Best Law Family

Best Law Family A page for Ethiopian Tax, Customs, Finance and Procurement laws.

11/02/2026
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ስለመደረጉ አሳውቋል።በቅርቡ ተሻሽሎ የወጣውን የባንኩ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁጥር (FXD/04/2026) ምን ይላል ? 1. የአገልግሎት ላ...
11/02/2026

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ስለመደረጉ አሳውቋል።

በቅርቡ ተሻሽሎ የወጣውን የባንኩ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁጥር (FXD/04/2026) ምን ይላል ?

1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡

2. ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ሕጋዊ ሰነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክ በማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋሩና ለልጆቹ የትምህርት፤ የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል፡፡

4. ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ምንጩ ከወጪ ንግድ የሚገኝን የውጭ ምንዛሪ ሳይጨምር በእርዳታ/ስጦታ አለያም ከሌላ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የተንቀሳቃሽ፣ የቁጠባና የጊዜ ገደብ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላል፡፡

5. ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የውጭ ምንዛሪ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ይጠየቁት የነበረው አነስተኛ 100 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀር ተደርጓል፡፡

6. ድርጅቶች የመዋእለ ነዋያቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስመረመሩ ከሀገር ውጭ በሌላ ሀገር መዋእለ ነዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

7. ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ወደ ሀገር ይዞት የተመለሰውን የትኛውንም ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮችና ሕጋዊ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በኩል ወደ ብር መመንዘር አለያም ወደ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ በማስገባት ተቀማጭማድረግ ይችላል፡፡

8. ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ሰነድ ለባኮች በማቅረብ መጠኑ ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ እንዲውል ከሀገር ወደ ውጭ ማስተላለፍ የሚችሉበት ሥርዓት ተፈቅዷል፡፡

9. ባንኮች የፎርዋርድ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ ማካሄድ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

10. የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፣ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡

11. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመጡት የውጭ ብድር (በገንዘብና በዓይነት) እና የሰፕላዬርብድርን የማጽደቅ ሥራ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መስፈርቶችን በተከተለ መልኩ ሙሉ በሙሉ በባንኮች እንዲከናወን ተፈቅዷል፡፡

12. ማንኛውም በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ላኪ ድርጅት ከማንኛውም የውጭ አካል የቅድመ ክፍያ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የስምምነት ሰነድ ለላኪው ድርጅት ደንበኛ ባንክ በማቅረብ የቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላል፡፡

13. በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለወደፊት የወጪ ንግድ ክፍያ እንደ ቅድመ ክፍያ የሚቆጠረው (ሀ) ስምምነቱ ገዥውን ለማመላከት ታስቦ “ቅድመ ክፍያው ለወደፊት ወጪ ወይም ገቢ ንግድ የሚውል" ወይ (ለ) ወደፊት ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦችን ከዘረዘረ ወይም የደረሰኝ ቁጥሩ ከተጠቀሰ አለያም የግብይት የውል ስምምነት ሰነድ ቁጥር በሚላከው የውጭ ምንዛሪ ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰ ይሆናል፡፡

14. ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

15. ባንኮች የውጭ ተቋም በሚሰጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ እና ደንበኛው በሚያቀርበው ጥያቄ ላይ በመመርኮዝ በአንድ ጉዳይ ከ20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከተመጣጣኝ የሌላ ሀገር ገንዘብ ያልበለጠ የውጭ ምንዛሪ ለህክምናና ለትምህርት ያለ ቪዛ እና የአውሮፕላን ትኬት ቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላሉ፡፡

16. ያለምንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሰነድ ለባንካቸው በማቅረብ እንዲሁም ባንኮች በመመሪያው መሰረት የቀረበው ሰነድ መሟላቱን በማረጋገጥ በትርፍ ክፍፍል መልክ ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ማስወጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

17. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎችን የገንዘብ ፍሰትና ካፒታል የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የሚይዘውን ተቀማጭ ገንዘብ፤ (አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሥራ ላይ ለሆኑ ቢሮዎች 30 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢያንስ ለስድስት ወራት በሥራ ላይ ላሉ ቢሮዎች 15 ሚሊዮን ብር) ተመላሽ ያደርጋል፡፡

18. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ቀደም ሲል ከነበረው የካፒታላቸው 10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ተሻሽሏል፡፡ ከዚህ በላይ የሆነ ትርፍ የውጭምንዛሪ ገንዘብ ለባንኮች መሸጥ አለበት፡፡

19. ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች አስፈላጊውን ሰነድ በመጠየቅ ለቪዛ፣ ለፓስፖርትና ለፈቃድ እድሳት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል፡፡

10_False_Claims from Trump’s recent talk about the Grand Ethiopian Renaissance DamFalse Claim No. 1: “The United States ...
23/01/2026

10_False_Claims from Trump’s recent talk about the Grand Ethiopian Renaissance Dam

False Claim No. 1: “The United States paid for the dam.”

False. GERD was built by Ethiopians and financed by Ethiopians through public bonds, domestic contributions, and state resources. The U.S., other countries, and international organizations were not involved. None.

False Claim No. 2: “The dam stops the Nile.”

False. That is not how hydropower works. Water enters. Water exits. GERD does not consume water, block the river, or hold it hostage. Electricity is generated by flow, not obstruction.

False Claim No. 3: “Ethiopia cut off Egypt’s water.”

This never happened. Not once. No river was shut. No country was denied flow. Repeating this story does not turn fiction into fact.

False Claim No. 4: “The Nile belongs to Egypt.”

This is the oldest false claim of all. The Nile rises in Ethiopia. Ethiopia contributes over 86 percent of the Nile’s water. A country that provides the water does not need permission to use it. Ownership does not come from habit.

False Claim No. 5: “This is a crisis Ethiopia created.”
Ethiopia built a power plant to electrify its people using its own river, on its own land. That is not a crisis. That is development. The real crisis is the belief that Africans must remain poor to keep others comfortable.
False Claim No. 6: “Someone allowed Ethiopia to build this dam.”
No one allows a sovereign nation to develop. Ethiopia did not ask for approval and did not need it. GERD exists because Ethiopians decided to build it.
False Claim No. 7: “GERD is a weapon.”
It is concrete, turbines, and transmission lines. It produces electricity. Water passes through it unchanged. That is all.
False Claim No. 8: “GERD threatens Egypt’s survival.”
GERD does not erase water, alter rainfall, or rewrite geography. Egypt’s water problems existed long before this dam. Blaming Ethiopia is easier than fixing mismanagement.
False Claim No. 9: “One powerful outsider can solve the despute.
False Claim No. 10: That Ethiopia must apologize for progress.

Ethiopia used its own resources, on its own river, to meet its people’s basic needs. That requires no apology.

GERD is not the problem.
Ethiopia is not the problem.
Misinformation is.

12/01/2026

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ሕግ በኢትዮጵያ

መግቢያ
እንደኢትዮጵያ ባለ አገር ውስጥ የከተማ መሬት ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል መሳሪያ ነው፡፡ በአገራችን ዘመናዊ የከተማ መሬት በሕግ እንዲተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርአት የተዘረጋለት በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት እንደነበር በተለያዩ ጸሐፍት ተገልጿል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በበርካታ የሕግ ማሻሻያዎችና ተቋማዊ አደረጃጀቶች ላይ እያለፈ ያለ ዘርፍ ነው። በአሁኑ ወቅትም በሁሉም ከተሞች ውስጥ የሚገኝን የመሬት ይዞታ መረጃ ለማደራጀት፣ በእያንዳንዱ የመሬት ይዞታ ላይ የሚገኝን መሬት ነክ ንብረት ከቁራሽ መሬት ይዞታው ጋር አስተሳስሮ ለመመዝገብ፣ መረጃውን ለማደራጀትና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1381/2017 ጸድቆ በሥራ ላይ ይገኛል። በዚህ ጽሑፍም የከተማ መሬትን ምንነት፣ የምዝገባ ሂደት፣ አዋጁ ያካተታቸውን ቁልፍ ጉዳዮች እና የተቀመጡ የሕግ ተጠያቂነቶችን እንመለከታለን።

የከተማ መሬት እና የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ምንነት
በአዋጁ አንቀፅ 2(2) መሠረት “የከተማ መሬት” ማለት በከተማ አስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኝ መሬት ሲሆን “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም 2 ሺ እና ከዚያ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያለው ሆኖ ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰው ኃይል ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ ላይ የተሰማራ ኗሪ የሚገኝበት አካባቢ እንደሆነ በዚሁ አንቀፅ 2(1) ስር ተደንግጓል።

“ምዝገባ” ማለት የመሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት ወቅታዊ መረጃ በወረቀት እና በዲጂታል ምዝገባ የሚመዘገብበት አሰራር ሲሆን “መሬት ነክ ንብረት” ማለት በመሬት ይዞታ ላይ ከላይ እና በታች ለንግድ፣ ለመኖሪያነት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለማኅበራዊ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ለሽያጭ፣ ለኪራይ አገልግሎት እንዲውል የተገነባ ህንፃ እና በመሬት ላይ የሚገኙ ቋሚ ተክሎችን የሚያካትት እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2(25) እና (4) ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

ተፈጻሚነትና ጠቅላላ መርሆዎች
አዋጁ በመላ አገሪቱ ውስጥ ባሉ ከተሞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን አዋጁ የከተማ መሬት ምዝገባ ሂደት የሚመሰረትባቸውን መርሆዎች አካቷል፡፡ ይኸውም
 የተረጋገጠ መሰረታዊ መብትን የማይነካ ስለመሆኑ፡- የምዝገባ ተቋሙ ቀደም ብሎ በይዞታው ላይ የተሰጠን መብት፣ ክልከላና ኃላፊነትን አረጋግጦ ከመመዝገብና በተመዘገበ ይዞታ ላይ አገልግሎት ከመስጠት ውጪ መብት መፍጠር፣ ማስቀረት፣ መቀነስ፣ መጨመር፣ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡ ይህም ሲባል ይዞታን መስጠት ወይም ማስቀረት በሌላ የሕግ ሥርአት ለምሳሌ በሊዝ ሕጉ የሚረጋገጥ ጉዳይ ነው እንደማለት ነው።
 የአካታችነት መርህ፡- የከተማ መሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ማረጋገጥ፣ ምዝገባና አገልግሎት አሰጣጥ ሥራ በሚተገበርበት ወቅት ኅብረተሰቡንና የኅብረተሰቡን የተለያዩ አካላት ተሳታፊነት ባረጋገጠ መልኩ መሆን አለበት።
 መሰረቱ ቀድሞ የተረጋገጠ ይዞታ ስለመሆኑ፡- የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ የሚከናወነው ከፍ ብሎ እንደቀረበው አግባብነት ባለው ሕጋዊ አሰራር መሰረት ቀደም ብሎ በተረጋገጡና በተመዘገቡ ይዞታዎች ላይ ነው፡፡
 አዋጁ የቀደሙ ሰነዶች ላይ ተፈፃሚ ስለመሆኑ፡- ይህ አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት በቀደመው ሕግ ተረጋግጠው በተመዘገቡ ይዞታዎች ላይ የሚገኝ መሬት ነክ ንብረት ይህ አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ በኃላ ከይዞታው ጋር በማስተሳሰር መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
 ቴክኖሎጂያዊ አሰራር፡- የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት የሚመዘገብበትና አገልግሎት የሚሰጥበት አገራዊ የካዳስተራል ሥርአት (Cadastral System) እና ሌሎች ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ መሆን እንዳባቸው አስቀምጧል።

የአዋጁ አስፈላጊነትና የያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች፡-
 ብቸኛ እና ልዩ መለያ ቁጥር (Unique Parcel Identification Code): ለእያንዳንዱ የከተማ መሬት ይዞታ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ፣ የማይደገምና ልዩ መለያ ኮድ እንዲሰጠው ይደነግጋል። ይህም መሬትን በቀላሉ ለመለየትና መረጃን ለማደራጀት ይረዳል።
 የካዳስተር ሥርአት (Legal Cadaster): "ካዳስተር" የሚለው ፅንሰ-ሀሳብ በአዋጁ አንቀፅ 2(10) ስር “የይዞታውን የገጸ-ምድር መረጃ የያዘ ማለትም የመሬት ይዞታውን ስፋት፣ አዋሳኝ ድንበሮች፣ የመሬቱ መገኛ አካባቢን፣ የይዞታውን ወርድና ርዝመት እንዲሁም የቁራሽ መሬቱን እና መሬት ነክ ንብረቱን የካዳስተር ካርታ አካቶ የያዘ የይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት መረጃ ማሰባሰቢያና ማደራጃ ሥርአት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይህም በአጭሩ የመሬቱን ወሰን፣ ስፋት፣ የመሬቱን አቀማመጥ (Topography) እና ካርታን ያካተተ የአንድ ውስን መሬት ዝርዝር መረጃ መያዝን ይመለከታል።
 የመብት ማረጋገጥና ምዝገባ (Systematic Adjudication and Registration): አዋጁ አዲስ መብትን ከመፍጠር ይልቅ በነባር ሕጎች (በሊዝ ወይም በነባር ይዞታነት) የተገኙ መብቶችን በሥርአት የማጣራትና የመመዝገብ ሂደትን ይከተላል። ይህ ሂደት በዚህ ጽሁፍ እንደተገለጸው ከከተማ መሬት ጋር በተያያዙ አስተዳደራዊና የፍርድ ሂደቶች ላይ ቀልጣፋና ፍትሐዊ ውሳኔ ለማስተላለደፍ የሚረዳ ነው።
 የባለይዞታነት ዋስትና (Tenure Security):- ሌላው መሬትና በመሬት ላይ የሰፈረ ንብረት በትክክል ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም ሰርተፊኬት እንዲሰጥ በማድረግ የባለቤትነት ዋስትናን ያረጋግጣል። በዚህም ማንኛውም የመሬት ይዞታ ምዝገባ ተቃራኒ ማስረጃ አስካልቀረበበት ድረስ ለይዞታው ተጠቃሚነት መብት ዋስትናና በይዞታው ላይ ለተገነባው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የመጨረሻ ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል፡
 የተረጋገጠ ሕጋዊ ሰነድ፡- በመሬት ይዞታ ላይ ያለ መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት መቃወሚያ ሊሆን የሚችለው ከተመዘገበ ብቻ በመሆኑ ሁነኛ የሕግ ማስረጃ በመሆን ያገለግላል፡፡
 ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ: የመሬት መረጃዎች በወረቀት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፈው እንዲያዙ ያስገድዳል።

የከተማ መሬት ምዝገባ ሂደት
አዋጁ ዝርዝር የምዝገባ አፈፃጸምና አተገባበርን አስመልክቶ በሥልታዊ ዘዴ ይዞታን ማረጋገጥ እና በአልፎ አልፎ ዘዴ የመሬት ይዞታን ማረጋገጥ ዘዴን አካቷል፡፡ በሥልታዊ ዘዴ ይዞታን ማረጋገጥ ማለት በአንድ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰፈር ውስጥ በሚገኙ ይዞታዎች ላይ የነበረን መብት በመደዳው የማረጋገጥ ዘዴ ሲሆን በአልፎ አልፎ ዘዴ የመሬት ይዞታን ማረጋገጥ ደግሞ በአንድ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሠፈር ውስጥ ቀደም ብሎ የነበረን መብት ለማረጋገጥ በባለይዞታው ጥያቄ መሠረት የሚተገበር የይዞታ መብት ማረጋገጥ ዘዴ እንደሆነ በአዋጁ አንቀፅ 2(13) እና (14) ተመለክቷል፡፡ በዚህ መሰረት በመጀመሪያ ስልታዊ የይዞታ የማረጋገጥ ዘዴ እንዲከናወን በተወሰነበት ቀጠና እና ሰፈር ውስጥ የይዞታ መብት ያለው ማንኛውም ሰው እንዲረጋገጥለት ማመልከት አለበት፡፡ የዚህን ማመልከቻ ዝርዝር ሁኔታና የክፍያ መጠን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በደንብ ይወስናሉ።

በአዋጁ አንቀጽ 14(7) መሠረት የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው የሚተገበረው በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ነው፡፡
 የከተማ ፕላን ተግባራዊ በሆነበት፣
 ሕገ-ወጥ ይዞታዎችን ሥርዓት የማስያዝ ሥራዎች በተከናወኑበት ወይም እየተከናወኑ
በሚገኙበት፣
 ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሰነድ እንዲያገኙ በተደረገበት ወይም ሰነድ እንዲያገኙ እየተደረገ
ባለበት፣
 የከተማው የመሬት አስተዳደር ተቋም ለእያንዳንዱ የመሬት ይዞታ ቀደም ብሎ የሰጠውን መብት፣ የመዘገበውን ክልከላና ኃላፊነት የሚመለከቱ ማስረጃዎች አደራጅቶ ለመዝጋቢ ተቋም ርክክብ በተፈጸመበት ሁኔታ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በከተሞች የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላንና ኃላፊነትን ለማረጋገጥ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላተ እንዳለባቸው የአዋጁ አንቀፅ 13 በግልፅ ያስቀምጣል።
 የከተማው አስተዳደራዊ ወሰን መስመራዊ ካርታ ተዘጋጅቶለት አስቀድሞ መጽደቅ፣
 የከተማውን አስተዳደራዊ ወሰን ያገናዘበ በሕግ አስገዳጅነት ያለው የከተማ ፕላን ሥልጣን ባለው አካል መጽደቅ እና
 የማረጋገጥ ቅድመ ሁኔታ ሥራዎች የተሟሉ መሆናቸውን እና የይዞታ ማረጋገጥ ሥራን ለማከናወን እንዲያስችል ለማድረግ የምዝገባ ተቋም፣ የመብት ሰጪ፣ የፕላን ተቋማት ኃላፊዎች ወይም የወከሏቸው አካላት አማካኝነት እና እንደስፈላጊነቱ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማካተት ተረጋግጦ መቅረብ እንዳለበት ደንግጓል፡፡

የወንጀል ተጠያቂነት
አዋጁን ለማስፈፀም ሥልጣን የተሰጣቸው አስፈፃሚ አካላት ወይም ማንኛውም ኃላፊነት ያለው ሰው በሕጉ ከተቀመጠው ዓላማ ተቃራኒ በሆነ መንገድ የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀም የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀፅ 53 ይደነግጋል። በዚህም፡-
አዋጅንና በአዋጁ መሠረት የወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን ለማስፈጸም የተመደበ ማንኛውም የመዝጋቢው ወይም የመብት ሰጪ ተቋም ኃላፊ፣ የመሬት ይዞታ መብት መዝጋቢ፣ የመሬት ይዞታ መብት አረጋጋጭ፣ የካዳስተር ቀያሽ፣ ልዩ ፈቃድ የተሰጠው ቀያሽ ወይም ሠራተኛ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም ከወጣው ደንብና መመሪያ ውጪ
 የመሬት ይዞታዎችን የማረጋገጥ ሥራ የሠራ እንደሆነ ከ5 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራትና ከብር 40,000 (አርባ ሺ) እስከ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በሚደርስ መቀጮ
 የመሬት ይዞታን የመዘገበ እና አገልግሎት የሰጠ እንደሆነ ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ከብር 30,000 (ሰላሳ ሺ) እስከ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ) ሊደርስ በሚችል መቀጮ እንዲሁም
 የመሬት ይዞታን በማረገገጥ ሂደት ላይ አገልግሎት የሰጠ እንዲሁም ለይዞታ ማረጋገጥ ተግባር የሚውሉ መሰረታዊ መረጃ እና ምላሾችን በወቅቱ ለሚያረጋግጠው አካል ያላቀረበ ከ5 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እስከ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ) ሊደርስ በሚችል መቀጮ ይቀጣል

በተጨማሪም
 በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሠፈር ለሚሰሩ ሥልታዊ ዘዴ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራዎች ትብብር እንዲያደረግ መጥሪያ ተሰጥቶት ያለበቂ ምክንያት ለመተባበር ፈቃደኛ ያልሆነ፣ እንዲያቀርብ የተጠየቀውን ሰነድ ሳያቀርብ ከቀረ ወይም ወደ ይዞታ ለማስገባት ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት ወይም ከብር 1,000 (አንድ ሺ) እስከ ብር 3,000 (ሶስት ሺ) በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል፡፡
 ሕጋዊነት የሌለው ወይም የሀሰት ማስረጃ በመጠቀም ሆነ ብሎ መዝጋቢ ተቋሙን በማሳሳት ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ጥቅም ያስገኘ ወይም ለማስገኘት የሞከረ ወይም የሌሎች ሰዎችን የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ከብር 40,000 (አርባ ሺ) አስከ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
 በአዋጁ መሠረት በሚደራጁ መዝገቦች ደህንነት ላይ ሥጋት ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በመፍጠር የሕጋዊ ካዳስተር መረጃ መዝገብ እንዲጠፋ ወይም እንዲጎዳ ያደረገ ማንኛውም ሰው
o ወንጀሉ ሆነ ተብሎ የተፈጸመ ሲሆን ከ7 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እስከ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) በሚደርስ መቀጮ
o ወንጀሉ በቸልተኛነት የተፈጸመ ሲሆን ከ3 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 20,000 (ሀያ ሺ) እስከ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሺ) ሊደርስ የሚችል መቀጮ ይቀጣል፡፡
 ማንኛውም አመራር ወይም ባለሞያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት የሚሰሩ ሥራዎችን እንዳይተገበር ሆን ብሎ ያደናቀፈ፣ ያጓተተ በአጠቃላይ የተጣለበትን ኃላፊነት ያልተወጣ ከ6 ወር እስከ 2 አመት በሚደርስ ጽኙ እስራት እና ከብር 5,000 (አምስት ሺ) እስከ ብር 20,000 (ሀያ ሺ) በሚደርስ ገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

ማጠቃለያ
መሬት በአገራችን ወሳኝ ሐብት እንደመሆኑ በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል፣ በአግባቡ እንዲመዘገብና እንዲተዳደር የሚመለከታቸው ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንዲሁም ማኅበረሰቡም የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል።
Source MoJ

11/01/2026

ዲጂታል የታክስ አስተዳደር ሥርዓት

በገቢዎች ሚኒስቴር ተግባራዊ የተደረጉና ለትግበራ እየተዘጋጀ ያለ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓቶች;-

1. ኤሌክትሮኒክ-ታክስ (E-Tax)

ኤሌክትሮኒክስ ታክስ (ኢ-ታክስ) በድረ-ገጽ ታክስን ለማሳወቅ፣ ክፍያን ለማከናወን፣ የዕዳ ነጻ ማረጋገጫ (Tax Clearance) አገልግሎት ለማግኘት፣ የተለያዩ ታክስ ነክ ጉዳዮች ማብራሪያ ለማግኘት እና ግብር ከፋዮች የራሳቸውን የታክስ መረጃ ለማየትና ለማንበብ የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

2. የተቀናጀ የመንግሥት የታክስ አስተዳደር ሥርዓት (SIGTAS)

የተቀናጀና ሁሉንም የታክስ አስተዳደር ሥራዎች ለማከናወን የሚያስችል ሥርዓት ሲሆን ሥርዓቱም ለረጅም ዓመታት ሲያገለግል ቆይቷል።

3. ባዮሜትሪክ ምዝገባ እና ብሄራዊ መታወቂያ ትስስር

ባዮሜትሪክ ሲስተም በተፈጠሯዊ መለያዎች (በጣት አሻራ፣ ዓይን እና በፎቶ ግራፍ) የተደገፈ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መስጫ ሥርዓት ነው፡፡

4. ባለ ፈጣን መላሽ ኮድ (ፈመ ኮድ/QR Code) ወረቀት ደረሰኝ ፖርታል

ደረሰኝ በሻጭና በገዢ መካከል ግብይት መከሰቱን ግብይቱ የተከናወነበትን ቀንና ሰዓት የአቅርቦቱን ዋጋ እንዲሁም ሌሎች የሻጭና የገዢ እንደ አድራሻ እና የመሳሰሉትን መረጃ የሚይዝ ሰነድ ነው፡፡

5. የገቢ ዳታ ዌርሃውስ

የዳታ ዌርሃውስ ሲስተም አሁን በሥራ ላይ ካሉ የተለያዩ ሲስተሞችና የሦስተኛ ወገኖች መረጃ በመሰብሰብ ለታክስ አስተዳደሩ ውሳኔ ደጋፊ የሆኑ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት የሚያስችሉ ሪፖርቶችን ያካተተ ነው።

6. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ሥርዓት

ላለፉት 17 ዓመታት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በዚህም በተለይ በግምት ይወሰን የነበረውን የታክስ ውሳኔ በማስቀረት ግብር ከፋዮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ የታክስ ውሳኔ እንዲደርሳቸው በማድረግ በግብር ከፋዩና በታክስ ሰብሳቢው ተቋም መካከል መተማመንን ከመፍጠሩም በላይ ግብር ከፋዩ ዘመናዊ የሂሳብ መዝገብ እንዲይዝ ከፍተኛ አስተዋጾኦ አበርክቷል፡፡

7. የጥሪ ማዕከል

የጥሪ ማዕከል ህብረተሰቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ጉዳዮች የሚኖራቸውን ማንኛውንም ጥያቄ፣ መረጃና ማብራሪያ በስልክ (8199)፣ በኢ-ሜይል፣ በአጭር መልዕክትና በድረ ገጽ አማካኝነት መጠየቅ እንዲችልና በተመሳሳይ መስመር መልስ እንዲገያኙ የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

8. ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት

ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት ለምተው ወደ ትግበራ እንዲገቡ ዝግጁ የተደረጉ አዳዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ጥቅም ላይ ያለውን የፊሲካል ካሽ ሬጅስተር ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ሊያስተካክል የሚችል ነው፡፡

9. ኤሌክትሮኒክ ክሊራንስ

የኤሌክትሮኒክ ክሊራንስ ሥርዓት ግብር ከፋዮች ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚጠቀሙበትን የታክስ ክሊራንስ ለማግኘት ባሉበት ቦታ ሆነው ጥያቄ የሚያቀርቡበት እና ግዴታቸውን መወጣታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ተገቢውን ክሊራንስ የሚያገኙበት ሥርዓት ነው።

10. ድረ- ገጽ (Website)

የተቋማት ድረ-ገጾች እንደ ተቋማቱ ባህሪ የሚያቀርቡት አገልግሎት እና ትኩረታቸው የሚለያይ ሲሆን አዲስ የለማው የገቢዎች ሚኒስቴር ድረ-ገጽም ይህንን መሰረት ያደረገ ነው።
Source MoR

08/01/2026

በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገባቸው ጉዳዮች
መግቢያ
ግብር የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን መንግሥትም የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት በማረጋገጥ ረገድ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልገውን ገቢ የሚያገኝበት ምንጭ ነው። የግብር ሕግ እንደማንኛውም ሌሎች ሕጎች ሁሉ ማኅበረሰቡ የደረሰበትን ሁለንተናዊ የእድገት ደረጃ ከግምት ባስገባ መልኩ ተቀርፆ በሥራ ላይ የሚውል እንደመሆኑ በየወቅቱ የሚኖሩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ለውጦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሻሻል ይኖርበታል።
የአገራችንም የግብር ሥርአት በየጊዜው የሚከሰቱ ለውጦችን ከግምት ባስገባ መልኩ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል። በቅርቡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው የግብር ሕግ አይነቶች አንዱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 ሲሆን በአዋጅ ቁጥር1395/2017 ማሻሻያ ተደርጎበታል። በዚህ አጭር ጽሑፍ የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአጭሩ እንዳስሳለን።
የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች
 ከመቀጠር፣ ከቤት ኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር
ከመቀጠር፣ ከኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር ምጣኔዎች በማሻሻያ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡ ይኸውም በቀድሞ የገቢ ግብር አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 11) ተደንግጎ የነበረው ከግብር ነፃ ከሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ወርሃዊ ገቢ መጠን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የግብር ምጣኔ ድረስ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ በቀድሞው ሕግ ከገቢ ግብር ነፃ የሆነው እስከ ብር ስድስት መቶ (600) ያለ ገቢ የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(6) መሠረት እስከ ብር ሁለት ሺ (2,000) ድረስ ያለ ከመቀጠር የሚገኝ ወርሀዊ ገቢ ከግብር ነፃ እንዲሆን ተደርጓል። በተጨማሪም ከፍተኛው የማስከፈያ ምጣኔ የሆነው 35% ከአስር ሺ ዘጠኝ መቶ (10,900) ብር ወርሃዊ ገቢ ጀምሮ ይጣል የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ ግን ይሄው የ35% ምጣኔ ከአስራ አራት ሺ (14,000) ብር በላይ ወርሀዊ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ይሆናል።
ሌላው በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገው በኪራይ እና ንግድ ሥራ ገቢዎች ምጣኔ ላይ ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ (አንቀፅ 14(2)) እና 19(2) መሠረት እስከ ብር ሰባት ሺ ሁለት መቶ (7,200) ድረስ ያሉ አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢዎች ከግብር ነፃ የነበሩ ሲሆን ይኸው መጠን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(😎 እና 2(10) መሠረት ማስተካከያ ተደርጎበት ወደ ብር ሃያ አራት ሺ (24,000) አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢ ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከፍተኛው የ35% የግብር ምጣኔ የሚጣልበትን የኪራይ እና የንግድ ሥራ የገቢ መጠን በተመለከተ በማሻሻያ አዋጁ በቀድሞ አዋጅ ከነበረው ከብር አንድ መቶ ሰላሳ ሺ ስምንት መቶ (130,800) በላይ ከፍ በማድረግ ከብር አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺ (168,000) በላይ አመታዊ ገቢ ላይ እንዲሆን ተደርጓል።
ሌላኛው ከግብር ምጣኔ አንፃር ለውጥ የተደረገው ከዕድል ሙከራ በሚገኙ ገቢዎች ላይ ነው። ቀደም ሲል ከዕድል ሙከራዎች ገቢ ያገኘ ሰው የገቢውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 57(1)፤ በማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(22) መሰረት ከዕድል ጨዋታ ገቢ ያገኘ ሰው ከገቢው ላይ 20% (ሃያ በመቶ) ግብር መክፈል ይጠበቅበታል። ነገር ግን ይሄ የግብር መጠን በዕድል ሙከራ ከአንድ ሺ ብር በታች ባገኘ ሰው ላይ አይጣልም።
 የግብር ከፋይ ደረጃዎች
ሌላኛው በማሻሻያ አዋጁ ለውጥ ከተደረገባቸው ነጥቦች መካከል አንዱ የግብር ከፋይ ደረጃዎችን የተመለከተው ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀፅ 3 መሠረት የደረጃ “ሀ”፣ “ለ” እና “ሐ” በሚል በሶስት የግብር ከፋይ ደረጃዎች ከፋፍሎ ያስቀመጣቸው ሲሆን ክፍፍሉም ጠቅላላ አመታዊ ገቢን ታሳቢ ያረገ ነው። በዚህም መሰረት ድርጅት ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢው ብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው በደረጃ “ሀ” ስር የሚመደብ ሲሆን፣ ከብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) በታች እና ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በላይ አመታዊ ገቢ ያላቸው (ድርጅቶችን ሳይጨምር) ደግሞ ደረጃ “ለ” ስር ይጠቃለላሉ። ድርጅትን ሳይጨምር አመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በታች የሆኑ ግብር ከፋዮች በደረጃ “ሐ” ስር ይመደባሉ።
ነገር ግን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(2) መሠረት በሶስት ደረጃዎች የመክፈሉ ሂደት ቀርቶ የግብር ከፋዮች ደረጃ “ሀ” እና “ለ” በሚሉ ሁለት ደረጃዎች ብቻ እንዲከፈል ተደርጓል። ከአመታዊ ገቢ ምጣኔውም አንፃር ቀደም ሲል የነበረው እንዲሻሻል ተደርጎ በደረጃ “ሀ” ስር የሚወድቁ ግብር ከፋዮች ድርጅቶች ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢያቸው ከብር ሁለት ሚሊዮን (2,000,000) እና በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች ሲሆኑ ከዚህ መጠን በታች የሆነ ጠቅላላ አመታዊ ገቢ ያላቸው ሰዎች (ድርጅቶችን ሳይጨምር) በደረጃ “ለ” ስር እንዲመደቡ ተደርጓል።
 የገቢ ምንጭ (የታክስ መሰረት) ማስፋት
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁ በቀድሞው አዋጅ ያልነበረ አዲስ የግብር ምንጭ አካቶ የወጣ ነው። ይኸውም በማሻሻያ አዋጁ ላይ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢም ግብር እንደሚከፈልበት በግልፅ ተደንግጓል። በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ አንቀፅ 2(1) መሰረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግልቶችን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን (በበይነ መረብ) መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም በገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው። ይህም ከማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣ ከምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣ ከአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች፣ ከደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ ከገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ (ክራውድ ፈንዲንግ)፣ ከአባልነት ክፍያዎች፣ ከዲጂታል ወይም ከአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣ ከማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግልቶች እና ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎችን ያካትታል፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ነዋሪ ወይም ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የዲጂታል አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ 5% የማይበልጥ የገቢ ግብር እንደሚከፍል በአዋጅ አንቀጽ 2(17 ተደንግጓል)። የዲጂታል አገልግሎት ምንነትን በተመለከተ፣ የማስከፈያ ምጣኔ፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ሌሎች ተያያዥነት ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ የሚንስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት የሚወሰን ስለመሆኑ በማሻሻያ አዋጁ ተጠቅሷል።
ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራው ትርፍ ለማግኘት ታስቦ በመደበኛነት የሚከናወን ከሆነ፣ ፈጣሪው ድርጅት ከሆነ፣ የሂሳብ መዝገብ የሚያዝ ከሆነ ወይም ከንግድ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ተቀናሽ የሚደረጉለት ከሆነ የሚገኘው ገቢ እንደ ንግድ ሥራ ገቢ እንደሚቆጠር ከማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(11) መረዳ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጭ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኙ ገቢዎች እንደሌላ ገቢ ተቆጥረው በአዋጁ ሠንጠረዥ “መ” መሠረት ግብር የሚጣልባው ሲሆን ዝርዝር አፈፃፀሙም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ መሠረት የሚወሰን ይሆናል። ስለሆነም የዲጂታል ይዘት አመንጪዎች እንደማንኛውም ግብር ከፋይ ሁሉ መለያ ቁጥር የማውጣት፣ ገቢን የማስታወቅ እና ሌሎችም የታክስ ከፋዮች ግዴታዎች ይኖሩባቸዋል ማለት ነው።
 አማራጭ አነስተኛ ግብር
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት ነው። ግብር ከፋዮች ምንም አልሰራንም (ገቢ አላገኘንም) ወይም ስለከሰርን ግብር ልንከፈል አይገባም በማለት ማስታወቅ የተለመደ ነገር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ማናቸውም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ለአመታት በኪሳራ ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ ነው። ይህም ግብር ሳይከፍሉ ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስገንዘበናል። ከዚሁ መነሻ ከግብር ለመሸሽ ኪሳራ የሚያስታውቁ ትክክለኛውን ግብር እንዲከፍሉ፣ በትክክል ኪሳራ ያጋጠማቸው ደግሞ መክሰራቸው ሲረጋገጥ የከፈሉት ግብር እንዲካካስ ለማስቻል ሲባል አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት እንዲካተት ተደርጓል።
አማራጭ አነስተኛ የግብር ምጣኔን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀፅ 2(11) መሠረት ማናቸውም ድርጅት ወይም ሰው ግብር በሚወሰንበት የግብር አመት ከሁሉም የንግድ ሥራ የገቢ ምንጮች ባገኘው ትርፍ ላይ ሊከፍል የሚገባው ግብር በዚሁ የግብር አመት ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ2.5% (ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) በታች ከሆነ በአዋጁ በተመለከተው የማስከፈያ ምጣኔ መሠረት አማራጭ አነስተኛ ግብር መክፈል እንደሚኖርበት ተደንግጓል።
 በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ላይ የተደረገ ገደብ
ሌላኛው የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ይዞት የመጣው ጉዳይ በጥሬ ገንዘቦች የሚደረጉ ግብይቶች ላይ ገደብ ማበጀት ነው። በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ስለግብር ከፋዩ ግብይት በቂ መረጃ እንዳይኖር በማድረግ ለታክስ መሰወር ድርጊት በር ከፋች ይሆናል። ይህንንም ለመቀነስ እንዲያስችል ማናቸውም ግብር ከፋይ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ ቼክ፣ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ የባንክ ድራፍት፣ ከባንክ ሂሳብ ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ በማስተላለፍ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጣቸው የክፍያ መፈጸሚያ መንገዶች ካልሆነ በስተቀር በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ሰው ጋር በተደረገ ጠቅላላ ግብይት ወይም ከአንድ ግብይት ጋር በተያያዘ የሚፈጸም ክፍያ ወይም ከአንድ ሰው ጋር ከተፈጸመ አንድ ግብይት ወይም ተግባር ጋር የተያያዘ ክፍያ/ግብይቶች ከሃምሳ ሺ (50,000) ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ መቀበል አይቻልም። ነገር ግን ይህ ገደብ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በተለዩ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ከማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(28) ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ማሻሻያዎች ጨምሮ ገቢ ስለሚጣመርበት ሁኔታ፣ ግብር ቀደም ብሎ የሚከፈልበትን አሰራር እና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካቶ ወደ ሥራ የገባ ሕግ ነው። ምንጭ የፍትሕ ሚኒስቴር

06/01/2026

Tewedaj Mehammed (Admin) wish you a happy Ethiopian merry Christmas!!!

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ህግ ተገዢነትን ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የአሰራር ስርአት በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክስሳይዝ ታክስ ግዴታቸውን ባልተወጡ ድርጅቶች ላይ ...
02/01/2026

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ህግ ተገዢነትን ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የአሰራር ስርአት በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክስሳይዝ ታክስ ግዴታቸውን ባልተወጡ ድርጅቶች ላይ የማምረቻ ቦታን ለጊዜው ስለማሽግ፣ ፈቃድ ስለማገድ እና ስለመሰረዝ በተመለከተ የተዘጋጀውን የአሰራር እና የአፈጻጸም ማንዋል ተግባራዊ እንዲሆን በመወሰን በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ልኳል።

የአሰራር ማንዋሉ ተግባራዊ እንዲደረግና ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው በጉዳዩ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስተያየት ከሰጠበት በኋላ ነው።

ዳይሬክቶሬቱ በሰጠው አስተያየት ማንዋሉ "አዋጁን መሰረት ያደረገና በአዋጁ ላይ ከተቀመጠዉ መብትና ግዴታ ዉጭ በአዲስ መልክ ያካተተዉ ስልጣንና ሀላፊነት የሌለ በመሆኑ ማንዋሉን በማጽደቅ ወደስራ መግባት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን" ብሏል።

ዳይክቶሬቱ ማንዋሉ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነው የተዘጋጀዉ ረቂቅ የአሰራር ስርአት ማንዋል በኤክሳይስ ታክስ አዋጁ ላይ የተቀመጡ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጡ ዝርዝር ተግባራትና ሀላፊነትን:-

• በተለይም ኤክሳይስ ታክሱን በማያከብሩ አምራች ፋብሪካዎችን ለጊዜዉ የሚታገዱበትን ስነስርአት፣

•ፈቃዳቸዉ ስለሚታገድበትና ስለሚሰረዝበት ሁኔታ ቀለል ባለ መልኩ ለፈጻሚዎቹ እንዲረዱት ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ

• አዋጁን መሰረት ያደረገና በአዋጁ ላይ ከተቀመጠዉ መብትና ግዴታ ዉጭ በአዲስ መልክ ያካተተዉ ስልጣንና ሀላፊነት የሌለ በመሆኑ ምክንያት መሆኑን በአስረጂነት ጠቅሷል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ታህሳስ 15/2018 ዓም በጻፈው መመሪያው የተዘጋጀው የአሰራር ማንዋል ተግባራዊ እንዲደረግና ስራ ላይ እንዲውል ያሳሰበ ሲሆን አምራች ፋብሪካዎች እና የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እንዲያውቁት ብሏል።

የንግድ ድርጅት ለጊዜዉ ከሚታሸግበት ምክንያቶች አንዱ አንድ ታክስ ከፋይ በግብር ህግ መሰረት የሚፈለግበትን ሰነድ ሳይዝ ሲቀር ወይም ታክሱን በመክፈያ ጊዜዉ ሳይከፍል ሲቀር ሲሆን የግብር ህግ ማለት የኤክሳይስ ታክስ አዋጁን የሚጨምር መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በማብራሪያው ላይ ጠቅሷል።

በእነዚህም መሰረት የኤክሳይስ ታክስ አዋጁ ግዴታቸውን ባልተወጡ ድርጅቶች ላይ የማምረቻ ቦታን ለጊዜው ማሽግ፣ ፈቃድ ማገድ እና መሰረዝ ያሉ ውክልናዎችን ለገቢዎች ሚኒስቴር የሚሰጥ መሆኑን ይገልጻል።

Source:- tikvahethiopia

Address

6killo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Best Law Family posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category