የህግ አማካሪ legal consultant

የህግ አማካሪ  legal consultant Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የህግ አማካሪ legal consultant, Lawyer & Law Firm, Butajira, Addis Ababa.

14/10/2017

የቅጥር፣ የመብትና የወሊድ እረፍትን ጨምሮ ዝርዝር
ጉዳዮችን በመያዝ የተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ
አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ማሻሻያ
የተደረገበት የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ
ዝርዝር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
ረቂቅ አዋጁ ነባሩን የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ
ቁጥር 515/99ን ለመተካት የተዘጋጀ ነው።
ነባሩን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት
የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ፣ ብቃት እና ስነምግባር
የተላበሰ የፐብሊክ ሰርቪስ እንዲፈጠር ለማስቻል
የሚለው ይገኝበታል።
ከዚህ ውጭ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚካሄደው
ምልመላ እና የመረጣ ስርዓት በመሰረታዊነት በመለወጥ
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ እና የስራ ብቃት ማረጋገጫ
አሰራር ለመዘርጋት የአዋጁ መሻሻል ማስፈለጉን በሰነዱ
ላይ ተመልክቷል።
እንዲሁም በነባሩ አዋጅ የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና
በፐብሊክ ሰርቪስ ውስጥ ያለውን የኪራይ ሰብሳቢነት እና
የመልካም አስተዳደር ችግር መፍታት የሚያስችል የህግ
ማዕቀፍ እንዲኖር ለማድረግ ነው ተብሏል።
በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ የመንግስት መስሪያ ቤት
አደረጃጀትን፣ የስራ ምዘና፣ የደመወዝ ስኬል እና አበል፣
የስራ አካባቢ ደህንነት እና ጤንነት፣ መብት እና
ግዴታዎች፣ የዲሲፕሊን እርምጃዎች፣ የመንግስት
ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና ሌሎች ዝርዝር
ጉዳዮች ተካተዋል።
በረቂቅ አዋጁ ተሻሽለው የቀረቡ እና አዲስ የተካተቱ
ድንጋጌዎች ያሉ ሲሆን፥ አንድ የመንግስት ሰራተኛ ወደ
ፐብሊክ ሰርቪስ የሚገባበት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ
ስርዓትን መዘርጋት እንደሚገባ በማሻሻያው ቀርቧል።
የጊዜያዊ ሰራተኛ ቅጥርን በተመለከተ በነባሩ ህግ
የጊዜያዊ ሰራተኞች መብት እና ግዴታን በመመሪያ
መወሰኑ በአፈፃፀሙ ላይ ክፍተት ሲፈጥር የነበረ በመሆኑ
በሰራተኞች መብት አጠባበቅ ላይ ከፍተኛ ችግር ሲፈጥር
መቆየቱ ተነስቷል።
በዚህም መሰረት በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ላይ መሰረታዊ
መብቶች እና ግዴታዎች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው
በሚወጡ በአዋጅ ወይም በደንብ መመላከት
እንዳለባቸው ተመላክቷል።
ልዩ ሙያ እና እውቀት ያላቸውን ሰራተኞች የመንግስት
መስሪያ ቤቶች በጋራ ቀጥረው በጋራ መጠቀም እንዲችሉ
የሚያስችል አሰራር መዘርጋት አስፍላጊ መሆኑም
በድንጋጌው ተካቷል።
ምን ማሻሻያዎች ተደረጉ?
ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የሰራተኛው ልዩ እውቀት እና
ሙያዊ አቅም መስሪያ ቤቱ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
ብቻ እንደሆነ እና የቅጥሩ ሁኔታ፣ የሚቆይበት ጊዜ፣
ደመወዝ አከፋፈል እና ሌሎች ሁኔታዎች ሚኒስቴሩ
በሚያወጣው መመሪያ እንድሚወሰን በረቂቁ ላይ
ተጠቅሷል።
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በክፍት የስራ መደብ ላይ
የደረጃ እድገት ሊሰጠው የሚችለው ከሌሎች መስፈርቶች
በተጨማሪ ለስራ መደቡ ያለውን የብቃት ማረጋገጫ
የማቅረብ ግዴታውን ሲፈፅም ይሆናል።
በነባሩ አሰራር ከአንደ ዓመት በላይ ለትምህርት ወይም
ስልጠና የሄደን የመንግስት ሰራተኛ ለመተካት
በተጠባባቂነት የሚመደቡ ግለሰቦች ለረዥም ጊዜ በስራ
መደቡ ላይ ያለውድድር እንዲመደቡ መደረጉ ቅሬታ
ሲያስከትል ቆይቷል።
በአዲሱ ረቂቅ አዋጅም ማሻሻያ በማድረግ ምድባው
ከገንዘብ እና ከጥቅማጥቅም ጋር የተያያዘ በመሆኑ
በውሳኔ ብቻ ምድባውን ማካሄዱ ፍትሃዊ ባለመሆኑ
በውድድር መፈፀም እንዳለበት ነው የተደነገገው።
አንድ የመንግስት ሰራተኛ ወደ ሌላ የመንግስት መስሪያ
ቤት በሚዘዋወርበት ጊዜ እንድ አዲስ የሙከራ ቅጥር
ሳይቆጠር፣ የጤና እና የፖሊስ ማስረጃ ሳይጠየቅ፣ ሌሎች
በአዋጁ የተቀመጡ መብቶች እና ጥቅሞች ተጠብቀውለት
በዝውውር እንዲስተናገድ የሚገልፅ አሰራር ተካቷል።
በተለያየ የስራ ቦታ የሚገኙ ባለትዳሮችን ለማገናኘት
ሲባል የመንግስት ሰራተኛውን ስምምነትን መሰረት
በማድረግ ተመሳሳይ መደብ ካልተገኘም ዝቅ ባለ ደረጃ
እና ደመወዝ አዛውሮ ማሰራት እንደሚቻልም በረቂቁ ላይ
ቀርቧል።
ፈቃድን በተመለከተ ለሴት የመንግስት ሰራተኞች
የሚሰጠው የድህረ ወሊድ ፈቃድ ከ60 ቀናት ወደ 90
ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል።
ይህም የሆነው እናቶች ህጻኑን ለመንከባከብ በቂ የእረፍት
ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የህክምና ባለሙያዎች
አስተያየት በመስጠታቸው እና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ
በመውሰድ ነው።
የወሊድ ፈቃድ ድንጋጌው ፅንስ የተቋረጠባቸው ሴቶችን
ያካተተ ሲሆን፥ በተለይም የቅድመ ወሊድ ከወሰዱ በኋላ
የፅንስ መቋረጥ የሚያጋጥማቸው ሴቶች የመውለጃ
ወራቸው ከገባ በኋላ በመሆኑ የፅንስ መቋረጥ
ያጋጠመበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ የቅድም ወሊድ
ወይም የድህረ ወሊድ ፈቃድ የምትተቀምበት አሰራር
እንዲካተት ተደርጓል።
ባል የትዳር አጋሩ ስትወልድ 5 ቀን ብቻ ፈቃድ
እንዲሰጠው ማድረጉ በቂ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ
ጉዳይ ስለሆነ ወንዶች የአጋርነታቸውን ሚና እንዲጫወቱ
10 ቀናት እንዲሰጣቸው በሚል ተሻሽሏል።
የህመም ፈቃድን በተመለከተ አሁን ስራ ላይ ያለው አዋጅ
በዓመት ፈቃድ ላይ ያለ ሰራተኛ ስትታመም በምን መልኩ
እንደሚስተናገድ በግልፅ አላስቀመጠም።
ይህ ደግሞ ችግር ስላስከተለ በዓመት ፈቃድ ላይ የሚገኝ
ሰራተኛ ከታመመ እና በሃኪም ፈቃድ ከተሰጠው የዓመት
ፈቃዱ ተቋርጦ የህመም ፈቃዱን እንዲጠቅም
እንደሚደረግ በግልፅ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል የህመም ፈቃድ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት
ከሙሉ ደመወዝ ጋር፣ ለተከታዮቹ ሶስተ ወራት ደግሞ
ከግማሽ ደመወዝ ጋር እና ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት
ያለደመወዝ እንደሚሰጥ ነባሩ አዋጅ ይደነግጋል።
በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ግን የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት
ከሙሉ ደመወዝ ጋር፣ ለተከታዮቹ ሁለት ወራት ደግሞ
ከግማሽ ደመወዝ ጋር እንዲሰጣቸው በሚል ተሻሽሏል።
በአዋጁ ላይ ሌሎች በርካታ ማሻሻያዎችን ያካተተ ሲሆን፥
የምክር ቤቱ አባላት ከመረመሩት በኋላ ለሚመለከተው
ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።
በምህረት አንዱዓለም

የመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ የፍትሐብሔርክርክሮች አካሄድ (General outlinefor first instance ordinary civilproceedings)የመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ የፍትሐብሔር ክ...
12/10/2017

የመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ የፍትሐብሔር
ክርክሮች አካሄድ (General outline
for first instance ordinary civil
proceedings)
የመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ የፍትሐብሔር ክርክሮች
አካሄድ (General outline for first instance
ordinary civil proceedings)
1. የክስ አቤቱታ (ከሰነድና ከፅሁፍ ማስረጃ
እንዲሁም ከማስረጃ ዝርዝር ጋር) ይቀርባል፡
2. ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ይዞ እንዲቀርብ
ይታዘዛል፡፡
3. የመከላከያ መልስ (ከሰነድና ከጽሑፍ ማስረጃ
እንዲሁም ከማስረጃ ዝርዝር ጋር) ይቀርባል፡፡
4. የመከላከያ መልሱ ከቀረበ በኋላ የጽሑፍ ክርክሩ
ያቆማል፡፡
5. የጽሑፍ ክርክሩ ከቆመ በኋላ ክሱን ለመስማት
ይቀጠራል፡፡
6. በተቀጠረው ቀን ባለጉዳዮች ራሳቸው ወይም
ወኪሎቻቸው ይቀርባሉ፡፡
7. ባለጉዳች ከፅሑፍ አቤቱታቸው ጋር ያላቀረቡትን
የፅሁፍ ማስረጃ ይዘው ይቀርባሉ፡፡
8. የጽሑፍ ማስረጃ ሁሉ በባለጉዳች ወይም በፍርድ
ቤቱ ትዕዛዝ ተጠቃሎ ይገባል፡፡ፍርድ ቤቱ
ባለጉዳዮችን ወይም ወኪሎቻቸውን ይመረምራል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከቀረበ ውሳኔ
ይሰጥበታል፡፡
9. በተደረገው ምርመራ ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ካመነ
ወዲያውኑ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
10. ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ካላመነ የክርክሩ ጭብጥ
ይያዛል፡፡
11. ጭብጡ ከተመሠረተ በኋላ ክርክሩን መስማትና
ማስረጃ መመርመር ይቀጥላል፡፡
12. ለሁለቱም ወገን ምስክሮች መጥሪያ ይላካል፡፡
13. የሁለቱም ወገን ምስክሮች ተሟልተው ይቀርባሉ፡፡
14. ከሳሹ (በተወሰኑ ሁኔታዎች ተከሳሹ) ሙግቱን
ይከፍታል፡፡
15. ሙግቱን የጀመረው ወገን ምስክሮቹ
የሚመሰክሩለትን ነጥብ በአጭሩ ያስረዳል፡፡
16. ምስክሮች እውነት ለመናገር ይምላሉ ወይም እውነት
እንደሚናገሩ ያረጋግጣሉ፡፡
17. ሙግቱን የጀመረው ሰው ምስክሮቹን አንድ በአንድ
አቅርቦ ዋና ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ፍርድ ቤቱ
በማንኛውም ሰዓት አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ
ይጠይቃል፡፡
18. ሙግቱን የከፈተው ወገን ምስክሮቹን አሰምቶ
ከጨረሰ በኋላ ለሌላኛው ወገን ምስክሮቹን
የሚያስረዱለትን የመከላከያ ነጥብ በአጭሩ
አስረድቶ በተመሣሣይ ሁኔታ ምስክሮቹን ያሰማል፡፡
19. ማስረጃ የመስማቱ ሂደት ሲጠናቀቅ ግራ ቀኙ
የመዝጊያ ቃላቸውን ይሰጣሉ
20. በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የፍርድ ውሳኔውን
ይሠጣል
ፍርድ
1. የማስረጃ መሰማት ሥርዓት ተጣርቶ ካለቀ በኋላ
ተከራካሪ ወገኖች የመዝጊያ (የማጠቃለያ) ቃላቸውን
ይሰጣሉ፡፡ ሙግቱን የጀመረው ወገን መጀመሪያ ስለ
ክርክሩ አጠቃላይ የመዝጊያ ቃሉን ይሰጣል፡፡ ከዚያ
ሌላኛው ወገን ስለ ክርክሩ ያለውን አስተያየት
በመዝጊያ ቃል ያቀርባል፡፡ በመጨረሻም ክርክሩን
የጀመረው ወገን ለክርክሩ ያለውን ጠቅላላ
የመዝጊያ ሐሳብ ያቀርባል
2. የማስረጃ መሰማት ሥርዓቱ ተጣርቶ ካለቀና ከላይ
የተጠቀሰው የመዝጊያ ቃል ከተሰጠ በኋላ ፍ/ቤቱ
የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል (ቁ.273)፡፡
3. ለፍርድ ውሳኔው መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ
ማስረጃዎች፤
1. የምስክሮች ቃል (ባለጉዳዮቹ
አቅራቢነት ወይም በፍ/ቤቱ
ትዕዛዝ ቀርበው ቃላቸውን የሰጡ፣
በምትክ ዳኛ የተሰበሰቡ
የምስክሮች ቃል ወይም ከፍ/ቤት
ውጪ በመሃላ የተሰጡ
የምስክሮች ቃል)፣
2. በኤክስፐርቶች የተሰጡ
ማረጋገጫዎች፣
3. በባለጉዳዮቹ ወይም በፍ/ቤት
ትዕዛዝ የቀረቡ የፅሑፍ
ማስረጃዎችና ሰነዶች፣
4. በምትክ ዳኛ የተሰበሰቡ ሌሎች
ማስረጃዎ፣
5. ባለጉዳዮች በፅሑፍ ወይም ፍርድ
ቤቱ በሚመረምራቸው ጊዜ
የሚሰጧቸው የእምነት ቃላት፣
6. ፍ/ቤቱ በቁ.272 መሠረት ባደረገው
ምርመራ የተገኙ መረጃዎች፣
7. የታወቁ ጉዳዮች (Judicial
notice)፣
8. በሕግ የተወሰደ የህሊና ግምት
(Legal presumption)፣
9. ያንድን ነገር አፈጣጠርና ሂደት
ማሳያ (Demonstration)፣
10. ፍ/ቤቱ በዓይነት እንዲመለከታቸው
የሚቀርቡለት ነገሮች
(Exhibits) ሊያጠቃልል
ይችላል፡፡
4. የእነዚህ ማስረጃዎች ተቀባይነት
(Admissibility) እና እውነተኛነት
(Credibility) ፍ/ቤቱ ይወስናል፡፡
5. ባለጉዳዮቹ ወይም ወኪሎቻቸው የመክፈቻና
የመዝጊያ ንግግር ሲያደርጉ ወይም
ምስክሮችን በሚመረምሩበት ጊዜ
የሚናገሯቸው ቃላት እንደማስረጃ መወሰድ
የለባቸውም፡፡
6. ከላይ በክፍል (ሠ) (3) ከተጠቀሰው ውጪ
ዳው ከችሎት ውጭ ያያቸው ወይም
የሰማቸው ነገሮች ወይም ያገኛቸው
ማስረጃዎች ለውሳኔው መሠረት መሆን
የለባቸውም፡፡
7. የቀረበው ክርክር ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ ነገሩ
እንዳለቀ ወዲያውኑ ወይም በአጭር ቀነ
ቀጠሮ በሚወስነው ጊዜ በግልጽ ችሎት
ፍርድ መስጠት አለበት (ቁ.180)፡፡
8. የፍርድ አሰጣጥ፣ የውሳኔው አፃፃፍና ፎርም
በቁ. 181 እና 183 በተደነገገው መሠረት
መሆን አለበት፡፡
9. በአንድ የፍርድ ሐተታ ላይ የተያዘው ጭብጥ፣
ጭብጡ እንዴት እንደተወሰነና የተወሰነበት
ምክንያት መገለፅ አለበት፡፡ በመጀመሪያ
ደረጃ የሚሰጥ ፍርድ ለክርክሩ መነሻ
የሆነውን ዋነኛ ጉዳይ ባጭሩ የሚገልጽ
መሆን አለበት (ቁ.182(1))፡፡
10. የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ተከራካሪዎቹ
ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም
በግልጽ ባላመለከቱት ጉዳይ ላይ ፍርድ
ለመስጠጥ አይችልም (ቁ.182(2))፡፡
11. በክርክሩ ላይ ከቀረቡት ብዙ ጭብጦች አንዱ
ጭብጥ ብቻ ቢወሰን ሌሎቹንም ጭብጦች
የሚያጠቃልል ከሆነ ክርክሩ ባንዱ ጭብጥ
ብቻ ሊወሰን ይችላል፡፡ ካልሆነ ግን
እያንዳንዱ ጭብጥ ለየብቻው ውሳኔ
ማግኘት አለበት(ቁ.182(4))፡፡
source
ethiopianattorney.blogspot.co.ke/2013/12/general-outline-for-first-instance.html?m=1

12/10/2017

SHEGER FM 102.1 RADIO
የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ተሻሻለ፡፡
ተሻሽሎ ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት
በቀረበው ረቂቅ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ
መሠረት የወሊድ ፈቃድ ከ90 ቀን ወደ 120 ቀን
ወይንም 4 ወር ከፍ ብሏል፡፡
አዋጁ ለምክር ቤቱ ሲቀርብ ለወሊድ ፈቃድ
ከቀድሞ አዋጅ 30 ቀን መጨመሩ መልካም
ቢሆንም “እናት ደህና፤ ልጅም ጤና” ይሆኑ ዘንድ
ፈቃዱ ወደ 6 ወር ከፍ ማለት እንዳለበት የጠየቁ
የምክር ቤቱ አባላት ነበሩ፡፡
በረቂቅ አዋጁ የመጦሪያ እድሜ የሚራዘምበት
አዲስ አዋጅም ተካቷል፡፡
የጡረታ እድሜ ከደረሰ በኋላ የሠራተኞችን
ትምህርት፣ ልዩ እውቀትና ችሎታ ለመሥሪያ ቤቱ
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም እስከ 10 ዓመት ድረስ
የጡረታ ጊዜን ማራዘም እንደሚቻል በረቂቅ አዋጁ
ሰፍሯል፡፡
አዋጁ ስለ ቅጥርና የደረጃ እድገትም አዳዲስ
አንቀፆችን የያዘ ሲሆን ለዝርዝር እይታ
ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
(ትዕግሥት ዘሪሁን)

‘እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ውሳኔ’ ምን ዓይነት ነው?BY ABRHAM YOHANNES በህግ አግባብ የተቋቋመ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮውሳኔ ከሰጠ በኋላ ለአፈጻጸም ሲቀርብ ውሳኔውእንዳልተሰጠ ...
07/10/2017

‘እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ውሳኔ’ ምን ዓይነት ነው?

BY ABRHAM YOHANNES

በህግ አግባብ የተቋቋመ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ
ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ለአፈጻጸም ሲቀርብ ውሳኔው
እንዳልተሰጠ ተቆጥሮ አፈጻጸሙን በያዘው ፍርድ ቤት ዋጋ
የሚያጣበት የህግ መሰረት አለ? ከሰበር ችሎት ውሳኔዎች
ለመረዳት እንደሚቻለው አንድ ውሳኔ በሶስት መንገዶት
እንዳልተሰጠ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ
የስረ ነገር የዳኝነት ስልጣን አለመኖር ነው፡፡ ምንም እንኳን
ችሎቱ በአንድ መዝገብ ላይ ይህን አቋም ቢያራምድም
በሌሎች ሁለት መዝገቦች ላይ ግን ራሱን በመቃረን የስረ
ነገር የዳኝነት ስልጣን የፍርድ ቤትን ውሳኔ እንዳልተሰጠ
እንደማያስቆጥረው የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ሌሎቹ ሁለት
መንገዶችና የችሎቱ ተቃርኖ የታየባቸው መዝገቦች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የሥረ ነገር የዳኝነት ስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት
የተሰጠ ውሳኔ
አንድ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከማየቱ በፊት የስረ ነገር የዳኝነት
ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ያለበት ሲሆን የስረ
ነገር የዳኝነት ስልጣን በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም
በማናቸውም የክርክር ደረጃ ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያነሳው
የሚገባው ጉዳይ መሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና
231/1/ ሰ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው
ጉዲይ ነው፡፡ የሥረ ነገር የዳኝነት ስልጣን በሌለው ፍርድ
ቤት የተሰጠ ውሳኔ ደግሞ በመርህ ደረጃ እንዳልተሰጠ
የሚቆጠር ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 64703 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 9፣
231/1/ ሰ
2. ችሎት ለማስቻል በህጉ የተቀመጠው የዳኞች ቁጥር
ባልተሟላበት ሁኔታ የሚሰጥ ውሳኔ
ጉዳዮች በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሠረት የሚመሩበት
አይነተኛ አላማ ክርክሮችን ፍትሃዊ በሆነ እና ሥርዓት
ባለው መንገድ በመምራት በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ
ወጭ እንዲቋጩ ማድረግ ስለመሆኑ ይታመናል፡፡ ይህንኑ
የሥነ ሥርዓት ሕጉን አላማ ለማሳካት ደግሞ በሕጉ
የተመለከቱትን የስነ ሥርዓት ድንጋጌዎችን
እንደየአግባብነታቸው መከተልን የግድ ይላል፡፡ በስነ
ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎችን
እንደየአግባብነታቸው ያለመከተል በተከራካሪ ወገኖች
መሰረታዊ መብት ላይ አሉታዊ ውጤት ማስከተሉ አይቀሬ
ነው፡፡ ስለሆነም በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት
ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ሊኖራቸው የሚገባው ለጉዳዩ
አግባብነት ሲኖራቸው እንጂ በዘፈቀደ ሊሆን አይገባም፡፡
ድንጋጌዎቹ አግባብነት ያላቸው ስለመሆኑ ከመለየቱ
በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ ተገቢነት አለው የሚለውን ትዕዛዝ
ወይም ውሣኔ የሚሰጠው ችሎትም በሕጉ አግባብ
የተመለከተው የዳኞች ቁጥር የተሟላ ሊሆን ይገባል፡፡
በሕጉ አግባብ ሊሟላ የሚገባው የዳኞች ቁጥር ሳይሟላ
የሚሰጠው ትእዛዝ ወይም ውሣኔ እንደተሰጠ
የማይቆጠርና ሕጋዊ ውጤት ሊኖረው የሚገባ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ 73696 ቅጽ 13
3. በሞተ ሰው ውክልና ክርክር ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ
በሞተ ሰው ስም ቀደም ብሎ የተሰጠን ውክልና በመያዝ
የሚቀርብ ክስ፣ የሚደረግ ክርክር እና የሚሰጥ ውሣኔ
ህጋዊ ዕውቅናና ውጤት ሊሰጠው የማይገባው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 95587 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 57፣ ፍ/ህ/
ቁ. 2232/1/
ከሰ/መ/ቁ. 64703 ጋር ተቃርኖ
አንድ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በሕግ ከተሰጠው የስረ
ነገር የዳኝነት ስልጣን ውጭ የሆነ ጉዳይ በማየት የሰጠው
ቢሆንም፣ ይህ ውሣኔ በይግባኝ ታይቶ እንዲታረም
ካልተደረገ በስተቀር በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 212 በጉዳዩ
ላይ አስገዳጅነት ያለውና የመጨረሻ ውሣኔ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 85718 ቅጽ 15
በሕግ አግባብ በፍ/ቤት የተሰጠን ውሣኔ የሞራልን
ወይም የሕሊናን አስተሳሰብ መሠረት በማድረግ ዋጋ
አልባ ሆኖ እንዲቀር ማድረግ በየትኛውም መለኪያ
ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም፡፡
ሰበር መ/ቁ. 38041 ቅጽ 8
[1] አመልካች ሻምበል ለታይ ገ/መስቀል እና ተጠሪ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 አስተዳደር ጽ/ቤት
ሐምሌ 29 ቀን 2003 ዓ.ም.
[2] አመልካች ወ/ሪት ሃና አበባው እና ተጠሪ አቶ አብዱ
ይመር /በሌለበት/ ሚያዝያ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.
[3] አመልካች ወ/ሮ ሐዋ በከር እና ተጠሪ እነ አቶ ቶፊቅ
መሀመድ 2 ሰዎች ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም.
[4] አመልካች አቶ ቴዎድሮስ አማረ እና ተጠሪ አቶ አዲሱ
ፍሰሃ ሰኔ 03 ቀን 2005 ዓ.ም.
[5] አመልካች ታደሰ ገ/መስቀል ተጠሪዎች እነ ሙሉጌታ
ዘካርያስ /7 ሰዎች/ መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
from the post of Ethiopian legal brief.

የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት፡ የስልጣን ምንጭ እናህጋዊነትከ10 ዓመት በላይ ማንሳትና መጣል በኋላ ‘ የአስተዳደርህግ መግቢያ’ የሚለው መጽሀፌ እነሆ 2010 ላይሲጠናቀቅ ትልቅ እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡...
22/09/2017

የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት፡ የስልጣን ምንጭ እና
ህጋዊነት
ከ10 ዓመት በላይ ማንሳትና መጣል በኋላ ‘ የአስተዳደር
ህግ መግቢያ’ የሚለው መጽሀፌ እነሆ 2010 ላይ
ሲጠናቀቅ ትልቅ እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ የህትመት ነገር
ከተሳካ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል፡፡ የሚከተለው ጽሁፍ
የተወሰደው ከመጽሐፉ ረቂቅ ላይ ነው፡፡
የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት፡ የስልጣን ምንጭ እና ህጋዊነት
በተለምዶ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት (አንዳንዴ ቢሮ)
እየተባለ የሚታወቀው አካል ስልጣንና ተግባሩ በህግ
ተወስኖ አልተቋቋመም፡፡ በአቋሙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ
የግል ቢሮ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህገ መንግስቱ
የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በአግባቡ እንዲያከናውን
ለማገዝ የሚረዱ የቢሮ ስራዎችን ከማከናወን በስተቀር
በማናቸውም መንግስታዊ ሆነ አስተዳደራዊ ጉዳዮች
የመወሰን ሆነ ለበታች አካላት መመሪያ የማስተላለፍ
ስልጣን የለውም፡፡
ጽ/ቤቱ በታሪካዊ አቋሙ ከነበረው የቆየ ስም እንዲሁም
የደርግ መውደቅን ተከትሎ በሽግግሩ መንግስት ጊዜ
በዘልማድ በሚያከናውናቸው መንግስታዊ ተግባራት
(በተለይ ቅሬታ ሰሚ በመሆን) የተነሳ በህግ ሳይሆን
በዕውቅና (de facto) ህልውና ያገኘ የመንግስት ተቋም
ለመሆን በቅቷል፡፡
በሰ/መ/ቁ. 16195 [1] ተጠሪዎች በመንግስት ለተወረሱ
መኖሪያ ቤቶቻቸው አበል እንዲከፈላቸው የሥራና ከተማ
ልማት ሚ/ር በወሰነላቸው መሰረት ይከፈላቸው ዘንድ
በአመልካች ላይ ክስ አቀረቡ፡፡ ከክርክሩ በኋላ ክሱ
እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ያለው አበል እንዲከፈላቸው
ተፈረደላቸው፡፡ ፍርዱም በከፍተኛው ፍ/ቤት ፀና፡፡ ሆኖም
የሰበር ችሎት ሻረው፡፡ በመዝገቡ ላይ የሥራና ከተማ
ልማት ሚ/ር ውሳኔ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ እንደተሻረ
ተመልክቷል፡፡ በዚህ መልክ መሻሩ ለስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ
ለመሻር ምክንያት ሆኗል፡፡ ችሎቱ ህገ መንግስቱን
በማጣቀስ ለማብራራት እንደሞከረው፤
[በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.] ህገ-መንግስት አንቀጽ 74/4/ ሁሉም
ሚኒስቴሮች የሚገኙበትን የሚኒስቴሮች ምክር ቤት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚመራ፣ እንደሚያስተባብርና
እንደሚወክል ተመልክቷል፡፡ እንዲሁም…የአስፈፃሚ
አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አ/ቁ
4/87 አንቀጽ 11/1/ ሥር እያንዳንዱ ሚኒስትር፣
የሚመራውን ሚኒስቴር መ/ቤት የሚመለከቱ ሥራዎች
ፕሮግራሞችና ህጎች አፈፃፀም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ
ሚኒስትሩና ለሚኒስቴሮች ምክር ቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከነዚህ ህጎች አኳያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስቴር መ/
ቤቶችን በበላይነት የመምራትና ስራቸውንም የመቆጣጠር
ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴር መ/ቤቶቹ
ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የፈፀሙትን ስህተት
ማረምና ማስተካከል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ስር
የሚወድቅ ነው፡፡
የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር ውሳኔን የሻረው ጽ/ቤቱ
እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይደለም፡፡ ሆኖም የሰበር
ችሎት የውሳኔውን ህጋዊነት ያጣራው የጠቅላይ
ሚኒስትሩን ህገ መንግስታዊ ስልጣን በማመሳከር ነው፡፡
ሁለቱ እንደ አንድ አምሳል፣ አንድ አካል ተቆጥረዋል፡፡ ይህ
የማደባላለቅ ስህተት በሌሎች የህግ ባለሞያዎች ላይም
ይታይል፡፡ በቅርቡ የጠቅላይ ዓቃቤ ባጠናቀረው
የተጠቃለሉ ህጎች ማውጫ ላይ ‘ለጠ/ሚኒስቴር ጽህፈት
ቤት ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን ማቋቋሚያ ህጎች’
የሚል ርዕስ እናገኛለን፡፡
ከላይ ለመጠቆም እንደተሞከረው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/
ቤት የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር የግል ቢሮ ነው፡፡ የግል
የሆነበት ምክንያት እንደ አገሪቱ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በህግ
አልተቋቋመም፡፡ የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.
131/1991 ጽ/ቤቱን ህጋዊ ሰውነት አላብሶ
አቋቁሞታል፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ግን ተመሳሳይ
የህግ መሰረት የለም፡፡ በስልጣኑ ላይ የሚነሳው ህጋዊና
ህገ መንግስታዊ ጥያቄ የማቋቋሚያ አዋጅ አለመኖር ብቻ
አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ ጽ/ቤቱን የሚያቋቁም አዋጅ
ቢወጣም እንኳን ከጽህፈት ስራ የዘለለ በማናቸውም
መንግስታዊ ጉዳዮች ውሳኔ የማስተላለፍ ሚናና ተግባር
ሊኖረው አይችልም፡፡
የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከህገ መንግስቱ የሚመነጩት
ስልጣናት ከእርሱ በቀር ወደ ሌላ አይተላለፉም፡፡
ከምክትል ጠ/ሚኒስትሩ በቀር ሚስት/ባል፣ ልጅ፣ ወላጅ፣
ጽ/ቤት ሆነ ሌላ ማናቸውም አካል የጠቅላይ ሚኒስትሩን
ስልጣን መጋራት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በህግ የተቋቋመ
የሚኒስቴር መ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ጽ/ቤቱ መሻር
ይችላል ማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ ተመሳሳይ
የመሻር ስልጣን አለው የማለት ያክል ነው፡፡
የሰበር ችሎት ይህን ግዙፍ ህገ መንግስታዊ ስህተት በሰ/
መ/ቁ. 34665 [2] ላይም ደግሞታል፡፡ በመዝገቡ ላይ
የተነሳው የህግ ጥያቄ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀት (ደብተር) የመሰረዝ ስልጣን ህጋዊነት ሲሆን የፍሬ
ነገሩ መነሻ ታሪክ አስደማሚና አስገራሚ ነው፡፡ ነገሩ
እንዲህ ነው፡፡ በወቅቱ ማለትም በ1991 ዓ.ም. ላይ
የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር በመስሪያ ቤቱ ይገኙ የነበሩ
የቤት ጉዳዮችን ከሰራተኞቹ ጋር ለአዲስ አበባ
መስተዲድር ምክር ቤት ስራና ከተማ ልማት ቢሮ
እንዲያስረክብ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ትእዛዝ ደረሰው፡፡
በትዕዛዙ መሰረት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጉዳዮቹንና ሰራተኞቹን
አስረከበ፡፡ የአ/አበባ መስተዳድ ቤት ስራና ከተማ ልማት
ቢሮ ከየካቲት 1 ቀን 1991 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ጉዳዮቹን
ተረክቦ ማስተዳደር ጀመረ፡፡ ቢሮው በዚህ ሁኔታ
የአመልካቾችን ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር በመሰረዙ
ምክንያት በስር ፍ/ቤት ክስ አቅርበው ጥያቄያቸው
ተቀባይነት አጣ፡፡ ይግባኝ ቢሉም አቤቱታቸው ውደቅ
በመደረጉ ጉዳዩ ወደ ሰበር ችሎት አመራ፡፡ አመልካቾች
በሰበር ክርክራቸው ደብተሩ ስልጣን በሌለው አካል
እንደተሰረዘ በመጥቀስ የቢሮውን ተግባር ህጋዊነት
ሞግተዋል፡፡
በህግ የተቋቋ የመንግስት መ/ቤት ስልጣን፣ መብትና
ግዴታ ወደ ሌላ የሚተላለፈው ህግ አውጭው አምኖበት
በአዋጅ ሲያጸድቀው ብቻ ነው፡፡ አንድ መ/ቤት በበላይ
ትዕዛዝ (ያውም በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት) የሚበተን ከሆነ፣
ስልጣኑን ተቀምቶ ወደ ሌላ የሚተላለፍ ከሆነ ያኔ
ህጋዊነትና ስርዓት አልበኝነት አንድ ሆነው ተዋህደዋል፡፡
የሰበር ችሎት ይህ አስደንጋጭ እውነት
አልተገለጠለትም፡፡ የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሲያጸና በሰ/
መ/ቁ. 16195 ያሰፈረውን (የተሳሳተ) ትንተና በመድገም
ነገሩን በአጭሩ ቋጭቶታል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 34665 የተለየ
ነጥብ የሚስተዋለው ጠቅላይ ሚኒስትሩና ጽ/ቤቱ ቦታ
ተቀያይረዋል፡፡ ለንፅፅር ይረዳ ዘንድ ሙሉ ዓረፍተ ነገሩ
እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
የጠቅላይ ሚ/ ር ጽ/ ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ስራ
የመከታተልና በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ያለው
እንደመሆኑ መጠን የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር ቤቶችን
የሚመለከት ጉዳይ ለአ/አበባ ስራና ከተማ ልማት ቢሮ
እንዲያስተላልፍ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ስራውንና
ሰራተኞቹን ለቢሮው አስተላልፏል፡፡ (ሰረዝ የተጨመረ)
[1] አመልካች የኪራይ ቤቶች ድርጅት እና ተጠሪ እነ
ልዕልት ተናኘወርቅ ኃ/ስላሴ /6 ሰዎች/ ቅጽ 4 ሚያዝያ
11 ቀን 1999 ዓ.ም.
[2] አመልካች እነ አቶ ናትናኤሌ ዘውገ /2 ሰዎች/ እና
ተጠሪ እነ ወ/ሮ እግዜሩ ገ/ሕይወት /2 ሰዎች/ ሰ/መ/
ቁ. 34665 ቅጽ 10 ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም
BY ABREHAM YOHANNIS

ሺሻን ለሽያጭ ከማቅረብና ከመጠቀምጋር ተያይዘው የሚፈፀሙ ወንጀሎች******** WRITTEN BY  ****** *           ABIYOU GIRMA TAMIRATየሺሻን ምንነት፣ ሺሻ የሚይደር...
17/09/2017

ሺሻን ለሽያጭ ከማቅረብና ከመጠቀም
ጋር ተያይዘው የሚፈፀሙ ወንጀሎች
******** WRITTEN BY ****** * ABIYOU GIRMA TAMIRAT
የሺሻን ምንነት፣ ሺሻ የሚይደርሰውን
ጉዳት፣ ሺሻን መጠቀም፣ ማስጠቀም እና ወደ አገር
አስገብቶ ማከፋፈል ከሕግ አንፃር የሚያስከትለው
ኃላፊነት ስለመኖሩ፣ ፖሊስና የወረዳ (ቀበሌ)
አስተዳደር ሠራተኞች ሺሻ የሚያጨሱና የሚያስጨሱ
ግለሰቦችን እንዲሁም የማስጨሻ ዕቃዎችን
የሚይዙበትና ማስጨሻ ቤቶችን የሚዘጉበትን
እንዲሁም ዐቃቤ ሕግ ሺሻ በሚያስጨሱ ግለሰቦች
ላይ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት ላይ የሕግ
አስተያየት እና ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ ላይ እንደ
አጠቃላይም ከሺሻ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ችግሮች
የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ላይ ያተኮረ አነስተኛ ጥናት
ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚሁ መሠረትም ይህ
አነስተኛ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
የሺሻ ምንነት
ሺሻ የሚለው ቃል “ሺሼ” /Shishe/ ከሚለው
የፐርሺያ ግንድ ካለው የአረቢኛ ቋንቋ የተወሰደ ቃል
ሲሆን የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም በጠርሙስ ውስጥ ያለ
ውሃ ማለት ነው፡፡ ሺሻ ከጠርሙስ ውስጥ ካለ ውሃ
ውስጥ በቀጭን አየር ማስተላለፊያ ቱቦ በአፍ
የሚሳብ የትምባሆ ምርት ነው፡፡ ሺሻ ለማጨስ ሁለት
ነገሮች የሚያስፈልጉ ሲሆን እነርሱም የማጨሻ
ዕቃውና የሺሻ ትምባሆው ናቸው፡፡ የሺሻ ትምባሆው
በሺሻ ማጨሻ ዕቃው አናት በኩል ባለው ጎድጓዳ
ሠሀን በኩል ተጨምሮ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡
ሺሻ ከ3ዐዐ ዓመታት በፊት በሠው ልጆች የሚታወቅ
የትምባሆ ምርት ሲሆን ከባህላዊው ትምባሆ
የሚለየው በተጨማሪነት መልካም መዓዛ ከሚሰጡ
እና ጣፋጭነት ካላቸው ንጥረ ነገሮች ጋር ተቀይጦና
ተደባልቆ አገልግሎት ላይ በመዋሉ ነው፡፡ በሺሻ
ውስጥ የሚገኘው የትምባሆ መጠን ከ10 እስከ 20
ግራም የሚመዝን ሲሆን በሶስት ዓይነቶችም
ይከፈላል፡፡ እነዚህም ሙአስል ወይም ማስል /
Mu’essel or Maasel/፣ ቱምባክ ወይም አጃሚ /
Tumbak or Ajami/ እና ጁራክ /Jurak/
ይባላሉ፡፡ ሙዜል /Mu’essel/ የሚባለው የሺሻ
ዓይነት 3ዐ% ትምባሆ እና 7ዐ% ጣፋጭነት ያለው
በፖም፣ በማንጐ፣ በሙዝ፣ በእንጆሪ፣ በብርቱካን፣
በወይን፣ በሜንታ፣ በካኘቹኖ ወይም በሌሎች ቃናዎች
የሚዘጋጅ የሺሻ ዓይነት ሲሆን በተለያዩ ፍራፍሬዎች
ምስል ባሸበረቀ ካርቶን ወይም የኘላስቲክ ከረጢት
ታሽጐ ለገበያ ይቀርባል፡፡ ቱምባክ ወይም አጃሚ /
Tumbak or Ajami/ የተሰኘው የሺሻ ዓይነትም
ሙሉ በሙሉ ከንጹህ ጥቁር ትምባሆ የተዘጋጀና ሌላ
ነገር የማይቀየጥበት የሺሻ ዓይነት ነው፡፡ ሶስተኛውና
ጁራክ /Jurak/ ተብሎ የሚጠራው የሺሻ ዓይነት
ደግሞ ከሕንድ እንደመጣ የሚታመንና በብዛት ህንድ
ውስጥ የሚዘወተር እና በመካከለኛነት የሚመደብ
ፍራፍሬዎችን የሚይዝ ከጣፋጭነቱ ጋር በተያያዘ
የየትኛውም ፍራፍሬ ጣዕም እንዳይኖረው ተደርጐ
የሚዘጋጅ የሺሻ ዓይነት ነው፡፡ ከሶስቱ የሺሻ ዓይነቶች
መካከልም ሙዜል ወይም ማዜል የተባለው የሺሻ
ዓይነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች
ውስጥ በርካታ ተጠቃሚዎችን አፍርቷል፡፡
የሺሻ ማጨሻ መሣሪያ ራስ ከብረት የተሠራ አካል፣
ጠርሙስ፣ ከሰው አፍ ጋር የሚገናኝ ተጣጣፊ ተያያዥ
ቱቦ አለው፡፡
የዕቃው ራስ ጎድጓዳ ሳህን ያለው ሲሆን
በሚያጤሱበት ወቅት ከሰሉንና ትምባሆውን
በመሸከም ያገለግላል፡፡
ጎድጓዳው ሳህን ትምባሆ ከተሞላ በኋላ
በብልጭልጭ ወረቀት ወይም በብረት ይሸፈናል፡፡
ከሰልም ትምባሆውን እንዲያሞቅ በአናቱ ላይ
ይደረጋል፡፡
ዝርጉ ሳህን ከጎድጓዳው ሳህን በታች የሚቀመጥ
ሲሆን አስቀድሞ አገልግሎት ላይ የዋለ ከሰል
ማስቀመጫ በመሆን ያገለግላል፡፡
ብረታማ አካሉ ቱቦ ያለው ሲሆን ከውሃው መያዣ
ጃምባ ጋር በማገናኘት ያገለግላል፡፡
ሺሻ የሚያደርሰው ጉዳት
በዓለም ላይ በቀን ውስጥ ከ1ዐዐ ሚሊዮን ሕዝቦች
በላይ ሺሻ የሚያጨሱ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ፣
በቱርክ፣ በሕንድ፣ በፓኪስታን፣ በባንግላዲሽ እና
በተወሰኑ የቻይና ክፍሎች ውስጥ ሺሻ ማጨስ
የተለመደ እና ተራ የሆነ ተግባር ነው፡፡ በተወሰኑ
የመካከለኛው ምስራቅ ክፍሎች ውስጥም ከሲጃራ
ይልቅ ሺሻ የተሻለ ተመራጭነት ያለውና በብዙሀኑ
የሕብረተሰብ ክፍል አገልግሎት ላይ የሚውል
የትምባሆ ምርት ነው፡፡
አንድ ጊዜ ሺሻን ማጨስ ሀያ አራት ወይም አንድ ፓኮ
ሲጃራ ከማጨስ ጋር የሚስተካከል ሲሆን የተለያዩ
ሳይንሳዊ የጥናት ውጤቶች ሺሻ ሲጃራ ማጨስ
ከሚያስከትለው የጤና ችግር ጋር ተመሳሳይ የሆነ
የጤና ችግር እንደሚያስከትል ይጠቁማሉ፡፡ በዚሁ
መሰረትም ሺሻን ማጨስ በዋናነት ሁለት ዋነኛ
የሰውታችንን ክፍሎች እነሱም ሳምባችንን እና
ልባችንን እንደሚጐዳ ተረጋግጧል፡፡ የሳምባ ካንሰር፣
የምግብ ማስተላለፊያ ቧንቧ ካንሰር፣ ቋሚ የሆነ
የሳምባ በሽታ፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች፣ የሳንባ
ምችና የአተነፋፈስ ችግሮች ሺሻ ማጨስ በጤና ላይ
ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሲጃራ
ማጨስ ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች በተጨማሪነት
ሺሻ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ያሉ ሲሆን የማጨሻ
ቱቦውን በጋራ መጠቀም ለተላላፊ በሽታዎች
ማጋለጡ እና በትምባሆ ላይ የሚጨመሩ አልኮል
ወይም አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን መጠቀም
በተጨማሪነት የሚጠቀሱ ሺሻ በማጨስ የሚመጡ
ጉዳቶች ናቸው፡፡ ሌላው ሺሻ መጠቀምን አሳሳቢ
የሚያደርገው ቀደም ሲል ሺሻ አገልግሎት ላይ
የሚውለው እንደ እነ ሕንድና ፓኪስታን ባሉ አገራት
በገጠር አካባቢ በሚኖሩ አዛውንቶች ሲሆን አሁን
አሁን ግን ሺሻ በተለያዩ አሕጉራትና አገራት በሰፊው
ጥቅም ላይ ውሎ ይገኛል፡፡ በርካታ ምግብ ቤቶችና
መዝናኛ ቦታዎችም ሺሻን ለደንበኞቻቸው ከሌሎች
አገልግሎት ጋር በተጨማሪነት የሚያቀርቡ በመሆኑ
የተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በርካታ
ወጣቶችም ሺሻ መጠቀምን እንደ መዝናኛ፣
ዘመናዊነትና አስደሳች ተግባር እየቆጠሩት
መጥተዋል፡፡ ሺሻ እንደ አርሰኒክ፣ ኮባልት፣ ክሮሚየም
እና ሊድ የመሳሰሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከባድና
አደገኛ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የሚይዝ የትምባሆ
ምርት ሲሆን ሺሻን መጠቀም ለአፍ እና የሽንት
ከረጢት ካንሰር የሚያጋልጥ ከመሆኑም በተጨማሪ
የወንዶችን የዘር ፍሬ ብዛትም እንደሚቀንስ በሺሻ ላይ
የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ሺሻ
በነፍሰጡሮች በእርግዝና ወቅት በእናቲቱ ሲጨስ
ካንሰር አምጪ ኬሚካሎች በቀላሉ ወደ ፅንሱ
ስለሚገቡ በፅንሱም ሆነ በእናትየዋ ላይ ጉዳት
ያደርሳል ከጉዳቶቹ መካከልም እናቶች ፅንስ መሸከም
ያለመቻል እና ለውርጃ የመጋለጥ እድላቸው የሠፋ
ሲሆን ፅንሱ ቢወለድ እንኳን ከሚጠበቀው በታች
የሆነ ክብደት ያለው ሕፃን ይሆናል የአተነፋፈስ
ስርዓቱም የተዛባ መሆኑና ድንገተኛ ሞት በሕፃኑ ላይ
ማስከተሉ በዋናነት የሚጠቀሱ ጉዳቶች ናቸው፡፡
ሺሻ በሁለተኛ አጫሾች /Passive Smokers/ ላይ
የሚያደርሰውን ጉዳት በተመለከተም ሺሻ ከሚያጨሱ
ሰዎች አካባቢ የሚገኙና የማያጨሱ ሰዎች ላይ
ከሚያደርሳቸው ጉዳቶች መካከል የዓይንና የአፍንጫ
ማቃጠልና ማስለቀስ፣ የጉሮሮ መከርከር፣ ከፍተኛ
የራስ ምታት፣ የሳንባ ካንሰር፣ ድንገተኛ የልብ ምት
ማቆም፣ የሳንባ ኢንፌክሽን፣ አስም፣ ብሮንካይትስ
አለርጂክ እና ካንሰር አምጪ ለሆኑ ኬሚካሎች
በእጥፍ መጋለጥ ይገኙበታል፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሺሻ
በብዛት የሚጨሰው በጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ
በመሆኑ አጫሾችን በተለይም ወጣቱን የሕብረተሰብ
ክፍል ለሺሻና ሌሎች ተያያዥ ሱሶች ተጋላጭ
የሚያደርግ ከመሆኑም በተጨማሪ ሺሻ
የሚጨስባቸውና ጫት የሚቃምባቸው ቤቶች
የወንጀል ፈጻሚዎች ዕቅድ መንደፊያና መሸሸጊያ ቦታ
ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡
ከኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ
አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከብሄራዊ
የትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ማህበር እንዲሁም
ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኙ መረጃዎች
እንደሚጠቁሙትም በአገራችን ሺሻ በማጨስና
በማስጨስ ተግባራት ላይ ያሉ ግለሰቦች ከሺሻ ምርት
ጋር ካናቢስ /Cannabis/ የተባለ ሀሺሽ በተባበሩት
መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አ በ1991 ዓ/ም በተፈረመ
ስምምነት መሰረት ቁጥጥር የሚደረግበትን ሕገ-
ወጥ የሆነ አደንዘዥ ዕፅ እና ሌሎች ባዕድ የሆኑ
ነገሮች ቀላቅለው ጥቅም ላይ ያውላሉ፡፡ የሀሺሽና
ሌሎች አደንዛዥ ዕጾች አጫሾችም የተለያዩ
ወንጀሎችን በመፈጸም የሕብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ
እንዲያደፈርሱ አልፎ ተርፎም በአገረቷ ውስጥ
ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት
እንዳይኖር የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡
ሺሻን መጠቀም፣ ማስጠቀም እና ከውጭ አገር
አስገብቶ ማከፋፈል ከሕግ አንጻር የሚያስከትለው
ኃላፊነት
የሺሻን ምንነትና የሚያደርሰውን ጉዳት ከተመለከትን
በኢትዮጵያ ሕግ ሺሻን ማጨስ ወይም ማስጨስ
የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት ስለመኖሩ
መመልከቱ አስፈላጊ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሺሻ ከትምባሆ
ምርቶች ውስጥ የሚመደብ ስለመሆኑ ብሄራዊ
የትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ማህበር ለጽ/ቤታችን
በጻፈው ደብዳቤ ያረጋገጠ ሲሆን አክሲዮን ማህበሩ
በአዋጅ ቁጥር 371/1985 አንቀጽ 1ዐ መሠረት
የትምባሆ ምርቶችን /ውጤቶችን/ ከውጭ
ለማስመጣት፣ ወደ ውጭ ለመላክ፣ ለመሸጥ፣
ለማዘጋጀትና በፋብሪካ ሰርተው ለማውጣት
ለሚፈልጉ ሰዎችና ድርጅቶች ፈቃድ የመስጠት
ስልጣን ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሠረት
ሺሻ ከትምባሆ ምርቶች የሚመደብ በመሆኑ አክሲዮን
ማህበሩ ሺሻን አስመልክቶ ከፍ ብለው የተጠቀሱትን
ተግባራት ማከናወን ለሚፈልጉ ግለሰቦች ፍቃድ
የመስጠት ስልጣን አለው፡፡ ብሔራዊ የትምባሆ
ድርጅት /ኢትዮጽያ/ አክሲዮን ማህበርም ይህንኑ
ስልጣኑን መሰረት አድርጐ ሺሻ ወደ አገር ውስጥ
ማስገባትና ማከፋፈል የሚፈልጉ ግለሰቦች
የሚስተናገዱበትን ሁኔታ የሚያብራራ እ.ኤ.አ
ከመስከረም 16 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ
አሁን እየተሰራበት የሚገኝ መመሪያ አውጥቷል፡፡
እስከአሁን ድረስም ሺሻን ለአንድ ጊዜ ብቻ ወደ
ኢትዮጵያ እንዲያስገቡ ከማህበሩ ፍቃድ የተሰጣቸው
afrah To***co እና Wambely Transport
Service የተባሉ ሁለት ድርጅቶች ብቻ መሆናቸውን
ከድርጅቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም ሺሻን
መጠቀም እና ከብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት በሚገኝ
ፍቃድ መሰረት ሺሻን ወደ አገር ውስጥ አስገብቶ
ማከፋፈል በሕግ ያልተከላከለ ይልቁንም ሺሻን
በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ማስገባትና ማከፋፈል
እንዲሁም መጠቀም እንደሚቻል ሕጉ በግልጽ
ያስቀምጣል፡፡ ሺሻ የሚያጨሱ፣ የሚያስጨሱ እና
ከድርጅቱ ፍቃድ አግኝተው ወደ አገር አስገብተው
የሚያከፋፍሉ ሰዎችም የሕግ ኃላፊነትና ተጠያቂነት
አይኖርባቸውም፡፡
በመሆኑም ሺሻ የሚያጨሱ እና ሺሻውን ከንግድ
ዓላማ ውጭ የሚያስጨሱ ግለሰቦች ሺሻውን
በማጨሳቸው ወይም በማስጨሳቸው ብቻ
የሚተላለፉት የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡
በሺሻ ላይ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት ከዚህ
ቀደም ሲታዩ የቆየበት ሁኔታ
ሺሻ በሚስጨሱ ግለሰቦች ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ
ኮሚሽን ሥር በሚገኙ የተለያዩ የፖሊስ
መምሪያዎችና ጣቢያዎች ተጣርተው የቀረቡ
የምርመራ መዛግብትን ሲያዩ የቆዩት የአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶችና በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤቶች የአቤቱታ ምርመራና የክስ
አቀራረብ ንዑስ የሥራ ሂደቶች ሲሆኑ
በተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሲቀርብባቸውም ሆነ
ሲቀጡ የነበረው አዋጅ ቁጥር 67/1989 አንቀጽ
21/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ያለንግድ
ፍቃድ የንግድ ሥራ ሠርታችኋል በሚል መሆኑን
ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 67/1989 ከ 3 ዓመት እስከ 5 ዓመት
በሚደርስ እስራት ያስቀጣ የነበረው ያለንግድ ፍቃድ
ንግድ ላይ የመሰማራት ተግባር በአዋጅ ቁጥር
686/2002 ከ 7 ዓመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ
እስራት እንዲያስቀጣ ተደርጎ ከተሸሻለ በኋላ ሺሻ
ሲያስጨሱ እና ያለንግድ ፍቃድ ንግድ ላይ የተሰማሩ
ግለሰቦች ላይ በፖሊስ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት
ከዚህ ቀደም ሲሰሩበት እንደነበረው በምርመራ
መዛግብቱ ላይ እንዲወስኑበት በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር የልደታ ፍትሕ ጽ/ቤት የአቤቱታ ምርመራና
የክስ አቀራረብ ንዑስ የሥራ ሂደት የምርመራ
መዛግብቱ ሲቀርቡላቸው ቀደም ሲል ተመሳሳይ
ጉዳዮችን በአዋጅ ቁጥር 67/1989 ሲሰሩ የነበረ
መሆኑን ሆኖም ይሕ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር
686/2002 የተሻሻለ መሆኑንና በአዲሱ አዋጅ
ስልጣኑ የእነሱ አለመሆኑን ገልፀው ሺሻ ያስጨሳሉ
የተባሉ ግለሰቦች ላይ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት
በፍትሕ ሚኒስቴር የልደታ ፍትሕ ጽ/ቤት በኩል
እንዲያስወስን ለአብነት አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ
በመግለፅ የምርመራ መዛግብቱን መልሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች እና የከተማ ነክ
ፍትሕ ጽ/ቤቶች የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው ገንዘብ
እያስከፈሉ ሺሻ ሲያስጨሱ የነበሩ ሠዎችን
አስመለክቶ የተጣሩ የምርመራ መዛግብትን በአዋጅ
ቁጥር 67/1989 አንቀጽ 21/1/ መሠረት ሲከሱ እና
ጉዳዩን ሲመለከቱ የቆዩበት ሥልጣን በራሱ አጠያያቂ
ነው፡፡ ይኸውም በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ
28 (1) ላይ እንደተመለከተው የከተማው የዐቃቤ
ሕግ መስሪያ ቤት በከተማው ፍርድ ቤቶች ሥልጣን
ሥር ማለትም በአዋጁ አንቀጽ 41 (2) ሥር
በተመለከቱት የወንጀል ጉዳዮች እነዚህም በቻርተሩ
አንቀጽ 52 በተመለከቱ የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ
በሚነሱ ወንጀሎች፣ በደንብ መተላለፍ ጉዳዮች
(በወንጀል ሕጉ ከአንቀጽ 778 እስከ አንቀጽ 865
የተመለከቱት ላይ)፣ በፌዴራል ወንጀሎች ላይ
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ
የጊዜ ቀጠሮ እና የዋስትና ጉዳዮች፣ በከተማው
አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የሚጣሉ የደንብ
መተላለፍ ጉዳዮችን የማስፈፀም ጉዳዮች) ላይ ብቻ
ሊሰሩ እንደሚገባ በሕጉ በግልፅ ተመልክቶ ሳለ
በእነዚህ ዝርዝር ውስጥ በማይካተቱ በሺሻ ማስጨስ
ተግባር ላይ ተጣርተው የቀረቡ፣ በአዋጅ ቁጥር
67/1989 የሚሸፈኑ፣ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 46 (1)
መሠረት ከ 3 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት
የሚያስቀጡ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና
በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ሊታዩ የሚገባቸውን የምርመራ
መዛግብት ሥልጣንና ተግባራቶቻቸውን ለመወሰን
በወጣውን ሕግ ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጭ
በመውጣት ሲሰሩ መቆየታቸውን መመልከት ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ
ፍትሕ ጽ/ቤት የአቤቱታ ምርመራና የክስ አቀራረብ
ንዑስ የሥራ ሂደት በሺሻ ላይ የተጣሩ የምርመራ
መዛግብት ላይ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን
የንግድ ፍቃድ ሳይኖራችሁ በንግድ ላይ
ተሰማርታችኋል በሚል ከ 3 ዓመት እስከ 5 ዓመት
በሚደርስ እስራት በሚያስቀጣው በአዋጅ ቁጥር
67/1989 አንቀጽ 46 (1) መሠረት ሲከስና
ሲያስቀጣ የነበረበት አግባብ እንዲሁም የአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር የልደታ ምድብ ችሎት እነዚሁኑ
ጉዳዮች ተቀብሎ ሲመረምርና ሲወስን የነበረበት
አካሄድ ስልጣንና ተግባራቶቻቸውን
የሚወስነውን አዋጅ ቁጥር 361/1995፣ ለፌዴራል
ፍርድ ቤቶችና ለፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ሥልጣን
የሚሰጡትን አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አዋጅ
ቁጥር 471/1998 (በአዋጅ ቁጥር 691/2003
እንደተሻሻለው) ላይ ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች
የወንጀል ዳኝነት ሥልጣን እንዲሁም የፍትሕ
ሚኒስቴርን ሥልጣን የተመለከቱትን ድንጋጌዎች
የጣሰ፣ የትኛውንም ሕግ መሠረት ያላደረገ እና
ከሥልጣናቸው በላይ ሲሰሩ የነበረ መሆን መረዳት
ይቻላል፡፡
ሺሻ የሚያጨሱና የሚያስጨሱ ሰዎች እንዲሁም
የማስጨሻ ዕቃዎች የሚያዙበት የማስጨሻ ቤቶችም
የሚዘጉበት የሕግ አግባብ
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆኑትንና ሌሎች ጉዳዮችን
ጨምሮ ፖሊስ ሺሻ በማጨስና በማስጨስ ተግባራት
ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንና የማስጨሻ ዕቃዎች
በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ሲያጣራ ቆይቷል፡፡
ሺሻ ማጨስም ሆነ ማስጨስ በየትኛውም ሕግ
ያልተከለከሉ ተግባራት እንደመሆናቸው ያጨሱም ሆነ
ያስጨሱ ሰዎች እንዲሁም የማስጨሻ ዕቃዎች
ግለሰቦቹ በማጨሳቸው ወይም በማስጨሳቸው ብቻ
ሊያዙ የሚችሉበት የሕግ አግባብ የለም፡፡ ሆኖም ሺሻ
የሚያጨሱ ወይም የሚያስጨሱ ሰዎች ሺሻ
ከማጨሳቸው ወይም ከማስጨሳቸው ጐን ለጐን
የሚተላለፏቸው ሌሎች ሕጉች እንዲሁም
የሚፈጽሟቸው ሌሎች ወንጀሎች ካሉ የወንጀለኛ
መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ በተቀመጠው ሥነ-
ሥርዓት መሰረት ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ቅድመ ሁኔታ
ውጭ ግን ፖሊስ ሺሻ አጫሾችንም ሆነ አስጫሾችን
እንዲሁም የሺሻ ማጨሻ ዕቃዎችን መያዝ
የሚችልበት የሕግ መሰረት የለውም፡፡ የክፍለ ከተማ
ወይም የቀበሌ አስተዳደር ሠራተኞችም ሺሻ
አጫሾችን፣ አስጫሾችና የማስጨሻ ዕቃዎችን ይዘው
ለፖሊስ የሚያስረክቡበት እንዲሁም ሺሻ
ሲጨስባቸው ነበር የሚባሉ ቤቶችን ሺሻ
ስለሚጨስባቸው ብቻ የሚያሽጉበት የሕግ መሠረት
የላቸውም፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 መሠረት
የፍ/ቤት የብርበራ ማዘዣ በማውጣት ወይም በወ/
መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32 (2) (ለ) መሠረት ከሺሻ
ማጨስ ወይም ማስጨስ ጋር በተያያዘ ተፈጽሟል
የተባለው ወንጀል ከ3 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ
እንደሚችል በማረጋገጥ ወንጀሉ የተፈጸመበት ነገር
ማስጨሻ ቤት ውስጥ ይገኛል የሚል ጥርጣሬ
ሲኖርና ፖሊስ የብርበራ ማዘዣ እስኪቀበል ድረስ
ወንጀል ተሰራበት የተባለው ነገር ካለበት ቦታ
ይወስዳል ተብሎ በበቂ ምክንያት የታመነ ሲሆን ብቻ
ፖሊስ የሺሻ ማስጨሻ ቤቶችን ለመበርበርና
እንደአግባብነቱ የማስጨሻ ዕቃዎችን ለመያዝ
ይችላል፡፡ የሺሻ አጫሾችንም ሆነ አስጫሾችን ሺሻ
ከማጨስ ወይም ማስጨስ ጋር በተያያዘ ሌላ ወንጀል
ፈጽማችኋል በሚል ለመያዝም ፖሊስ በወ/መ/ሥ/
ሥ/ሕ/ቁ. 53 መሰረት ከፍ/ቤት የመያዣ ትዕዛዝ
ማውጣት ወይም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5ዐ
መሰረት ሺሻ ከማጨስ ወይም ማስጨስ ጋር በተያያዘ
ከ3 ወራት ቀላል እስራት በማያንስ እስራት
የሚያስቀጣ ሌላ ወንጀል እጅ ከፍንጅ ሲፈጽሙ
ማግኘት አለበት፡፡
ከእነዚህ በሕጉ ከተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ውጭ
ግን ፖሊስ ሺሻ አጫሾችንም ሆነ አስጫሾችን
እንዲሁም ማጨሻ ዕቃዎችን መያዝ የሚችልበት
የሕግ መሠረት የለውም፡፡ የመያዣ ወይም
የመበርበሪያ ትዕዛዝ የሚሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ
ፍ/ቤቶችም ትዕዛዙን ከመስጠታቸው በፊት ከፍ
ብለው የተጠቀሰውትን ነጥቦች ከግምት ማስገባት
ይኖርባቸዋል፡፡
ሺሻ ማስጨስን አስመልክቶ የተጣሩና በፖሊስ
ጣቢያዎች የሚገኙ የምርመራ መዛግብት ሁኔታ
በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሥር በሚገኙ
የአብነት አከባቢ እና የልደታ (ባልቻ) አከባቢ ፖሊስ
ጣቢያዎች ብቻ ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ሺሻ ያስጨሳሉ
የተባሉ ግለሰቦች ላይ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት
ያሉ ሲሆን ከምርመራ መዛግብቱ መረዳት
እንደሚቻለው ሺሻ የሚያስጨሱ ግለሰቦች አጫሾችን
አንድ ጊዜ ለማጨስ በአማካይ ከአምስት እስከ
ስምንት ብር ያስከፍላሉ፡፡ ይሕ አድራጎትም ሺሻ
ማስጨስን አገልግሎት ከሚሰጥባቸው የንግድ
ተግባራት ውስጥ ያስመድበዋል፡፡ አንዳንዶቹ ሺሻ
አስጫሳችኋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 27 (2)
መሠረት ለፖሊስ ቃላቸውን ሲሰጡ ሺሻ
እንደማያስጨሱ ገልፀው ጫት የሚያስቅሙ መሆኑን
ብቻ ያስረዳሉ፡፡ አያይዘውም ከቀበሌ (ወረዳ)
የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተሰጣቸውን
ጫት በችርቻሮ ለመሸጥ የሚያስችል የንግድ ፍቃድ
ከምርመራ መዝገቡ ጋር አያይዘዋል፡፡ ተጠርጥረው
የቀረቡት ግለሰቦች ሺሻ እያስከፈሉ አስጭሰዋል
ወይስ አላስጨሱም የሚለው የሚወሰነው
በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ ከቀረቡት ማስረጃዎች
አንፃር ሆኖ ጫት የማስቃም አገልግሎት በራሱ በሕግ
ዕውቅና የተሰጠውና ማስቃም ለሚፈልጉ ሰዎች
በመንግስት በኩል የንግድ ፍቃድ የሚሰጥ ስለመሆኑ
ማጣራቱ አስፈላጊ ነው፡፡
በንግድ ሕጉ አንቀጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት ተግባራት
መካከል አንዱን በማከናወን ዕቃ በመሸጥ ወይም
አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ በመሰማራት
ተግባሩን ሙያው አድርጎ ተሰማርቶ ጥቅም ወይም
ገቢ ለማግኘት በማሰብ የሚሰራ ሰው ነጋዴ ሊባል
እንሚችል ተመልክቷል፡፡ በአንቀጽ 5 ሥር ከተዘረዘሩት
ተግባራት ውጭ ያሉትን ሌሎች የንግድ ተግባራት
በሙያነት ለትርፍ መሥራት በነጋዴነት ያስመድባል
ወይስ አያስመድብም የሚለው ጥያቄ ሲነሳ የነበረና
የሚነሳ ጥያቄ ቢሆንም በአሰራር ደረጃ በአንቀጽ 5
ከተዘረዘሩት ተግባራት ውጭ ላሉ ሌሎች የንግድ
ተግባራት በመንግስት በኩል ፍቃድ እየተሰጠ
ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በአንቀጽ 5 ሥር
ከተመለከቱት ተግባራት ውጭ ያሉ ሌሎች የንግድ
ተግባራትን በሙያነት ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ፍቃድ
ወስዶ በተግባራቱ ላይ መሰማራት ይቻላል፡፡ ሆኖም
እንደ ሺሻ ማስጨስ፣ ጫት ማስቃም፣ ቁማር
ማጫወት ላሉ የንግድ ተግባራት ተግባራቱ በአንቀጽ 5
ሥር ከተዘረዘሩት ውጭ ቢሆኑም በመንግስት በኩል
በእነዚህ የንግድ ተግባራት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ
ሠዎች የንግድ ፍቃድ አሰጥም፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ
ሥር ከሚገኙት የወረዳ 1 እና የወረዳ 4 የንግድና
ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤቶች ለመረዳት እንደተቻለው
ሺሻ ለሚያስጨሱ እና ጫት ለማስቃም ለሚፈልጉ
ግለሰቦች በመንግስት ደረጃ የንግድ ፍቃድ
አይሰጥም፡፡ ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም
ተግባራት ሕብረተሰቡን በተለይም ወጣቱን
የሕብረተሰብ ክፍል ለሱስ ተገዥ በመሆን አምራች
እንዳይሆን እና ምግባረ ብልሹነት እንዲስፋፋ
አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ በመሆኑ በመንግስት
ዕውቅና ያልተሰጣቸው እና የንግድ ፍቃድ
የማይሰጥባቸው የንግድ ተግባራት ናቸው፡፡
በመሆኑም ሺሻ የማስጨስና ጫት የማስቃም
ተግባራት በመንግስትና በሕግ ዕውቅና ያልተሰጣቸው
ተግባራት ናቸው፡፡
በንግድ ሕጉ አንቀጽ 24 (1) ላይ በሕግ የተከለከሉ
የንግድ ተግባራት ላይ መሰማራት በወንጀል
ሊያስጠይቅ እንደሚችል በግልፅ የተመለከተ ቢሆንም
ሺሻ የማስጨስና ጫት የማስቃም ተግባራት ላይ
መሰማራት እንደማይቻል ወይም ስለመከልከሉ
የሚደነግግ ሕግ የለም፡፡ ሆኖም አንድ የንግድ ተግባር
ላይ መሰማራት እንደማይቻል ወይም የተከለከለ
ስለመሆኑ የሚደነግግ ሕግ ስለሌለ እንደተፈቀደ
ተቆጥሮ መሰማራት ይቻላል ሊባል ቢችልም የወረዳ
(የቀበሌ) የንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤቶች ፍቃድ
ለሚፈልጉ ሠዎች የንግድ ፍቃድ የሚሰጡት
በየትኛዎች የንግድ ተግባራት ላይ እንደሆነ
የሚያመላክት ዝርዝር የንግድ ተግባራቶችን የያዘ
ሠነድ ያለ ሲሆን አመልካች ልሰማራበት ብሎ
የጠየቀው የንግድ ተግባር በዚህ ሰነድ ውስጥ
ከተመለከቱት ውስጥ ካለ ብቻ ፍቃድ ይሰጠዋል
ተግባሩ ከዝርዝሩ ውስጥ ከሌለ ግን የንግድ ፍቃድ
አይሰጠውም በንግድ ሥራ ላይም መሰማራት
አይችልም ማለት ነው፡፡
ከዚህ የአሰራር ሁኔታ አንፃር ሺሻ የማስጨስና ጫት
የማስቃም ተግባራትን ለመመለከት ያህል ሁለቱ
ተግባራት ላይ መሰማራት እንደማይቻል የሚገልፅ
ሕግ የሌለ ቢሆንም በመንግስት የንግድ ፍቃድ ሰጭ
አካላት አሰራር መሠረት ፍቃድ የማይሰጥባቸው
የንግድ ተግባራት ሲሆኑ በእነዚህ ተግባራት ላይ
መሰማራት እፈልጋለሁ የሚል ግለሰብ ካለ ለንግድ
ፍቃድ ሰጭ አካላት በሕጉ መሠረት የንግድ ፍቃድ
እዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ፍቃድ ሊሰጥበት የማይችል
የንግድ ተግባር መሆኑ ሲገለፅለት መሰማራት
አይኖርበትም፡፡ ሆኖም ከፍቃድ ሰጭ አካል በሺሻ
ማስጨስ ወይም በጫት ማስቃም የንግድ ተግባራት
ላይ መሰማራት እንደማይቻል ተገልፆለት ወይም
ከመጀመሪያው ፍቃድ ለማውጣት ጥያቄ ሳያቀርብ
በእነዚህ ተግባራት ላይ የተሰማራ ነጋዴ የፀና የንግድ
ፍቃድ ሳይኖረው በሕገ ወጥ መንገድ በንግድ ላይ
እንደተሰማራ ይቆጠራል፡፡
ዐቃቤ ሕግ ሺሻ በሚያጨሱ እና በሚያስጨሱ
ግለሰቦች ላይ የተጣሩ የምርመራ መዛግብት ላይ
የሕግ አስተያየት እና ውሳኔ የሚሰጥበት እንዲሁም
ምርመራ እንዲጣራ የሚያዝበት አግባብ
ሺሻ ማጨስም ሆነ ማስጨስ በሕግ ያልተከለከሉ
ይልቁንም በሕግ ድጋፍ ያላቸው ተግባራት
በመሆናቸው ሺሻ አስጭሳችኋል ወይም አጭሳችኋል
በሚል የተከሰሱና ምርመራ የተጣራባቸው ግለሰቦች
ካሉ በማጨሳቸው ወይም በማስጨሳቸው ብቻ
የፈጸሙት ወንጀልና የተላለፉት ሕግ ባለመኖሩ
በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23 /1/ እና /2/ መሠረት ሕገ
ወጥነቱና አስቀጪነቱ በሕግ ያልተደነገገ እንዲሁም
ወንጀልን ከሚያቋቁሙ ሕጋዊ፣ ግዙፋዊ እና ሞራላዊ
ፍሬ ነገሮች ሕጋዊ ፍሬ ነገር ያልተሟላ በመሆኑ
በዐቃቤ ሕግ በኩል የክስ አያስቀርብም ውሳኔ
ተሰጥቶ የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎች ተይዘው ከሆነ
ለባለንብረቱ እንዲመለሱ መደረግ ይኖርበታል፡፡
ሆኖም ሺሻ ከማጨስ ወይም ከማስጨስ ተግባራት
ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የተለያዩ ወንጀሎች ያሉ
በመሆኑ በፖሊስ በኩል ምርመራ ከመጣራቱ በፊት
እንዲሁም በዐቃቤ ሕግ በኩል በምርመራና በሕጋዊ
አስተያየትና ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት ተያያዥ
ወንጀሎች የተፈፀሙ ስለመሆናቸው በጥንቃቄ
ሊፈተሹ ይገባል፡፡ ሺሻ ከማጨስ ወይም ማስጨስ
ተግባራት ጋር በተያያዘ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች
መካከልም አደንዛዥ ዕጾችን ማዘዋወር ወይም
መጠቀም፣ የንግድ ፍቃድ ሳያወጡ ሺሻ እያስጨሱ
ገቢ በማግኘት በንግድ ስራ ላይ መሰማራት፣ ሺሻንና
ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን ያለፍቃድ ከውጭ
ማስመጣት ወይም ለሽያጭ ማቅረብ ይገኙበታል፡፡
እነዚህ ከሺሻ ማጨስና ማስጨስ ጋር በተያያዘ
የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንዴት እንደሚፈፀሙ፣
ወንጀሎቹ ከተፈፀሙ እና ምርመራ ከተጣራ በኃላ
በየትኞቹ ሕጎች ጉዳዮቹ እንደሚሸፈኑ ማየቱ አስፈላጊ
በመሆኑ እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡
ሀ. አደንዛዥ ዕጾችን ማዘዋወር ወይም መጠቀም
ከፌዴራል ፖሊስ እና ከኢትዮጵያ የምግብ፣
የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር
ባለስልጣን የተገኙት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሺሻ ማስጨሻ
ቤቶች ውስጥ ሺሻ ከተለያዩ አደንዛዥ ዕጾች
በተለይም እንደ ካናቢስ ካሉ አደንዛዥ ዕጾች ጋር
ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን አደንዛዥ
ዕጾችን ልዩ ፍቃድ ሳይኖር መግዛት፣ በሽያጭ
ማቅረብ፣ ማሰራጨት፣ ማዘዋወር፣ ይዞ መገኘት፣
መጠቀም፣ መኖሪያ ቤትን ወይም ይዞታን ለአደንዛዥ
ዕፆች መሸጫነት መስጠት፣ ማከራየት ወይም
መፍቀድ በራሱ አደንዛዥ ዕፁን ለተጠቃሚዎች
ባቀረቡት፣ በተጠቃሚዎች፣ ይዘው በተገኙና
ቤታቸውን ወይም ይዞታቸውን አደንዛዥ ዕፁን
ለሚሸጡ ሰዎች በፈቀዱ፣ ባከራዩና በሰጡ ሰዎች
ላይ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 525 የተለያዩ ንዑስ
ቁጥሮች ላይ በተመለተው መሰረት ተጠያቂ እንዲሆኑ
ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡
በማስረጃ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይም ከሺሻ ማስጨሻ
ዕቃው አናት ላይ ከሚገኘው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ
ከሚገኘው የሺሻ ትምባሆ ላይ አደንዛዥ ዕፅ
ስለመኖሩ ወይም ከሺሻ ስለመቀላቀሉ ከኢትዮጵያ
የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና
ቁጥጥር ባለስልጣን አስመርምሮ በሰነድ ማስረጃ
ማረጋገጡ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ የተቀረው በበቂ
ሁኔታ በሚያስረዱ የሰው ማስረጃዎች ሊረጋገጥ
ይችላል፡፡
ለ. የንግድ ፍቃድ ሳያወጡ ሺሻን በማስጨስ ገቢ
እያገኙ በንግድ ስራ ላይ መሰማራት
ሺሻን ከማስጨሻው ዕቃው ጋር ለአጫሾች አቅርቦ
ላጨሱበት ክፍያ እንዲከፍሉ ማድረግ ሺሻ ማስጨስን
አገልግሎት ከሚሰጥባቸው የንግድ ዘርፎች ውስጥ
ያስመድበዋል፡፡ አንድ ሰውም ከአጫሾች /
ከተጠቃሚዎች/ በተጠቀሙት የሺሻ ማጨስ መጠን
ልክ ገንዘብ እየተቀበለ ለማስጨስ ከፈለገ ስልጣን
ካለውና ከሚመለከተው አካል የፀና የንግድ ፍቃድ
ማውጣት ይኖርበታል፡፡ ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር
67/1989 አንቀጽ 21/1/ ላይ እንዲሁም በአሁኑ
ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 686/2ዐዐ2 አንቀጽ 31/1/ ላይ
እንደተመለከተው ማንኛውም ሰው የፀና የንግድ
ፍቃድ ሳይኖረው የንግድ ስራ መስራት አይችልም፡፡
በመሆኑም ሺሻ የማስጨስ የንግድ ስራ ላይ
ለመሰማራት የሚያስችል የፀና የንግድ ፍቃድ ያላቸው
ስለመሆኑ ከአስጫሾች እና ስልጣን ካለው
ከሚመለከተው አካል ማጣራቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ሺሻ
አስጫሽ ግለሰቦችም እያስጨሱ ገንዘብ የሚቀበሉ
ስለመሆኑ ለማስረዳት አጫሾችን በማስረጃነት
መጠቀሙ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡
በመሆኑም ሺሻ አስጫሽ ግለቦች ሺሻ እያስጨሱ
ገንዘብ ስለመቀበላቸው እንዲሁም ይህንን
ለማከናወን የሚያስችል የፀና የንግድ ፍቃድ
የሌላቸው ስለመሆኑ ማስረዳት ከተቻለ አስጫሾች
በአዋጅ ቁጥር 686/2ዐዐ2 አንቀጽ 6ዐ/1/ መሰረት
የወንጀል ክስ ሊቀርብባቸውና ፍ/ቤት ሲወስንም
የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎች ሊወረሱ፤ በአንቀጽ 31/2/
መሰረት አግባብ ባለው ባለስልጣን የንግድ ድርጅቱ
ሊዘጋባቸው እንዲሁም በሌላ የንግድ ሥራ ላይ
ለመሰማራት የሚያስችል የንግድ ፍቃድ ኖሯቸው ሺሻ
በማስጨስ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ላይ
በአንቀጽ 39/1/ለ መሰረት የንግድ ፍቃዳቸው
እንዲሰረዝ ማድረግ ይገባል፡፡
ሐ. ከፍቃድ ውጭ መሥራት
አንድን የንግድ ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ
ፍቃድ የተሰጠው ሠው ለመሰማራትና ለመስራት
የሚችለው የተፈቀደለትን የንግድ ሥራ ብቻ ሲሆን
ከዚህ ከተፈቀደለት የንግድ ሥራ ውጭ በሌሎች
ተያያዥ በሆኑና ባልተፈቀዱለት የንግድ ተግባራት ላይ
መሰማራት የለበትም፡፡ ጫት በችርቻሮ ለመሸጥ ብቻ
የሚያስችል የንግድ ፍቃድ የተሰጠው ሠው ከዚህ
ፍቃዱ በመውጣት በችርቻሮ በሚሸጥበት የንግድ
ቤት ውስጥ ጫት ሲያስቅም ወይም ሺሻ ሲያስጨስ
ቢገኝ ፈቃዱን ከተሰጠበት ዓላማ ውጭ ሲገለገልበት
ወይም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ሥራ ሲሠራበት የተገኘ
በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 39 (1)
(ለ) መሠረት ፍቃዱ በሚመለከተው አካል በኩል
እንዲሰረዝበት ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀል
ሕጉ አንቀጽ 433 መሠረት ተጠያቂ እንዲሆነ ማድረጉ
ተገቢ ነው፡፡
መ. ሺሻንና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን ያለ ፍቃድ
ከውጭ ማስመጣት ወይም ለሽያጭ ማቅረብ
ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/ አክሲዮን
ማህበር ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶችን ለመግዛት፣
ለመቀመም በፋብሪካ ሰርቶ ለማውጣት፣ ለመሸጥ
ወደ አገር ለማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ ለመላክ
ብቸኛ ልዩ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር
37/1985 አንቀጽ 9 ላይ ተመልክቷል፡፡ ሆኖም ይህ
የአክሲዮን ማሕበሩ ብቸኛ ሥልጣን (exclusive
power) በአንቀጽ 1ዐ ላይ እንደተመለከተው ድርጅቱ
ትምባሆና የትምባሆ ምርቶችን ከውጭ ማስመጣት
እና ለሽያጭ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን
ለሚያከናውኑ አካላት ፍቃድ ሊሰጥ እንደሚችልም
ተመልክቷል፡፡ አዋጁ በአንቀጽ 11 ላይም እነዚህን
ተግባራት ያለ ፍቃድ ማከናወን እንደማይቻል
ያስረዳል፡፡ ሺሻም የትምባሆ ምርት /ውጤት/
እንደመሆኑ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ሺሻን ወደ
አገር ውስጥ ለማስገባት እና ለሽያጭ ማቅረብ
ከፈለጉ ከብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት አክሲዮን
ማህበር በአዋጅ ቁጥር 37/1985 አንቀጽ 1ዐ እና
ድርጅቱ ሺሻ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚፈልጉ
ድርጅቶችና ግለቦች የሚስተናገዱበትን ሁኔታ
ለማመቻቸት ባወጣው መመሪያ አንቀጽ 2 መሰረት
ፍቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም የሺሻ
ምርት ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/
አክሲዮን ማህበር ፍቃድ ካልሰጠ በስተቀር ወደ አገር
እንዳይገባ ወይም ከአገር እነዳይወጣ ወይም
እንዳይተላለፍ ገደብ የተደረገበት ዕቃ ነው፡፡
በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 (1) (2) እና
(3) መሠረትም በሕግ መሠረት ሥልጣን ከተሰጠው
አካል ፍቃድ ካልሰጠ በስተቀር ወደ አገር እንዳይገባ
ወይም ከአገር እንዳይወጣ ወይም እንዳይተላለፍ
ገደብ የተደረገበት ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ማስገባት
ወይም ከጉምሩክ ክልል ማስወጣት እንዲሁም በሕገ
ወጥ መንገድ የተገኙ ዕቃዎች መሆናቸውን እያወቁ
ወይም ማወቅ ሲገባ ይህንኑ ዕቃ ወደ አገር
ማስገባት፣ ማስወጣት፣ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት፣
ለሽያጭ ማቅረብ እና መግዛት ወንጀል መሆኑ
ተደንግጎ ከባድ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ ሺሻም ያለ
ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/ አክሲዮን
ማህበር ፍቃድ ወደ አገር እንዳይገባና አገልግሎት
ላይ እንዳይውል እንዲሁም እንዳይዘዋወር ገደብ
የተጣለበት ዕቃ ነው፡፡ በመሆኑም ያለ ትምባሆ
ድርጅት ፍቃድ የሺሻ ምርት ወደ አገር ማስገባት፣
ማስወጣት፣ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት፣ ለሽያጭ ማቅረብ
እና መግዛት የሚያስጠይቅ በመሆኑ በብርበራ ወቅት
የሺሻ ምርት የተገኘባቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች
ካሉ የሺሻ ምርቱን ወደ አገር ለማስገባት ወይም
ለማዘዋወር የሚያስችል ፍቃድ እንዳላቸው
ለማስረዳት ወይም ፍቃዳቸውን ለማሳየት ካልቻሉ
በጉምሩክ አዋጁ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
የሺሻ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎች ገደብ
የተደረገባቸውን ዕቃዎች ያለፍቃድ ወደ አገር
አስገብተው የሚያከማቹ፣ የሚያዘዋውሩ እንዲሁም
ሌሎች በአዋጅ ቁጥር 622/2001 ላይ የተመለከቱን
ድንጋጌዎች የሚተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ
ምርመራ የማጣራት እና ለሕግ አቅርቦ ተገቢውን
ቅጣት እንዲያገኙ የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው
ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የጉምሩክ ሹም እና
ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡ በመሆኑም ሺሻን አስመልክቶ
ከጉምሩክ ጋር ተያይዘው የሚፈፀሙ ወንጀሎችን
በመመርመርና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ አቅርቦ
ከማስቀጣት አኳያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ፖሊስ ኮሚሺንም ሆነ የፍትሕ ሚኒስቴር ሥልጣን
አይደለም፡፡ ሆኖም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽ ፖሊስ
እና የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ከሺሻ ጋር በተያያዘ
በሥልጣናቸው ሥር የሚወድቁ ጉዳዮችን
በሚመረምሩበት ወይም በሚመለከቱበት ወቅት
ከጉምሩክ ጋር የተያያዘ ወንጀል መፈፀሙን ከተረዱ
መረጃ ሳይባክን ይህንኑ ለገቢዎችና ጉምሩክ
ባለሥልጣን የጉምሩክ ሹምና ዐቃቤ ሕግ በማሳወቅ
እንዲከታተሉት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ
ረገድም ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር
በትብብር መስራት ያስፈልጋል፡፡
ከአዋጅ ቁጥር 622/2001 በስተቀር የተቀሩት ሕጎች
ማለትም የአዋጅ ቁጥር 37/1985 አንቀጽ 11 እና
13 እና በብሐየራዊ ትምባሆ ድርጅት የወጣው
መመሪያ ሲጣሱ ምርመራ የማካሄድና ወንጀል
ፈፃሚዎችን ተጠያቂ የማድረግ ኃላፊነት የአዲስ አበባ
ፖሊስ ኮሚሽ ፖሊስ እና የፍትህ ሚኒስቴር በመሆኑ
ሺሻን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ
ማስገባትን በተመለከተ ከገቢዎችና ጉምሩክ
ባለሥልን የጉምሩክ ሹምና ዐቃቤ ሕግ ጋር
የሥልጣን መደራረብ ይኖራል፡፡ ሆኖም የሺሻ ምርትን
ያለፍቃድ ወደ አገር ውስጥ የማስገባት፣ የማከማቸት፣
የማጓጓዝ፣ ለሽያጭ የማቅረብና የመግዛት ወንጀሎች
አፈፃፀም ባህሪ በዋናነት ከጉምሩክ አሠራር ጋር
የተያያዘ በመሆኑ ይህንኑ በማረጋገጥ በገቢዎችና
ጉምሩክ ባለሥልጣን እንዲታይ ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡
በአጠቃላይ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በመመሪያው
መሰረት ከትምባሆ ድርጅት ፍቃድ ሳይኖራቸው የሺሻ
ምርት ከውጭ አስመጥተው ለሽያጭ ያቀረቡት፣
ያከማቹት ወይም ያዘዋወሩት መሆኑን ማስረዳት
ከተቻለ የመመሪያውን አንቀጽ 2፣ የአዋጅ ቁጥር
37/1985 አንቀጽ 11 እና 13 እንዲሁም አዋጅ
ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 (1) (2) ወይም (3)
መሠረት በማድረግ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ ሊቀርብባቸው ይገባል፡፡
ማጠቃለያ
ሺሻ መጠቀም በጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት
ባሻገር ለተለያዩ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና
ፖለቲካዊ ችግሮች መንስኤ መሆኑ በተለያዩ ጥናቶች
ተረጋግጧል፡፡ ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ ሺሻ
ማጨስንም ሆነ ማስጨስን የሚከለክል ሕግ የሌለ
ይልቁንም ሺሻ አገልግሎት ላይ የሚውልበት ሁኔታ
ላይ ዝርዝር ሕግ ያለ በመሆኑ ሺሻ ማጨስም ሆነ
ማስጨስ የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ሺሻ
ሲያጨሱም ሆነ ሲያስጨሱ የሚገኙ ሠዎችን
እንዲሁም የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎችን ሺሻ
በማጨሳቸው ወይም ማስጨሳቸው ብቻ የሚያዙበት
የሕግ መሠረት የለም፡፡
ሆኖም አደንዛዥ ዕፅ ይዞ መገኘት እና መጠቀም፣ ያለ
ፍቃድ ንግድ መነገድ እና ገደብ የተጣለበትን ዕቃ
(ሺሻ) ያለፍቃድ ወደ አገር ማስገባት ከሺሻ ማጨስ
እና ማስጨስ ተግባራት ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ
ወንጀሎች በመሆናቸው ወንጀሎቹ መፈፀማቸውን
በመለየት ፈፃሚዎችን ለሕግ ማቅረቡ አስፈላጊ ነው፡፡
የመፍትሔ ሃሳቦች
ሺሻ ከማጨስና ማስጨስ ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙትን
ወንጀሎች ከመለየትና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ

Address

Butajira
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የህግ አማካሪ legal consultant posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share