያላቸውን ሥጋት ለማግባባት እንደተጠቀሙበት የአሜሪካ ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የክስ ሰነድ ያስረዳል።

በጥቅሉ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ እ.ኤ.አ. በጁን 16 ቀን 2022 ከሜኔንዴዝ ቤት በድምሩ 486,461 ዶላር፣ አንድ ወቄት የሚመዝኑ 11 የወርቅ አሞሌዎችንና አንድ ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት የወርቅ አሞሌዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል።

በአጠቃላይ የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች የተከሰሱ ሲሆን፣ ባለፈው ማክሰኞ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው ተበይኖባቸዋል።

የቅጣት ውሳኔውን ለማስተላለፍ ለመጪው ጥቅም ወር 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ የተያዘ ሲሆን፣ ሴናተሩ በትንሹ ከ20 ዓመት በላይ እስር ሊፈረድባቸው እንደሚችል ሲኤንኤንን ጨምሮ የተለያዩ የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

Credit - Reporter Newspaper
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/adislawoffice

02/11/2016የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ👇👇👇👇https://t.me/adislawoffice
10/07/2024

02/11/2016
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ
👇👇👇👇
https://t.me/adislawoffice

19/10/2016ዜና ችሎት!የግል ተበዳይ የሆነችውን ፀጋ በላቸውን በመጥለፍ እና አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰ ሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያም ላይ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ...
26/06/2024

19/10/2016
ዜና ችሎት!

የግል ተበዳይ የሆነችውን ፀጋ በላቸውን በመጥለፍ እና አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰ ሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያም ላይ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት የ14 ዓመት ጽኑ እስራት አስተላለፈ

ሀዋሳ: ሴኔ 19/2016 ዓ.ም

ሲብክመ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ያቀረበው የሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያም መዝገብ እንደሚያስረዳው በቀን 12/02/2016 ዓ.ም የግል ተበዳይ የሆነችውን ፀጋ በላቸውን በመጥለፍና አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰበት መዝገብ የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የበየነውን ተከሳሹ ያቀረበውን ይግባኝ በመስማት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ወደ 10 ዓመት ከ5 ወር በማድረግ ዝቅ ማድረጉን ዘግበን እንደነበር ይታወቃል።

ይሁንና የክልሉ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የይግባኝ ጥያቄ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተከራከረ ሲሆን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሲብክመ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማየትና በማመዛዘን በዛሬው ዕለት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያምን በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኖበታል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/adislawoffice

05/06/2024

" የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ?

➡ የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም።

➡ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

➡ የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

➡ አከራዮች ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም።

➡ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው አለባቸው።

➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት።

➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሊያንስ አይችልም።

NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/adislawoffice

02/06/2024

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከላይ በተጠቀሰው መዝገብ ቁጥር የሚከተሉትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል

✅ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ስለመሆኑ፡፡

✅ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት ያለዉ ስለመሆኑ፡፡

✅ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
Join👇👇👇 for more information.
https://t.me/adislawoffice

23/09/2016ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገ...
31/05/2024

23/09/2016

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው። #ኤፍቢሲ
Join 👇👇👇

Vacancy
30/05/2024

Vacancy

Labsiin namni lafa baadiyyaa gurgure ykn bite hidhaa hanga waggaa 5 akka adabamu taasisu har'a Mana Maree Bakka Bu'oota ...
14/05/2024

Labsiin namni lafa baadiyyaa gurgure ykn bite hidhaa hanga waggaa 5 akka adabamu taasisu har'a Mana Maree Bakka Bu'oota Ummataatiin ragga'eera.

Labsiin haaraan kun nama qabeenya waloo ykn mootummaa seeraan ala qabatee argame kamiyyuu adabbii hidhaa walfakkaatu kaa’a.

Labsiin har’a ragga’e kun labsii bulchiinsa fi itti fayyadama lafa baadiyyaa waggoota 18 dura bahe fooyyessa.

Mirga qonnaan bulaa, horsiisee bultootaa fi tiksitoota walakkaa lafa irratti qaban fooyyessee, tumaalee mirga dubartootaa fi namoota deeggarsa barbaadanii mirkaneessan of keessatti hammateera jedhama.

Labsichi maal of keessaa qaba?

- Namni kamiyyuu lafa gurguree yookiin bite yoo ta’e; Birrii kuma 100 hanga kuma 200 ykn hidhaa cimaa waggaa 1 hanga waggaa 5 ykn lamaan isaanii adabamuu danda'a.

NB. Akka heera mootummaa FDRE tti "Lafti qabeenya waloo saboota, sablammootaa fi ummatoota Itoophiyaa kan gurguramuu fi jijjiiramuu hin dandeenyedha". Heerri mootummaa lafa baadiyyaa fi magaalaa irratti abbummaa "mootummaa fi ummataaf" kenna.

- Namni kamiyyuu seeraan ala qabeenya ummataa ykn mootummaa yoo weerare; Hidhaa waggaa 1 hanga waggaa 5 ykn maallaqa kuma 30 hanga kuma 100 adabama.

- Namni qabeenya ummataa ykn mootummaa miidhee argame kamiyyuu; Hidhaa waggaa 3 hanga waggaa 7 ykn Birrii kuma 50 hanga kuma 150 adabama.

- Akka labsii haaraa kanaan namni ijaarsa kamiyyuu bakka hayyama hin qabnetti ijaare ykn hayyame waggaa 1 hanga waggaa 3tti ykn Birrii kuma 25 hanga kuma 50 adabama.

- Namni karoora itti fayyadama lafaatiin ala qabeenya kana fayyadamee argame hidhaa waggaa 1 hanga 3 ykn birrii kuma 25 hanga kuma 50 ni adabama.

- Abbaa qabeenyaa abbummaa lafaa ragaa sobaa dhiheessee fi ogeessa ragaa dhokse ykn ragaa sobaa kenne irratti hidhaan darbu, seeraan ala sarbamiinsa seeraa armaan olitti ibsame waliin tokko ta’us adabbiin gara Birrii kuma 20tti gadi bu’eera.
Odeeffannoo dabalataaf 👇👇👇 join godhaa.

https://t.me/adislawoffice

  Lawየገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል።አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም ...
14/05/2024

Law
የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል።

አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰው ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።

ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው።

አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች አሻሽሏል የተባለ ሲሆን የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል ተብሏል።

አዋጁ ምን ይዟል ?

- ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል።

NB. በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው።

- የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል።

- የወል ወይም የመንግስት ይዞታ ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል።
Join 👇👇👇for more info.

Address

Adis
Adis

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adis Kasa - Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Adis Kasa - Law Office:

Share