23/08/2026
ቡልድግሉ ወረዳ በግዳጅ ላይ ለተሰማራው ለሚሊሻ አባላት ለማበረታታት የገንብ ድጋፍ አደረገ።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦።
(ቡልድግሉ፣ነሀሴ 16/2018 ዓ.ም) ቡልድግሉ ወረዳ በኩርሙክ ወረዳ በግዳጅ ላይ ለተሰማሩ ሚሊሻያ አባላት 150,000 ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገላቸው ።
የቡልድግሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በክሪ አብዱላሂ ሚሊሻ አባላቱ ከመንግስት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት እና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን እያበረከቱት ላለውን አስተዋፆኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በዚህም አጠቃላይ ለክልሉ ህዝብ እና መንግስት ኩራት መሆናቸውንም ተናግረው ለወደፊቱም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
የተደረገላቸውን ድጋፉ የቡልድግሉ ወረዳ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጠይብ ሰቢት በቦታው ተገኝተው ለሚሊሻ አባላቱ አስረክበዋል ሲል የቡልድግሉ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል ።