AMAS Advocates LLP

AMAS Advocates LLP Diligence Matters

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ፡፡                     ...
20/03/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ፡፡
ዒድ ሙባረክ!

09/01/2026

"የባሕል ፍርድ ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር ዝግጅቱ ተጠናቅቋል" አቶ ዓለምአንተ አግደው

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው የባሕል ፍርድ ቤቶች እውቅና መስጠትን እና ወደ ሥራ ማስገባትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የባሕል ፍርድ ቤቶች እውነትን በማውጣት ፍርድን ለመስጠት አይነተኛ የፍትሕ መንገዶች ናቸው ብለዋል።

ሽምግልናን መሠረት አድርገው የሚሠሩ በመኾናቸው እርቅን በማምጣት፣ የበደለን እንዲክስ በማድረግ፣ ቁርሾን በማስቀረት ዘላቂ እና ጤናማ የማኅበረሰብ ግንኙነትን ለመፍጠር አይነተኛ ሚና አላቸው ነው ያሉት።

በመንግሥት በኩልም ዜጎች ባሕላቸውን እንዲያሳድጉ እና በመረጡት የመዳኘት መብታቸው እንዲከበር ኀላፊነት ያለበት በመኾኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት መኾኑን አንስተዋል።

በክልሉ ምክር ቤት የባሕል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል አዋጅ ወጥቶ ወደ ተግባር ተገብቷል ነው ያሉት። የአዋጁን አፈጻጸም የሚከታተል በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰብሳቢነት የሚመራ የአማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙንም ጠቁመዋል።

እስከ ቀበሌ ድረስ ጥናቶችን ማድረግ፣ የእውቅና መስጫ እና የማስተግበሪያ መመሪያ ማውጣት፣ የትግበራ ፍኖተ ካርታ እና የሥልጠና ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ የተግባቦት ስትራቴጅ መቅረጽ እና ሌሎች ሰፊ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም አንስተዋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም አዋጁን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር እና የባሕል ፍርድ ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸዋል። ታኅሣሥ 21 እና 22/2018 ዓ.ም በክልል ደረጃ የእውቅና እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

መርሐ ግብሩ ከየወረዳው የተወከሉ ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አዋጁን ለማሥፈጸም ኀላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት፣ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እንደሚከናወንም አብራርተዋል።

በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ በኾኑ ቀበሌዎች ሥራው እንደሚጀመርም ገልጸዋል። በባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ የሚደረጉ ሽምግልናን ጨምሮ 15 የባሕላዊ ግጭት መፍቻ ሥርዓቶች መለየታቸውንም ተናግረዋል። በቀጣይም ጥናት እየተደረገ ሊጨመር እንደሚችል ጠቁመዋል።

"የባሕል ፍርድ ቤቶች የመደበኛ ፍርድ ቤቱን የሚተኩ ሳይኾኑ ጎን ለጎን የሚሠሩ የዜጎች አማራጭ የፍትሕ ሥርዓቶች ናቸው" ብለዋል። እውቅና ሲሰጣቸውም ባሕሉ እንዲዳብር ታሳቢ የተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል። ለዚህም የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በአስገዳጅነት ተፈጻሚ እንዲኾኑ ተደርጓል ነው ያሉት።

ሥራቸውን ሲሠሩም የማኅበረሰቡን የባሕል እሴት በጠበቀ መልኩ የሚያከናውኑ ይኾናል ብለዋል። የባሕል ፍርድ ቤት ዳኛ ኾነው የሚመረጡ ሽማግሌዎች ገለልተኛ እና ታማኝ ኾነው ሰብዓዊ መብቶችን እና ሕገ መንግሥቱን የማክበር ኀላፊነት እንዳለባቸውም አብራርተዋል።

ለባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ውጤታማነት እና ለአዋጁ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

09/01/2026

አዲስ የዲፕፌክ ቴክኖሎጂ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ላይ ስጋት እየደቀነ መሆኑ ተገለጸ

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም (WEF) ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ የዲፕፌክ (Deepfake) ቴክኖሎጂዎች በዲጂታል ማንነት ማረጋገጫ ስርዓቶች ላይ ከባድ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን ገለጸ።

በፈረንጆቹ ጥር 8 ቀን 2026 ይፋ የሆነው ይኸው ሪፖርት፣ በተለይ የሰዎችን ፊት በሌላ የመተካት (Face-swapping) ቴክኖሎጂ ወንጀለኞች የባንክና የፋይናንስ ተቋማትን የደህንነት ስርዓት ለመስበር እየተጠቀሙበት መሆኑን ያመላክታል።

ወንጀለኞች የሰዎችን ፊት የሚቀይሩ መተግበሪያዎችን እና የሐሰት ምስሎችን በቀጥታ ወደ ካሜራ ሲስተም የሚልኩ ቴክኖሎጂዎችን (Camera Injection) በማቀናጀት፣ ተቋማት ደንበኞቻቸውን በአካል ሳይገኙ የሚያረጋግጡበትን (KYC) ሂደት እያታለሉ እንደሚገኙ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ይህ ድርጊት በተለይ በፋይናንስ ዘርፍ እና በክሪፕቶ ምንዛሬ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የደህንነት አደጋ እየፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

ሪፖርቱ ለቀጣዩ አንድ ዓመት የሚስተዋሉ አምስት ዋና ዋና አዝማሚያዎችን የተነበየ ሲሆን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች በዝቅተኛ ዋጋ ለሁሉም መገኘታቸው የጥቃቱን ብዛት እንደሚጨምረው ተጠቁሟል።
ወንጀለኞች ከፋይናንስ ዘርፍ ባለፈ ዲጂታል መታወቂያ ወደሚጠይቁ ሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች ትኩረታቸውን እንደሚያዞሩም በሪፖርቱ ተመልክቷል።

በተጨማሪም፣ በቴክኖሎጂው የሚሰሩ የሐሰት ምስሎች ጥራት እየጨመረ መምጣቱ ምስሎቹን ከእውነተኛው ለመለየት አስቸጋሪ እንደሚያደርጋቸው ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል።

ምንም እንኳን የዲፕፌክ ቴክኖሎጂ እየረቀቀ ቢመጣም፣ አሁንም ድረስ በምስሎቹ ላይ የሚታዩ መጠነኛ ግድፈቶች መኖራቸውን ሪፖርቱ ጠቁሟል።

እነዚህም የብርሃን አለመመጣጠን፣ የንግግር እና የከንፈር እንቅስቃሴ አለመገጣጠም፣ እንዲሁም የምስል ጥራት መጓደል መሆናቸው ተገልጿል።

እነዚህን ድክመቶች በመጠቀምም የላቁ የመለያ ዘዴዎችን (Detection models) ማዘጋጀት እንደሚገባ ተመልክቷል።

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም የፋይናንስ ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ አበልጻጊዎች እና መንግስታት በጋራ በመሆን የተቀናጀ የመከላከያ ስርዓት እንዲገነቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933

09/01/2026

የባሕል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን

ባህርዳር፣ ታህሳስ 27/2018(አብክመ ጠ/ፍ/ቤት)

የባህል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት በወጣው አዋጅ ቁጥር 298/2017 መሰረት እውቅና ተሰጧቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የሚደረጉ የባሕል ፍርድ ቤቶች በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል።

የሥረ ነገር ሥልጣን

የባሕል ፍርድ ቤቶች ክርክሮችን ማየት የሚችሉት ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸው በባሕላዊ ፍርድ ቤት እንዲታይ ፍቃድ ከሰጡ በኃላ ሲሆን በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን አላቸው👇

👉 የፍትሐብሔር ጉዳዮች (በገንዘብ መጠን፣ በንብረቱ እና በጉዳዩ አይነት ገደብ ሳይደረግበት)፤

👉 በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮችን (አነስተኛ የወንጀል አይነቶች) እና የደንብ መተላለፍ ድርጊቶች፤

👉 በሌሎች በዐቃቢ ሕግ ክስ አቅራቢነት በሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ የወንጀል ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ባይኖራቸውም👇
👉 በክርክሩ ውስጥ ያሉ ወገኖችን ማስታረቅ
👉 ካሳ መወሰን እና ማስፈጸም
👉 ወጪ እና ኪሳራ የማስከፈል ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡

👉 ከዚህ ህግ ውጪ በሌሎች ህጎች በግልጽ ተለይቶ የመወሰን ስልጣን በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን አላቸው፡፡

የግዛት ወይም አካባቢያዊ ሥልጣን

ከላይ የተመለከተው የባሕል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የባሕል ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ጉዳይ ለማየት ከስር ከተመለከቱት መስፈርቶች መካከል ቢያንስ አንዱ የተሟላ መሆን ይጠበቅበታል 👇

👉 ከተከራካሪ ወገኖች መካከል ቢያንስ አንዱ የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ስር በሚገኝ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ ወይም ተወላጅ ከሆነ፤

👉 ለክርክር ምክንያት የሆነው ቋሚ ንብረት የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ስር በሚገኝ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፤

👉 ለክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የተጀመረው ወይም ፍፃሜ ያገኘው የባሕል ፍርድ ቤቱ የሥልጣን ወሰን ውስጥ ከሆነ ነው፡፡

👉 ከላይ አካባቢያዊ የዳኝነት ሥልጣን በሚመለከት ከተቀመጡ ማሳያዎች በተለየ መልኩ የሚያስቀምጥ የባህል ህግ በሚኖርበት ጊዜ የባሕል ሕጉ ተፈፃሚነት የሚኖረው ይሆናል፡፡

ሌሎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይወዳጁን👇

Facebook:
https://web.facebook.com/Amharascourt
Telegram:
https://t.me/Spc2016
Twitter(X):
https://x.com/Amharascourt
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/amharascourt/
Tiktok:
https://tiktok.com/
You Tube :
https://www.youtube.com/
Website:
https://amhsc.gov.et

በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገባቸው ጉዳዮች   መግቢያ   ግብር የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን መንግሥትም የዜ...
08/01/2026

በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገባቸው ጉዳዮች
መግቢያ
ግብር የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን መንግሥትም የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት በማረጋገጥ ረገድ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልገውን ገቢ የሚያገኝበት ምንጭ ነው። የግብር ሕግ እንደማንኛውም ሌሎች ሕጎች ሁሉ ማኅበረሰቡ የደረሰበትን ሁለንተናዊ የእድገት ደረጃ ከግምት ባስገባ መልኩ ተቀርፆ በሥራ ላይ የሚውል እንደመሆኑ በየወቅቱ የሚኖሩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ለውጦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሻሻል ይኖርበታል።
የአገራችንም የግብር ሥርአት በየጊዜው የሚከሰቱ ለውጦችን ከግምት ባስገባ መልኩ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል። በቅርቡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው የግብር ሕግ አይነቶች አንዱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 ሲሆን በአዋጅ ቁጥር1395/2017 ማሻሻያ ተደርጎበታል። በዚህ አጭር ጽሑፍ የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአጭሩ እንዳስሳለን።
የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች
 ከመቀጠር፣ ከቤት ኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር
ከመቀጠር፣ ከኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር ምጣኔዎች በማሻሻያ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡ ይኸውም በቀድሞ የገቢ ግብር አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 11) ተደንግጎ የነበረው ከግብር ነፃ ከሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ወርሃዊ ገቢ መጠን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የግብር ምጣኔ ድረስ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ በቀድሞው ሕግ ከገቢ ግብር ነፃ የሆነው እስከ ብር ስድስት መቶ (600) ያለ ገቢ የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(6) መሠረት እስከ ብር ሁለት ሺ (2,000) ድረስ ያለ ከመቀጠር የሚገኝ ወርሀዊ ገቢ ከግብር ነፃ እንዲሆን ተደርጓል። በተጨማሪም ከፍተኛው የማስከፈያ ምጣኔ የሆነው 35% ከአስር ሺ ዘጠኝ መቶ (10,900) ብር ወርሃዊ ገቢ ጀምሮ ይጣል የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ ግን ይሄው የ35% ምጣኔ ከአስራ አራት ሺ (14,000) ብር በላይ ወርሀዊ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ይሆናል።
ሌላው በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገው በኪራይ እና ንግድ ሥራ ገቢዎች ምጣኔ ላይ ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ (አንቀፅ 14(2)) እና 19(2) መሠረት እስከ ብር ሰባት ሺ ሁለት መቶ (7,200) ድረስ ያሉ አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢዎች ከግብር ነፃ የነበሩ ሲሆን ይኸው መጠን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(😎 እና 2(10) መሠረት ማስተካከያ ተደርጎበት ወደ ብር ሃያ አራት ሺ (24,000) አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢ ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከፍተኛው የ35% የግብር ምጣኔ የሚጣልበትን የኪራይ እና የንግድ ሥራ የገቢ መጠን በተመለከተ በማሻሻያ አዋጁ በቀድሞ አዋጅ ከነበረው ከብር አንድ መቶ ሰላሳ ሺ ስምንት መቶ (130,800) በላይ ከፍ በማድረግ ከብር አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺ (168,000) በላይ አመታዊ ገቢ ላይ እንዲሆን ተደርጓል።
ሌላኛው ከግብር ምጣኔ አንፃር ለውጥ የተደረገው ከዕድል ሙከራ በሚገኙ ገቢዎች ላይ ነው። ቀደም ሲል ከዕድል ሙከራዎች ገቢ ያገኘ ሰው የገቢውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 57(1)፤ በማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(22) መሰረት ከዕድል ጨዋታ ገቢ ያገኘ ሰው ከገቢው ላይ 20% (ሃያ በመቶ) ግብር መክፈል ይጠበቅበታል። ነገር ግን ይሄ የግብር መጠን በዕድል ሙከራ ከአንድ ሺ ብር በታች ባገኘ ሰው ላይ አይጣልም።
 የግብር ከፋይ ደረጃዎች
ሌላኛው በማሻሻያ አዋጁ ለውጥ ከተደረገባቸው ነጥቦች መካከል አንዱ የግብር ከፋይ ደረጃዎችን የተመለከተው ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀፅ 3 መሠረት የደረጃ “ሀ”፣ “ለ” እና “ሐ” በሚል በሶስት የግብር ከፋይ ደረጃዎች ከፋፍሎ ያስቀመጣቸው ሲሆን ክፍፍሉም ጠቅላላ አመታዊ ገቢን ታሳቢ ያረገ ነው። በዚህም መሰረት ድርጅት ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢው ብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው በደረጃ “ሀ” ስር የሚመደብ ሲሆን፣ ከብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) በታች እና ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በላይ አመታዊ ገቢ ያላቸው (ድርጅቶችን ሳይጨምር) ደግሞ ደረጃ “ለ” ስር ይጠቃለላሉ። ድርጅትን ሳይጨምር አመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በታች የሆኑ ግብር ከፋዮች በደረጃ “ሐ” ስር ይመደባሉ።
ነገር ግን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(2) መሠረት በሶስት ደረጃዎች የመክፈሉ ሂደት ቀርቶ የግብር ከፋዮች ደረጃ “ሀ” እና “ለ” በሚሉ ሁለት ደረጃዎች ብቻ እንዲከፈል ተደርጓል። ከአመታዊ ገቢ ምጣኔውም አንፃር ቀደም ሲል የነበረው እንዲሻሻል ተደርጎ በደረጃ “ሀ” ስር የሚወድቁ ግብር ከፋዮች ድርጅቶች ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢያቸው ከብር ሁለት ሚሊዮን (2,000,000) እና በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች ሲሆኑ ከዚህ መጠን በታች የሆነ ጠቅላላ አመታዊ ገቢ ያላቸው ሰዎች (ድርጅቶችን ሳይጨምር) በደረጃ “ለ” ስር እንዲመደቡ ተደርጓል።
 የገቢ ምንጭ (የታክስ መሰረት) ማስፋት
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁ በቀድሞው አዋጅ ያልነበረ አዲስ የግብር ምንጭ አካቶ የወጣ ነው። ይኸውም በማሻሻያ አዋጁ ላይ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢም ግብር እንደሚከፈልበት በግልፅ ተደንግጓል። በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ አንቀፅ 2(1) መሰረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግልቶችን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን (በበይነ መረብ) መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም በገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው። ይህም ከማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣ ከምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣ ከአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች፣ ከደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ ከገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ (ክራውድ ፈንዲንግ)፣ ከአባልነት ክፍያዎች፣ ከዲጂታል ወይም ከአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣ ከማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግልቶች እና ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎችን ያካትታል፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ነዋሪ ወይም ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የዲጂታል አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ 5% የማይበልጥ የገቢ ግብር እንደሚከፍል በአዋጅ አንቀጽ 2(17 ተደንግጓል)። የዲጂታል አገልግሎት ምንነትን በተመለከተ፣ የማስከፈያ ምጣኔ፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ሌሎች ተያያዥነት ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ የሚንስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት የሚወሰን ስለመሆኑ በማሻሻያ አዋጁ ተጠቅሷል።
ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራው ትርፍ ለማግኘት ታስቦ በመደበኛነት የሚከናወን ከሆነ፣ ፈጣሪው ድርጅት ከሆነ፣ የሂሳብ መዝገብ የሚያዝ ከሆነ ወይም ከንግድ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ተቀናሽ የሚደረጉለት ከሆነ የሚገኘው ገቢ እንደ ንግድ ሥራ ገቢ እንደሚቆጠር ከማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(11) መረዳ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጭ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኙ ገቢዎች እንደሌላ ገቢ ተቆጥረው በአዋጁ ሠንጠረዥ “መ” መሠረት ግብር የሚጣልባው ሲሆን ዝርዝር አፈፃፀሙም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ መሠረት የሚወሰን ይሆናል። ስለሆነም የዲጂታል ይዘት አመንጪዎች እንደማንኛውም ግብር ከፋይ ሁሉ መለያ ቁጥር የማውጣት፣ ገቢን የማስታወቅ እና ሌሎችም የታክስ ከፋዮች ግዴታዎች ይኖሩባቸዋል ማለት ነው።
 አማራጭ አነስተኛ ግብር
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት ነው። ግብር ከፋዮች ምንም አልሰራንም (ገቢ አላገኘንም) ወይም ስለከሰርን ግብር ልንከፈል አይገባም በማለት ማስታወቅ የተለመደ ነገር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ማናቸውም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ለአመታት በኪሳራ ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ ነው። ይህም ግብር ሳይከፍሉ ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስገንዘበናል። ከዚሁ መነሻ ከግብር ለመሸሽ ኪሳራ የሚያስታውቁ ትክክለኛውን ግብር እንዲከፍሉ፣ በትክክል ኪሳራ ያጋጠማቸው ደግሞ መክሰራቸው ሲረጋገጥ የከፈሉት ግብር እንዲካካስ ለማስቻል ሲባል አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት እንዲካተት ተደርጓል።
አማራጭ አነስተኛ የግብር ምጣኔን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀፅ 2(11) መሠረት ማናቸውም ድርጅት ወይም ሰው ግብር በሚወሰንበት የግብር አመት ከሁሉም የንግድ ሥራ የገቢ ምንጮች ባገኘው ትርፍ ላይ ሊከፍል የሚገባው ግብር በዚሁ የግብር አመት ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ2.5% (ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) በታች ከሆነ በአዋጁ በተመለከተው የማስከፈያ ምጣኔ መሠረት አማራጭ አነስተኛ ግብር መክፈል እንደሚኖርበት ተደንግጓል።
 በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ላይ የተደረገ ገደብ
ሌላኛው የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ይዞት የመጣው ጉዳይ በጥሬ ገንዘቦች የሚደረጉ ግብይቶች ላይ ገደብ ማበጀት ነው። በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ስለግብር ከፋዩ ግብይት በቂ መረጃ እንዳይኖር በማድረግ ለታክስ መሰወር ድርጊት በር ከፋች ይሆናል። ይህንንም ለመቀነስ እንዲያስችል ማናቸውም ግብር ከፋይ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ ቼክ፣ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ የባንክ ድራፍት፣ ከባንክ ሂሳብ ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ በማስተላለፍ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጣቸው የክፍያ መፈጸሚያ መንገዶች ካልሆነ በስተቀር በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ሰው ጋር በተደረገ ጠቅላላ ግብይት ወይም ከአንድ ግብይት ጋር በተያያዘ የሚፈጸም ክፍያ ወይም ከአንድ ሰው ጋር ከተፈጸመ አንድ ግብይት ወይም ተግባር ጋር የተያያዘ ክፍያ/ግብይቶች ከሃምሳ ሺ (50,000) ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ መቀበል አይቻልም። ነገር ግን ይህ ገደብ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በተለዩ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ከማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(28) ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ማሻሻያዎች ጨምሮ ገቢ ስለሚጣመርበት ሁኔታ፣ ግብር ቀደም ብሎ የሚከፈልበትን አሰራር እና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካቶ ወደ ሥራ የገባ ሕግ ነው። ምንጭ የፍትሕ ሚኒስቴር
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን!!
ዌብሳይት:- aabof.com.et
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP
ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA
ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu

04/01/2026

አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ!

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበርን በዘላቂነት ለመከላከል የወሰደው አዲሱ የአሰራር ለውጥ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነጥቦች በአጽንኦት ተገንዝበው ተግባራዊ እንዲያደርጉ አቶ ሲሳይ ገዙ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ቢሮ ኃላፊ አሳስበዋል።

1. የነባር ደረሰኞች ዕድሜ አብቅቷል!

በተለያዩ ማተሚያ ቤቶች ሲታተሙ የቆዩ ነባር ደረሰኞች አገልግሎት የሚያበቃው ታኅሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ነው።

ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ልዩ መለያ (QR-Code) የሌለው ማንኛውም ደረሰኝ በሕግ ፊት ዋጋ የለውም።

2. "QR-Code" ያለው ደረሰኝ ብቻ!

ከጥር 1 ቀን ጀምሮ በግብይት ወቅት ጥቅም ላይ መዋል ያለበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ እና ልዩ መለያ (QR-Code) ያለው ደረሰኝ ብቻ ነው።

ይህ ደረሰኝ የሌላቸው ግብር ከፋዮች ታክሳቸውን ማስላትም ሆነ ማሳወቅ አይችሉም።

3. የማስጠንቀቂያው ጥብቅነት

ተቀባይነት ማጣት፦ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ነባሩን ደረሰኝ ይዘው ወደ ገቢዎች ሚኒስቴር የሚቀርቡ ግብር ከፋዮች ሰነዳቸው ተቀባይነት አይኖረውም።

የሕግ ተጠያቂነት፦ ሕገ-ወጥ ደረሰኝ መያዝ ወይም መጠቀም የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን፣ በሕግም ያስቀጣል።

4. የታክስ ከፋዮች ግዴታ

ማተሚያ ቤቱ አንድ ብቻ በመሆኑ ሊፈጠር የሚችለውን ወረፋ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ሁሉም ግብር ከፋይ እስከ ጥር 1 ቀን ሳይጠብቅ በአስቸኳይ አዲሱን ደረሰኝ ማሳተም እና ዝግጁ መሆን ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ፦ "አላወቅኩም ነበር" ወይም "አላተምኩም" የሚሉ ምክንያቶች ከጥር 1 ቀን በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም!

ሊንኩን ላይክ በማድረግ ወቅታዊና ጂኦፓለቲካዊ መረጃዎችን በትንታኔ ይኮምኩሙ።
https://t.me/amasadvocatesllp

ለአማራ ክልል መንግሥት ሠራተኞች አስደሳች የሕግ ማሻሻያ ተደርጎላቸዋል=====================================አድስ አዋጅ ፀደቀ ህገወጥ ቤቶች ህጋዊ ሊሆኑ ነው!የአማራ ክል...
04/01/2026

ለአማራ ክልል መንግሥት ሠራተኞች አስደሳች የሕግ ማሻሻያ ተደርጎላቸዋል
=====================================
አድስ አዋጅ ፀደቀ ህገወጥ ቤቶች ህጋዊ ሊሆኑ ነው!

የአማራ ክልል መሬት ቢሮ አዲስ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ይፋ አድርጓል።የመንግስት ሰራተኞች በውርስ እና በስጦታ መሬት ማግኘት ይችላሉም ብሏል አዋጁ

አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ የተካተቱት 6 ወሳኝ ነጥቦች:-

1 በአዲሱ አዋጅ ካሁን በፊት ተግባራዊ በተደረጉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህጎች ያልነበሩና የገጠር መሬት ባለይዞታዎችን መብትና ጥቅም ለማስፋት በግል ይዞታ ላይ የለማን የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥ እና ማስተላለፍ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

በዚህም መሠረት በከተሞች ዙሪያ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መሬት ገዝተው ቤት የሰሩ ዜጎች በአዲስ ውል ቤታቸውን ህጋዊ ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው።

2 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መሬታቸውን በስጦታም ይሁን በውርስ ማስተላለፍ የሚችሉት በገጠር መሬት አዋጅ ለተፈቀደላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነበር፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸዉ መሬት የማግኘት መብት ሊኖራቸዉ የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጥቅም ገድቦ ቆይቷል። በአሁኑ አዋጅ የመንግስት ሰራተኞች ከቤተሰባቸው በዉርስና በስጦታ መሬት ማግኘት እንዲችሉ ይፈቅዳል።

3 በአዲሱ አዋጅ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የይዞታ መብትን ለፈለጉት ሰው በስጦታ፣ በውርስ ማስተላለፍ መብትን ለማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይፈቅዳል።

4 የገጠር መሬት ይዞታን ለብድር ዋስትና ማስያዣነት በመጠቀም የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበትን ድንጋጌ አካቷል። ይህም የክልሉን አርሶ አደር የብድር አቅርቦት ችግር መፍትሄ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

5 በአዲሱ አዋጅ በአስገዳጅ ሁኔታ የመሬት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱ ዲጂታላይዝ መሆን እንዳለበት በግልፅ ተመላክቷል፡፡

6 ለሴቶች፤ ለህፃናት፤ ከቀያቸዉ በጊዜያዊነት ለለቀቁ፤ በህግ ጥላ ስር ያሉ፣ ለህሙማን፤ ለአረጋዊያንና…ወዘተ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት በመሰጠት የህግ ከለላና መብት ጥበቃ ሰጥቷል፡፡
Via Wollo Addis

Address

Guinea Bissau St. , German Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AMAS Advocates LLP posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share