አለ ሕግ

አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልግሎት
ለሕግ ምክር አገልግሎት ቴሌግራም 👉 https://t.me/AleHig
ስልክ 👉 +251920666595
Alternative legal enlightenment and Service
https://linktr.ee/alehig
Our Website:- alehig.com

21/06/2026

የሕግ ባለሙያ ስብዕና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ወሳኝ ነው🙏✍️

20/06/2026

ፍርድ ቤት የፍትህ ማረፊያ እንጂ፣ የክርክር መድረሻ ብቻ መሆን የለበትም🙏✍️

ክብርት ዳኛዋን በችሎት የገደለው እራሱን አጠፋ።በችሎት አዳራሽ በሽጉጥ ክብርት ዳኛዋን እና ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ ከ3ኛ ፎቅ ላይ እራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጠፋ። ግንቦት 27 ቀን 201...
20/06/2026

ክብርት ዳኛዋን በችሎት የገደለው እራሱን አጠፋ።

በችሎት አዳራሽ በሽጉጥ ክብርት ዳኛዋን እና ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ ከ3ኛ ፎቅ ላይ እራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጠፋ።

ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በሆለታ ወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት አዳራሽ የቤተሰብ ክርክርን መዝገብ ስትመለከት የነበረችው ክብርት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ እንዲሁም የክርክሩ አካል የሆነች የተከሳሹ የቀድሞ ባለቤት ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸውን እንዲያልፍ ማድረጉ አይዘነጋም።

በዕለቱም እራሱ ላይ በመተኮስ ቆስሎ የነበረዉ አቅነዉ በቀለ የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ጥበቃ እየተደረገ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ላይ ነበር።

ሆኖም ግለሰቡ በዛሬው ቀን ሕክምናውን ጨርሶ ከሆስፒታሉ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ጊዜ ላይ ከሆስፒታሉ ሕንፃ 3ኛው ፎቅ በመስኮት እራሱን በመወርወር እራሱን ማጥፋቱ ተረጋግጧል።

Via: ታሪክ አዱኛ

7ኛው መፅሐፌየፍትሐብሔር ፍርድ አፈጻፀም የሚለውከቀን 12/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ ይገኛል፡፡መፅሐፉ በትልቁ የመፅሐፍ መጠን (በ “B 5”) በ17 ምዕራፎች ተከትቦ በ446 ገፅ ...
19/06/2026

7ኛው መፅሐፌ
የፍትሐብሔር ፍርድ አፈጻፀም የሚለው
ከቀን 12/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ ይገኛል፡፡

መፅሐፉ በትልቁ የመፅሐፍ መጠን (በ “B 5”) በ17 ምዕራፎች ተከትቦ በ446 ገፅ ተቀንብቦ ለተደራሲያን እነሆ ጀባ በያለሁኝ፡፡

በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የፍርድ ሕይወቱ መፈፀሙ (The life of a decision is an ex*****on) ከሚለው መርህ (“ከሚል መሪ ቃል”) እጅግ በርካታ የሆኑ በፍርድ አፈጻፀም አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን ከሕጉ፣ ከሰበር እና ከፌዴራሽን ምክር ቤት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር በሰፊው ተዳሰዋል፡፡

መፅሐፉን ልዩ የሚያደረገው

ይህ መፅሐፍ ከዚህ ቀደም ለሕትመት ካበቃዎቸው መፅሐፍት የሚለይበት አንድ ቁልፍ ነጥብ አለ፡፡ ይኸውም የፍርድ አፈጻፀም ችግሮችን ለይቶ ለፍርድ አፈጻፀም መሰረት የሚሆነውን ውሳኔ ከሚሰጠው እና ከአፈጻፀም ችሎቱ እስከ ፍርድ አስፈጻሚ አካል እና ለፍርድ አፈጻፀም ባለድርሻ አካላት እስሆኑት ድረስ መፍትሔዎችን ማስቀመጡ ነው፡፡ በመሆኑም መፅሐፉ ችግር ነቃሽ ብቻ ሳይሆን መፍትሔም አቅራቢም ጭምር መሆኑ ነው፡፡

19/06/2026

ውል የሰዎች መተማመኛ ሲሆን ሕግ ደግሞ የውል ጠባቂ ነው🙏✍️

16/06/2026

መከላከል ከማከም፣ የሕግ ምክርም ከክስ ሂደት ይበልጣል✍️🙏

15/06/2026

እውነት የፍትህ ነፍስ ናት፤ ሕግ ደግሞ የፍትህ አካል❓❓❓

15/06/2026

💡 የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1142/2018 ✍️
የታክስ አስተዳደር ሥርዓትን ማዘመንና ከወቅቱ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ማጣጣም የአንድ አገር ኢኮኖሚ በጤናማ ሁኔታ ለመራመድ ካሉት መሠረታዊ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መመሪያ እስካሁን ሳይወጣ መቆየቱ በታክስ አሰባሰብ፣ በዲጂታል ንግድ ቁጥጥርና በሕግ ተፈጻሚነት ረገድ በርካታ መዋቅራዊ ክፍተቶችን ፈጥሮ ቆይቷል።

በተለይም ፈጣን ዕድገት እያሳየ የመጣው የኢኮሜርስ (e-Commerce) ዘርፍ፣ የኦንላይን የገበያ መድረኮች እና የተለያዩ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ግልጽና ወጥ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ስላልነበራቸው መንግሥት ማግኘት የሚገባውን የታክስ ገቢ እንዲያጣ ከማድረጉም በላይ ሕጋዊ ታክስ ከፋዮች ካልተመዘገቡ ነጋዴዎች ጋር ፍትሐዊ ያልሆነ የገበያ ውድድር ውስጥ እንዲገቡ አስገድዶ ነበር። በተጨማሪም የወረቀቱ የደረሰኝ አሰጣጥ ሥርዓት ለታክስ ስወራ፣ ለሐሰተኛ ደረሰኝ ዝውውርና ለአሠራር መጓተት ሰፊ በር ከፍቶ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህ አዲስ የወጣው መመሪያ ቁጥር 1142/2018 እነዚህን ክፍተቶች በመሙላት ረገድ የሚከተሉት ከፍተኛ ፋይዳዎች አሉት፦
💡 የታክስ ስወራን መከላከልና ገቢን ማሳደግ፡ እያንዳንዱ ግብይት በተከናወነበት ቅጽበት (Real-time) በቀጥታ ከባለሥልጣኑ ማዕከላዊ ሥርዓት ጋር እንዲገናኝ በማድረጉ እና ደረሰኝ ማተም የሚቻለው የማዕከሉን መለያ ቁጥር (IRN) እና QR Code ሲያገኝ ብቻ በመሆኑ ሐሰተኛ ደረሰኞችን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
💡 ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግልጽ የሕግ ማዕቀፍ መፍጠር፡ መመሪያው የኢኮሜርስ ኦፕሬተሮችን፣ የክላውድ ሽያጭ መመዝገቢያዎችን እና ሶፍትዌርን እንደ አገልግሎት አቅራቢዎችን ሕጋዊ ኃላፊነት በግልጽ አስቀምጧል። በአንድ መድረክ ላይ ከአንድ በላይ ሻጮች ቢኖሩ እንኳ እያንዳንዱ አካል በገዛ የ-TIN ቁጥሩ ደረሰኝ እንዲቆርጥ በማስገደድ በዲጂታል ገበያው ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፍናል።
💡 የንግድ አሠራርን ማቅለልና ወጪን መቀነስ፦ ታክስ ከፋዮች የሽያጭ መረጃዎችን በዲጂታል አማራጮች (በኢሜይል ወይም በ-SMS) ለገዥዎች መላክ እንዲችሉ በመፍቀድ የሕትመትና የካርቦን ወጪን ከመቀነሱም በላይ ንግዶች የራሳቸውን የውስጥ ሥርዓት ከታክስ ሥርዓቱ ጋር በቀላሉ እንዲያዋህዱ ዕድል ይሰጣል።
💡 የመረጃ ደህንነትና የኦዲት ተአማኒነት፡ ሥርዓቱ ከመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ዕውቅና ማግኘት ያለበት በመሆኑ እና የኦዲት መዝገብ (Audit Log) እንዲኖረው ስለሚያስገድድ፣ የታክስ ከፋዩ መረጃ በምስጠራ (Encryption) ተጠብቆ እንዲቆይና ባለሥልጣኑ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሕጋዊ ኦዲት እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
💡 የአሠራር ቀጣይነትን ማረጋገጥ፡ የኢንተርኔት መቆራረጥ በሚኖርበት ጊዜ ንግዶች እንዳይደናቀፉ የራሱ የሆነ "ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ ሥራ ማስቀጠያ ሥርዓት" (Offline Resiliency) መዘርጋቱ የንግድ እንቅስቃሴው ሳይቋረጥ ታክስ በአግባቡ እንዲመዘገብ ያስችላል።

በአጠቃላይ ይህ መመሪያ መውጣቱ በታክስ አስተዳደሩ ላይ የነበሩትን ክፍተቶች በመሙላት የዲጂታልና የሕግ ሥነ-ምኅዳሩን በማቀናጀት፣ ፍትሐዊ የንግድ ውድድር እንዲሰፍንና የአገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ሕጋዊ መሠረት እንዲይዝ የሚያደርገው ፋይዳ እጅግ የጎላ ነው።
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት
Covenant Hub Law Firm LLP

15/06/2026

ቃል ሳይገቡ መኖር ነጻነት ነው፤ ገብቶ አለመፈጸም ግን በህሌና ሕግ መታሰር ነው።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አለ ሕግ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አለ ሕግ:

Share

Category