የሕግ ጉዳዮች ምክርና ጠበቃ / Attorney and Legal Advise

የሕግ ጉዳዮች ምክርና ጠበቃ / Attorney and Legal Advise we are a professional Lawyer aimed at providing legal advise, counselling, Attorney and other representation services.

07/04/2026

የውጭ ሀገር ገንዘብን በአደራ ማስቀመጥና መዘዙ
ውልን የሚያደርጉ ወገኖች የመዋዋል ነጻነት (Freedom of Contract) ያላቸው ቢሆንም ይህ የመዋዋል ነጻነት ፍጹማዊ አይደለም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ተዋዋይ ወገኖች ውጭ ሀገር ገንዘብን በአደራ ለማስቀመጥ ውል ይዋዋላሉ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ምንም እንኳን ተዋዋዮች የመዋዋል ነጻነት ያላቸው ቢሆነም በወንጀለኛ መቅጫ ህጋችንና በብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የውጭ ሀገር ገንዘብ ተቀመጠው ገደብ በላይ መያዝም ሆ0ነ ማስቀመጥ በህግ የተከለከለ በመሆኑ ይህንን ህግ በመተላለፍ የሚደረግ ውል ህግ ወጥ ተግባር በመሆኑ ውሉ ሊጸናም ሆነ ሊፈጸም የማይችል ከመሆነጀም በላይ ወንጀል ተጠያቂነት ያመጣል፡፡
የፍብ/ህ/ቁ 1716 (1)፣1678፣ወንጀሌ ህግ አንቀጽ 346 ፣አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 26 ፣ የብሓራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤፌ.ኤክስ.ዱ. 49/2017

ቴሌግራም:
ስልክ፡ (+251) 0911538683
https://t.me/GetishSalewLaw
facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61555121422107

07/04/2026

በፍርድ ቤት ውልን መሰረት ያደረገ ክርክር እና ክርክርን በእርቅ ለመጨረስ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
ውልን መሰረት በማድረግ በፍርድ ቤት ዘርፈ ብዙ ክርክሮች ይስተዋላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አብዛኛው ክርክሮች በእርቅ ከተቋጩ ቡኋላ ተከራካሪ ወገኞች በእርቅ ስምምነቱ ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው ነገሩ በእርቅ ካለቀና ስምምነቱም በፍርድ ቤት ከጸደቀ ቡኋላ አለመግባባት ሲፈጠር ተከራካሪ ወገኞች የእርቅ ስምምነቱን እንደ መደበኛ ውል በመውሰድ ውል ይፍረስልን ክስ እንደ አዲስ ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን አንድ የእርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ቀርቦ ስምምነቱ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከጸደቀ ቡኋላ እንደ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚቆጠር እና ቀጥታ የአፈጻጸም ክስ የሚቀርብበት እንጅ እንደ ማንኛውም ውል ተቆጥሮ ውል ይፍርሰስልኘ ክስ ሊቀርብበት የማይችል በመሆኑ በውል ላይ ተመስርቶ ያለንን ክርክር በእርቅ ስንጨርስ ድጋሜ ውሉን ለማፍረስ እድል የማናገኝ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁ/386፣ 392
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ
ቴሌግራም:
ስልክ፡ (+251) 0911538683
https://t.me/GetishSalewLaw
facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61555121422107

13/03/2026

በወንጀል ክስ የአቃቤ ህግ ማስረጃ አሰማምና የተከሳሽ መከላከል አንዳንድ ነጥቦች፡-
አንድ ተለይቶ ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን መሰረት በማድረግ ምርመራ የሚጀመረውም ሆነ ምርመራው ከተጠናቀቀ ቡኋላ ክስ የሚመሰረተው በመርህ ደረጃ በመንግስት በተቋቋመ ክፍል ነው፡፡ ስለሆነም በተደራጀ ተቋም የሚካሄድ ምርመራና የሚቀርብ ክስ ከተጠርጣሪው ወይም ከተከሳሹ የተሻለ አቅም ባለው አካል የሚከናወን ነው፡፡ ይህ ማለት በአንጻራዊ ከተጠርጣሪው ወይም ከተከሳሹ ይልቅ ምርመራውን የሚያካሂደውም ሆነ ክስ የሚመሰርተው አቃቤ ህግ ከተከሳሹ በተሻለ መልኩ የወንጀል ህጉን ይዘት፤ የወንጀል ምርመራን በተመለከተ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ህጉን እና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ይዘት በተሻለ መልኩ ይረዳል፡፡ በዚህ ሂደት በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛ ተብሎ ፍርድ የሚሰጥባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ ከሰማ ቡኋላ በተከሳሹ በኩል ማፍረሻ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ሳይሆን ተከሳሹን ጥፋተኛ የሚያደርገው አይደለም በማለት በነጻ ካላሰናበተው በስተቀር መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብና እንዲያሰማ ትእዛዝ ይሰጣል ወይም ለተከሳሹ ይነግረዋል፡፡ ስለሆነም በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ነው፡፡
ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባለት ማስረጃዎች ላይ በአንዴም ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን እንዳይኖር ማድረግ በመሆኑ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የአቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም አቃቤ-ህግ በአቀረበው ክስና ምስክሮች ተከሳሹ የተመሰከረበት ከሆነ ከላይ በተገለጸው መሰረት ማለትም የተከሰሱበትን የወንጀል ህግ ድንጋጌና ይዘትን እንዲሁም የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ህጉን እና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ይዘት በአግባቡ በመረዳት የአቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬ መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡
ቴሌግራም:
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን

22/09/2025

ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ መሰረት ጋብቻ ለመፈጸም በተጋቢዎቹ መሟላት ያለባቸው ሁኔታወች አሉ፡፡
አንደኛው እድሜ ሲሆን ተጋቢዎቹ ወንዱም ሆነ ሴቷ እድሜያቸው 18 አመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዱ ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት የፍትህ ሚንስትሩ ከመደበኛው የጋብቻ እድሜ ወይም ከ18 አመት ከሁለት አመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቀድ ይችላል፡፡ በዚህ መሰረት ከባድ ምክንያት ካጋጠመ በሚንስትሩ ፈቃድ የ16 አመት ልጅ ጋብቻ ልትፈጽም ትችላለች ማለት ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ በህጉ ተለይቶ የተቀመጠ ዝምድና (የስጋም ይሁን የጋብቻ ዝምድና ) ካለ ጋብቻመፈጸም የተከለከለ ነው፡፡ ይህም ሲባል በስጋ የሚዛመዱ በቀጥታ የስጋ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈጸም አይቻልም፡፡ እንዲሁም የጋብቻ ዝምድና ካለ ባል ከሚስቱ እህት ወይም ሚስት ከባሏ ወንድም ጋብቻ መፈጸም አይቻልም፡፡ እንዲሁም የአንድ ሰው ተወላጅነት በህግ መሰረት የተረጋገጠ ባይሆንም እንኳን በማህበረሰቡ ዘንድ በተወላጅነት የሚታወቅ ከሆነ ከላይ በተጠቀሰው ዝምድና መሰረት ጋብቻ መፈጸም አይቻልም፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ማንኛውም ሰው አስቀድሞ በጋብቻ የተሳሰረ ከሆነ ይህው ጋብቻ ጸንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ መፈጸም አይችልም፡፡ ይህም ማለት በጋብቻ ላይ ጋብቻ የተከለከለ ነው፡፡
በአራተኛ ደረጃ የተጋቢዎች ፈቃድ አስፈላጊ ሲሆን የጸና ጋብቻ እንዲኖር ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነጻና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሊሰጡ ብቻ ነው፡፡ ፈቃድን በተመለከተ በተጋቢዎቹ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ስህተት ከተፈጸመና ፈቃድ ከተጓደለ ጋብቻው አይጸናም ወይም ህጋዊ ውጤት አይኖረውም፡፡ መሰረታዊ ስህተት ማለት ለምሳሌ ተጋቢዎቹ በስህተት ምክንያት አገባዋለው/አገባታለው ብሎ ያላሰበውን/ያላሰበችውን ሰው ያገባ/ያገባች እንደሆነ፤ የሚያገባው ሰው ሊድን የማይችል ከባድ በሽታ ወይም ለተወላጆች ሊተላለፍ የሚችል ነዋሪ በሽታ ያለበት/ያለባት መሆኑን ሳያውቅ ያገባ እንደሆነ፤ ሌላው ተጋቢ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም የማይችል መሆኑን ባለማወቁ ምክንያት ያገባው እንደሆነ እና ሌላው ተጋቢ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙኘት የመፈጸም ልማድ ያለው መሆኑን ባለማወቅ ምክንያት ያገባው ከሆነ በፈቃድ አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ስህተት እንዳለ የሚያስቆጥሩ በመሆኑና በዚህ ስህተት ምክንያት ፈቃድ ስለሚጓደል በዚህ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ አይጸናም፡፡
በአጠቃላይ የጸና ጋብቻ እንዲኖር ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በሚገባ መሟላት አለባቸው፡፡

ጌትነት ሳለው ጠበቃና የሕግ አማካሪ
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
ቴሌግራም፡ https://t.me/GetishSalewLaw
Facebook : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555121422107

18/09/2025

በወንጀል ክስ የአቃቤ ህግ ማስረጃ አሰማምና የተከሳሽ መከላከል አንዳንድ ነጥቦች፡-
አንድ ተለይቶ ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን መሰረት በማድረግ ምርመራ የሚጀመረውም ሆነ ምርመራው ከተጠናቀቀ ቡኋላ ክስ የሚመሰረተው በመርህ ደረጃ በመንግስት በተቋቋመ ክፍል ነው፡፡ ስለሆነም በተደራጀ ተቋም የሚካሄድ ምርመራና የሚቀርብ ክስ ከተጠርጣሪው ወይም ከተከሳሹ የተሻለ አቅም ባለው አካል የሚከናወን ነው፡፡ ይህ ማለት በአንጻራዊ ከተጠርጣሪው ወይም ከተከሳሹ ይልቅ ምርመራውን የሚያካሂደውም ሆነ ክስ የሚመሰርተው አቃቤ ህግ ከተከሳሹ በተሻለ መልኩ የወንጀል ህጉን ይዘት፤ የወንጀል ምርመራን በተመለከተ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ህጉን እና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ይዘት በተሻለ መልኩ ይረዳል፡፡ በዚህ ሂደት በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛ ተብሎ ፍርድ የሚሰጥባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ ከሰማ ቡኋላ በተከሳሹ በኩል ማፍረሻ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ሳይሆን ተከሳሹን ጥፋተኛ የሚያደርገው አይደለም በማለት በነጻ ካላሰናበተው በስተቀር መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብና እንዲያሰማ ትእዛዝ ይሰጣል ወይም ለተከሳሹ ይነግረዋል፡፡ ስለሆነም በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ነው፡፡
ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባለት ማስረጃዎች ላይ በአንዴም ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን እንዳይኖር ማድረግ በመሆኑ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የአቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም አቃቤ-ህግ በአቀረበው ክስና ምስክሮች ተከሳሹ የተመሰከረበት ከሆነ ከላይ በተገለጸው መሰረት ማለትም የተከሰሱበትን የወንጀል ህግ ድንጋጌና ይዘትን እንዲሁም የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ህጉን እና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ይዘት በአግባቡ በመረዳት የአቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬ መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡
ቴሌግራም:
ስልክ፡ (+251) 0911538683
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
https://t.me/GetishSalewLaw
Fb: https://www.facebook.com/profile.php?id=61555121422107

01/09/2025

የውል መሰረታዊ ዓላማ በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ እና ይርጋ፡-
ውልን በተመለከተ በጠቅላላው የሚነሱ ክርክሮች በተለይም ውል እንዲፈጸም ወይም ካለመፈጸሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዳት ወይም ውል እንዲፈርስ የመጠየቅ መብት በ10 አመት ይርጋ እንደሚታገድ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ያስገነዝባል፡፡ ይህ ድንጋጌ በጠቅላላ አነጋገር የተቀመጠ ሲሆን ልዩ ሁኔታዎች ወይም በይርጋ ሊታገድ የማይችሉ ውሎች እንዳሉ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡
አንድ ውል በህግ ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው 4 መሰረታዊ መስፈርቶች መሟላት እንዳለባቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678 የሚያስገነዝብ ሲሆን እነሱም ውሉን ለማድረግ ሙሉ ፍላጎት፤ የተዋዋዮች አቅም፤ የውሉ ህጋዊነትና በህጉ የተመላከተውን አቀራረጽ ወይም ፎርም የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡ ከእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ ውሉ በህግ የተከለከለና የውሉ መሰረታዊ ዓላማ በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ (Unlawful Contract) እና በህጉ የተመላከተውን አቀራረጽ ፎርም ያላሟላ እንደሆነ ውሉ ከመሰረቱ እንዳልተደረገ የሚቆጠር፤ ረቂቅ እና ዋጋ አልባ የሚያደርጉት በመሆኑ ከላይ በፍ/ህ/ቁ 1845 የተቀመጠው የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 43226 የካቲት 07 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፍ/ህ/ቁ/1678፣1716 እና 1718ን በመተርጎም የውሉ መሰረታዊ ዓላማ በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ዳኞች ህገ ወጥ (unlawful contract) የሆነውን ውል በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ ህጋዊ ውጤትና ተፈጻሚነት የለውም በማለት ለመወሰን እንደሚችሉና ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊሆን እንደማይችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
ቴሌግራም:
ስልክ፡ (+251) 0911538683
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
https://t.me/GetishSalewLaw
በማናቸውም የፌደራል ፍ/ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ

31/08/2025

ስለ ስጦታ ውል አንዳንድ ነጥቦች፡-
አንድ ሰው ያለውን የንብረት ባለቤትነት መብት መገለጫዎች ውስጥ አንዱና ዋናው ንብረትን በስጦታ ማስተላለፍ ሲሆን ባለንብረቶች ከሞቱ ቡኋላ ተፈጻሚ የሚሆን የማይንቃሳቀስ ንብረት ስጦታ ያደርጋሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ የስጦታ ውሎች በውል አዋዋይ ፊት እንዲመዘገብ አስገዳጅ አይደሉም፡፡ በዚሁም መሰረት ስጦታ አድራጊ ከሞተ ቡኋላ ተፈጻሚ የሚሆን የማይንቀሳቀስ የስጦታ ውልን በተመለከተ ሕጉ ጥብቅ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያስቀምጥ ሲሆን እነዚህም በፍ/ብ/ህ/ቁ 85 እና ተከታዮቹ፤ 881፤883 እና 2443 እና ተከታዮቹ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም፡-
1ኛ. በስጦታ ውሉ የተካተተው ንብረት በእርግጥም የስጦታ አድራጊ መሆን ይኖርበታል፤
2ኛ. ስጦታው በጽሁፍ መደረግ አለበት፤
3ኛ. ስጦታ አድራጊው ስጦታውን ያለማንም አስገዳጅ በራሱ ሙሉ ፈቃድ ያደረገ መሆኑ መገለጽ አለበት፤
4ኛ. የስጦታ ውሉ የግዴታ በአራት ምስክሮች መፈረም ያለበት ሲሆን ምስክሮቹም ህጋዊ ተግባራትን ለመፈጸም አቅም ያላቸው መሆን አለባቸው፤
5ኛ. የስጦታ ውሉ በስጦታ ሰጭ እና በምስክሮች ፊት መነበብና ይህው የማንበብ ስርአት ስለመፈጸሙ በስጦታ ውል በግልጽ መመላከት ይኖርበታል፤
6ኛ. ስጦታ አድራጊና ምስክሮች በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
ስለሆነም እነዚህ ጥብቅ የሆኑ መስፈርቶች አለመሟላት የውሉን መፍረስእና ዋጋ አልባ መሆንን የሚያስከትሉ የስጦታ ውሉ በህግ ፊት የጸና እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት መስፍረቶች በአግባቡ መሟላት አለባቸው፡፡

ስልክ፡ (+251) 0911538683
ቴሌግራም:
ለተጨማሪ የህግ ግንዛቤ ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
https://t.me/GetishSalewLaw
በማናቸውም የፌደራል ፍ/ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ

አሁን በተግባር እንደሚታየው የሪል ስቴት ቤተ ሽያጭን በተመለከተ አልሚዎች ግንባታ ሳያካሂዱ አልያወ የተወሰነ ግንባታ በመጀመር ብቻ ሽያጭ ሲያከናውኑ ይስተዋላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሪልስቴት...
08/07/2025

አሁን በተግባር እንደሚታየው የሪል ስቴት ቤተ ሽያጭን በተመለከተ አልሚዎች ግንባታ ሳያካሂዱ አልያወ የተወሰነ ግንባታ በመጀመር ብቻ ሽያጭ ሲያከናውኑ ይስተዋላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሪልስቴት ግንባታ ጋር በተገናኘ አከራሪ ከሆኑ ጉዳዮች ዉስጥ አንዱ ጅምር ቤት ወደ ሶስተኛ ወገን ሊተላለፍ የሚችለዉ ግንባታዉ በየትኛዉ ደረጃ ላይ እያለ ነዉ የሚለዉ ነዉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ገና መሰረቱ የወጣን ቤት ለማስተላለፍ ስምምነት ተደርጎ፣ ክስ ከቀረበ በኋላ ጅምር ቤቱን ለማስተላለፍ ታምኖ ሲቀርብ ይስተዋላል፡፡ ከዚህ ላይ ጥያቄ የሚሆነዉ ጅምር የሪልስቴት ግንባታን ለማስተላለፍ ስምምነት ተደርጎ ወይም ክስ መቅረቡን ተከትሎ ለማስረከብ ታምኖ ሲመጣ ማስተላለፍ ይቻላል ወይ የሚለዉ ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ አስተዳደር ቦታን በሊዝ ለመያዝ ለመደንገግ የወጣ ደንብ ቁጥር 49/2004 አንቀጽ 39(2) መሰረት ሪል ስቴት አልሚ በተናጠል ለተጠቃሚ ከዉርስ በስተቀር ማስተላለፍ የሚችለዉ በደንቡ አንቀጽ 2(21) እና 39(5) መሰረት በግማሽ ወይም የግንባታዉ 50 በመቶ መሰራቱ ሲረገገጥ ነዉ፡፡
በተጨማሪም አዲስ በወጣዉ የሪልስቴት ግንባታ አዋጅ ጅምር ቤት ወደ ሶስተኛ ወገን ሊተላለፍ የሚችለዉ ግንባታዉ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ነዉ፡፡
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.235838 ዉሳኔ ሰጥቷል ::

Follow us on ቴሌግራም: https://t.me/GetishSalewLaw

Discussion about Law !

04/07/2025

ቁም ኑዛዜ ስጦታ

ሟች በህይወት እያለ በኑዛዜ ስጦት መስጠት የሚችል ሲሆን ለዚህም ህጉ የሚያስቀምጠው ፎሮሞች አሉ። ሟች ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለአንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ የሌሎችን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል አያስከትልም፡፡ ይህንንም የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻ ወይም አንድ ንብረት ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም፡፡

አባትና እናት ወይም ሌሎች ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸው እና ሌሎች ተወላጆች ሀብታቸውን ለመስጠትና ለማከፋፈል ይችላሉ፡፡ ይህ ክፍፍል ሥርዓት አንድን ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 1123 ተደንግጓል፡፡

አንቀጽ 1123/1/ ሲነበብ “በስጦታ አከፋፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንዱ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላል።
ቴሌግራም:

Join for more on : https://t.me/GetishSalewLaw

17/06/2025

የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የአስተዳደር አካላት በአንድ ወቅት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (ካርታ) ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ካርታው ከተሰጠ ቡኋላም ካርታ የተሰራለት ወገን ከ3ኛ ወገን ክርክር ቢነሳበት ፍ/ቤቱ ይህንን የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ መሰረት በማድረግ ውሳኔ ከሰጠ ቡኋላ በሌላ ጊዜ ካርታው በአስተዳደር አካሉ ቢመክን አስቀድሞ በፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በአንድ ጊዜና ሙሉ ለሙሉ ዋጋ የሚያሳጣው አይሆንም፡፡ ይልቁንም ካርታው በመምከኑ የተጎዳው ወገን የአስተዳደር አካሉ ካርታውን በማምከን የሰጠውን ውሳኔ ክርክር ሊያነሳበት የሚችልና ፍ/ቤቶችም የአስተዳደር አካሉ ካርታ የማምከን የወሰደውን እርምጃ አግባብነትና ህጋዊነት ሊመረመሩትና ውሳኔ ሊሰጡበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ የፍ/ብ/ህ/ ቁ 1195፣ 1196፣ ይህንን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 13 በመ/ቁ 64014 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 07:15 - 18:30
Thursday 08:00 - 21:30
Friday 07:30 - 16:00
Saturday 07:30 - 22:45
Sunday 07:30 - 18:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሕግ ጉዳዮች ምክርና ጠበቃ / Attorney and Legal Advise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share