ፍቃዱ ሞላ የህግ ቢሮ Fekadu Molla Law Office

ፍቃዱ ሞላ የህግ ቢሮ Fekadu Molla Law Office ከሰማይ በታች ህግ የማይመለከተው ነገር የለም።

06/08/2026
በዳኛች ዕረፍት ጊዜ በተረኛ ችሎት የሚሰሩ ስራዎች
04/08/2026

በዳኛች ዕረፍት ጊዜ በተረኛ ችሎት የሚሰሩ ስራዎች

⚖️  የመዝገብ ቁጥር፦ 234500 ⚖️ ወደ ከተማ ተካልሎ ነገር ግን የከተማ ፕላን ባልተሰራበተ አከባቢ የተሰራን ቤት አስተዳደሩ ካፈረሰ የሁከት ተግባር ነው።አንድ የክፍለ ከተማ አስተዳደር ...
01/05/2026

⚖️ የመዝገብ ቁጥር፦ 234500 ⚖️
ወደ ከተማ ተካልሎ ነገር ግን የከተማ ፕላን ባልተሰራበተ አከባቢ የተሰራን ቤት አስተዳደሩ ካፈረሰ የሁከት ተግባር ነው።

አንድ የክፍለ ከተማ አስተዳደር "የግንባታ ፈቃድ የላችሁም፣ ግንባታው ህገ-ወጥ ነው" በሚል የዜጎችን ቤት ለማፍረስ ሙከራ ያደርጋል። ይሁን እንጂ ይዞታው ገና ከገጠር መሬት አስተዳደር ወደ ከተማ መሬት ሙሉ በሙሉ ያልተሸጋገረ እና በገጠር ይዞታነት የሚታወቅ ነበር።
​የሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ትርጉም
ፍርድ ቤቱ የክፍለ ከተማውን ክርክር ውድቅ በማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች አፅንቷል፦
​✅ ህጉ ምን ይላል? መሬቱ በገጠር ይዞታነት እስከታወቀ ድረስ፣ የከተማ ግንባታ አዋጅ (ቁጥር 624/2001) በዝምታ ተፈፃሚ አይሆንም።
✅ መብታችሁ፡ አንድ አርሶ አደር ወይም የገጠር መሬት ባለይዞታ ለራሱና ለቤተሰቡ መጠለያ የሚሆን ቤት በይዞታው ላይ የመስራት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
✅ የአስተዳደሩ ስልጣን ገደብ፡ መሬቱ በይፋ ወደ ከተማ መሬት አስተዳደር ሳይዞር እና የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ሳይዘጋጅለት፣ አስተዳደሩ "ፈቃድ የላችሁም" በሚል የግንባታ እገዳ ወይም ማፍረስ አይችልም። እንዲህ አይነት ተግባር "የሁከት ተግባር" ነዉ ተብሎ ተወስኗል ።

02/04/2026

*****አዋጅ ቁጥር 1410/2018****,
*የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ
----------------------
(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 24፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ረቂቅ ሕጉ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማክበርና ለማስከበር የሕግ የበላይነት በማስፈን የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡

የተቀላጠፈ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እና ልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴን እንዲሁም ለተጎጂዎች ካሣ የሚከፈልበትን አግባብ ያካተተ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ ረቂቅ ሕግ እንደሆነ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ አያይዘው አስረድተዋል፡፡

ረቂቅ ሕጉ ከኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ መርሆች እና እሴቶች እንዲሁም ከወንጀል ህጉ ጋር የተጣጣመና ዘመናዊ በመሆኑ ጠቀሚ እንደሆነ ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል፡፡

ረቂቅ ህጉ በህገ መንግስቱ፣ በወንጀል ሕጉ፣ ዓለም አቀፍ ህጎች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች የተረጋገጡ ልዩ ትኩረት ለሚያሻቸው ለሴቶች፣ ህፃናት እና አካል ጉዳተኞች የተሰጣቸውን መብቶች ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ረጅም ጊዜ የቆየና የዘገየ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ወቅቱን የሚመጥን አዋጅ በመሆኑ የህዝብን የፍትህ ሥርዓቱን ለማስፈን እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

የዜጎችን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲአዊ መብቶችን ለማስከበር እና የፍትህ ሥርዓቱን በማዘመን ወቅቱን ያዋጅ አግልግሎት ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላት አመላክተዋል፡፡፡

በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ በአተገባበር ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ከፍትህ አካላት ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ከምርመራ ሂደት እና ከዲጂታል አሰራሮች ጋር በተያያዘ ዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብትን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላቱ አስገንዝበው፤ በማረሚያ ቤት ቆይተው ፍርድ ቤት ነፃ የሚላቸው ዜጎች የካሳ ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማስቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 አድረጎ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

(በ-መኩሪያ ፈንታ)

Address

Addis Ababa And Wolaytta S**o
Addis Ababa

Telephone

+251945956551

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍቃዱ ሞላ የህግ ቢሮ Fekadu Molla Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category