ሕጉ ምን ይላል ?

ሕጉ ምን ይላል ? Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሕጉ ምን ይላል ?, Lawyer & Law Firm, Bole Street, Addis Ababa.

⚖️"ሕጉ ምን ይላል"is the leading legal awareness page in providing various legal issues to communities.ABEBAW ABEBE is a Legal Advocates,Moderator,Author,founder and CEO for Maya Charitable Organization.📞+251991228122 +251942406060 www.abebawabebelawfirm.com

25/08/2026

ለወንጀል ጠቋሚ የሚከፈል ወሮታን በተመለከተ !
ሕጉ ምን ይላል ?

24/08/2026

ክሱን ያቋረጠ ከሳሽ በድጋሜ ክሱን ማንቀሳቀስ ይችላልን ?
ሕጉ ምን ይላል ?

24/08/2026

የሃራጅ ሽያጭ ያሸነፈ ሰው በምን ያህል ግዜ ነው ሙሁ ክፍያ መፈፀም ያለበት ? ሕጉ ምን ይላል ?

22/08/2026

በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ እንዲያስረዳ የሚጠበቀው የማስረጃ ሁኔታን በተመለከተ ! ሕጉ ምን ይላል ?

Vote For Ethiopia !!!
22/08/2026

Vote For Ethiopia !!!

22/08/2026

ሁከት ይወገድልኝ ምንድነው ?
ሕጉ ምን ይላል ?

10/08/2026

የአባቴ ስም ተሰርዞ በአሳዳጊዬ ስም ልጠራ በሚል አቤቱታ ማቅረብ እና ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል ?
ሕጉ ምን ይላል ?

10/08/2026

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ6ኛው የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በመዝገብ ቁጥር 150 በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ሰው፣ የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

​አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ (ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢሆን) ቤት ቢሠራ፣ የመሬቱ ባለይዞታነት ወይም የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም።
​የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው ሰው እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት አይደለም።

​ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ መብት ለቤቱ/ለግንባታው ያወጣውን ወጪ (ግምት) ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ ነው።
​በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት የሰጣቸውን የቀደሙ አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ናቸው በማለት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።

06/08/2026

የዋና ጥያቄ፣ መስቀለኛ ጥያቄና ድጋሚ ጥያቄ ምንነት ፦
1. ዋና ጥያቄ (Examination-in-Chief)
ዋና ጥያቄ የመጀመሪያ ጥያቄ ሆኖ መስካሪውን የጠራው ተከራካሪ ለምስክርነት ላቀረበው ሰው የሚያቀርብ ጥያቄ ሲሆን የዚህ ዋና ዓላማም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የጠሪው ተከራካሪ ወገንን የሚደግፉ እውነታዎችን በሚመለከት የምስክሩን ቃል ለማቅረብ ነው፡፡
ጭብጡን የሚመለከትና በቀጥታ ወይም በሌላ መንገድ ምስክሩ በሚያውቀው ወይም ሊያውቀው በሚችለው ነገር ላይ ብቻ የተመሰረተ ጥያቄ ነው።
በዚህ ግዜ ማለትም በዋና ጥያቄ ላይ ምስክሩን መምራት ወይም መሪ ጥያቄ ማቅረብ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ጠያቂው መልሱን ለምስክሩ መንገር ወይም ማሳየት የለበትም፡፡
2. መስቀለኛ ጥያቄ (Cross-Examination)
ይህ ጥያቄ ከዋና ጥያቄ ቀጥሎ በተቃራኒ ተሟጋች በኩል ለምስክሩ የሚቀርብ ሲሆን አላማውም የምስክሩን ትክክለኛነት እና ተዓማንነት ለመፈተን፤ በተሰጡት የምስክርነት ቃል ውስጥ የማይጣጣሙ ነገሮችን ለማጉላት ወይም ቀድሞ የተሰጡትን የምስክርነት ቃል ሊያዳክሙ የሚችሉትን እውነታዎች ለማስተዋወቅ ምስክሩ በመጀመሪያ ጊዜ የሰጠው የምስክርነት ቃል የተሳሳተበትን፤ እውነት ያልሆነውን ቃል፣ ወይም አጠራጣሪ መስሎ የተገመተበትን ነጥብ ፍርድ ቤቱ እንዲረዳው ለማድረግ የሚቀርብ ጥያቄ ነው።
በመስቀልኛ ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄዎችን መጠየቅ የተፈቀደ ነው፡፡
3. ድጋሚ ጥያቄ (Re-Examination)
ይህ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ምስክሩን በጠራው ተከራካሪ ወገን ለምስክሩ የሚሰነዘር ጥያቄ ሲሆን ጥያቄውም ምስክሩ በመስቀልኛ ጥያቄ ላይ የሰጠውን ቃል ለማብራራት ወይም ለማጣራት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።
ከመስቀለኛ ጥያቄ ጋር ያልተያያዙ አዳዲስ ርዕሶችን አንስቶ በድጋሚ ጥያቄ ላይ መጠየቅ አይፈቀዱም፡፡
በዚህ ግዜ ላይ፤ ምስክሩን መምራት ወይም መሪ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም።
* መሪ ጥያቄ
መሪ ጥያቄ ጠያቂው በጥያቄው ለተጠያቂው መልሱን የሚያሳይበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ጠያቂው ቃላትን ወደ አፍ እንደማስገባት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ቀይ መኪና አይተሃል አይደል? በሚል የሚቀርብ ጥያቄ መሪ ጥያቄ ነው፡፡ምክንያቱም ጠያቂው ምስክሩ አዎ ብሎ እንድመልስ የቀረበ መሪ ጥያቄ ነው፡፡ ነገር ግን ያየሄው መኪና ምን ዓይነት ቀለም ነው? በሚል የሚቀርብ ጥያቄ መሪ ጥያቄ አይደለም፡፡
የ/ፍ/ስ/ስ/ህግ/ቀ. 263 (1-4)
ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 137(1-3)፣ 13

Ovid Real state Brand Ambassadorship   Agreement 🙏
06/08/2026

Ovid Real state Brand Ambassadorship Agreement 🙏

Address

Bole Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሕጉ ምን ይላል ? posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሕጉ ምን ይላል ?:

Shortcuts

Share