21/09/2025
በዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ፣ እና ቨርጂኒያ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ነዎት? እንግዲያውስ ይህ ነጻ መድረክ እንዳያመልጦ!
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ለአሥርት አመታት ወሳኝ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንዲሁም ለሀገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከተ የቆየ ቢሆንም መሠረታዊ የሕግ ጉዳዮችን ካለመረዳት እና በቂ የሕግ ጥበቃ ባላማግኘቱ የተነሳ በተለያዩ አካላት ለሚፈፀም የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊት እየተጋለጠ በሰው ሃገር ያፈራውን ጥሪት በቀላሉ ሲዘረፍ ይስተዋላል፡፡ ይህንን ለመቅርፍ የሚያስችል ነጻ የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የኢትዮ ሌጋል ሺልድ የጥብቅና ድርጅት መስራች ጠበቆች ከኢትዮ አሜሪካን የንግድ ም/ቤት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶሎታል፡፡
የፊታችን ሀሙስ ሴፕቴምበር 25 ከ 5:00 PM -9:00 PM አድራሻ 1 Veterans Place Silver Spring MD
ዛሬውኑ ቦታ ይያዙ!
ያለ ክፍያ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ
https://www.eventbrite.com/e/protect-ethiopian-diaspora-through-legal-awareness-tickets-1723320721669?utm-campaign=social&utm-content=attendeeshare&utm-medium=discovery&utm-term=listing&utm-source=cp&aff=ebdsshcopyurl
ይህ አስፈላጊ የህግ ግንዛቤ ፕሮግራም እራስዎን፣ ቤተሰብዎን እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን ለመጠበቅ በሚያስችል እውቀት ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ነው።
ማን መታደም ይችላል?
ይህ ዝግጅት ለሁሉም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት፣ በንብረት ግዥ ላይ ለሚሳተፉ ወይም የህግ ጉዳዮች ላሏቸው ሰዎች ጠቃሚ ነው።
ምን ይማራሉ?
የኢትዮ ሌጋል ሺልድ መስራች እና ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች ተናጋሪዎች ሲሆኑ፣ በወሳኝ የህግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ይሰጣሉ።
የፕሮግራሙ ይዘት፡-
በቅርቡ የጸደቀውን የሪል እስቴት ሕግን እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ችግሮችን፡ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ገበያን ውስብስብ ሁኔታ ይዳስሳል። ባለሙያዎቻችን የንብረት ባለቤትነትን እና ግብይቶችን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎችን ያብራራሉ እንዲሁም የተለመዱ ማጭበርበሮችን እና ህጋዊ መፍትሄዎችን ይጠኡማሉ።
የውክልና ስልጣን (Power of Attorney, PoA)፡- ውክልና ከውጪ ሆነው ጉዳዮችዎን ለማስተዳደር ወሳኝ መንገድ ቢሆንም ብዙዎችን ለምዝበራ የዳረገ የተለመደ የብዝበዛ ምንጭ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዮችዎን ለማስተዳደር ስለሚያስችለው ህጋዊ POA፣ ህጋዊ ወሰኑን፣ በኢትዮጲያ ያሉ ጉዳዮችዎን ለማስፈጸም የሚስያስችል ትክክለኛው ውክልና ለማዘጋጀት እና ለመጠቀም እየሚረዱ ልምዶችን ይማራሉ።
አዲሱን የንብረት ማስመለስ እና መውረስ ህግን መረዳት፡ የኢትዮጵያን ንብረት ማስመለስ እና ንብረት መውረስ አዋጅን (አዋጅ ቁጥር 1364/2025) ማብራራት እና መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመጠቆም የህጉን ወሰን፣ ወደ ኋላ አተገባበር እና "ያልተገለጹ ንብረቶች" የሚለውን ጽንሰ-ሀሳብን ማብረራትን ያካትታል። ይህ ህግ በእርስዎ ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እና ንብረቶችዎን ለመጠበቅ ምን አይነት ቅድመ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብዎት መረጃ ያገኛሉ።
የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ላይ ያለው ለውጥ፡
የኢትዮጵያ የጥብቅና ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ በሕግ ቴክኖሎጂ (Legal-Tech) እንዴት እየተቀየረ እንዳለ ያውቃሉ? ከተለምዷዊ "ራፖርት ወይም ማመልከቻ ጽሀፊዎች" እስከ የህግ ቴክኖሎጂ እድገት እንዲሁም እነዚህ እድገቶች ለዲያስፖራዎች የበለጠ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዴት እንደሚሰጡ እናስረዳለን።
የዲያስፖራውን መብት ለማስጠበቅ በምናደርገው ጉዞ ይቀላቀሉን። ይህ ከተለመደው የተለየ እና በጋራ መፍትሄ ለመፈለግ የምንመክርበት ነው፡፡ እንዲሁም የዲያስፖራውን ማህበረሰባችንን የማንቃት እና ብተናጥል የሚደርስበትን ትቃት በጋራ መፍትሄ እንዲፈልግ እና መብቱን እንዲያስክብር አይን ከፋች ጅምር ነው።
መሠረታዊ የሕግ እውቀትን በማስጨበጥ በዲያስፖራው ላይ የሚፈፀመውን ማጭበርበር(scams targeting the diaspora) ለመዋጋት የታሰበ ነው::