Deacon Girma

Deacon Girma "ወመኑ መሐሪ ዘከማከ"
"ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ"

በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰነፍና ዋልጌ ሰዎች መኖራቸው መቼም የማናስተባብለው ሐቅ ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ግን አይኮረፍም!የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ ...
08/11/2025

በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰነፍና ዋልጌ ሰዎች መኖራቸው መቼም የማናስተባብለው ሐቅ ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ግን አይኮረፍም!
የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ የምእመናን ሕይወት የማይገዳቸው፤ ስለደመወዛቸው ካልሆነ በቀር ስለምእመናን መብዛትና ስለዘለዓለም ሕይወታቸው የማያስቡ ምንደኞች ቢበዙባትም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ተናግረው የሚያናግሩ፤ ለሰው ስሜት የማይጠነቀቁ፤ አማረልኝ ብለው እንዳመጣላቸው የሚያወሩ፤ ንግግራቸው ቤተ ክርስቲያንንና አገልግሎቱን ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ የማይፈልጉ፤ ሥራዬ ብለው ምእመናን እንዲበተኑ የሚተጉ፤ ከሩቅ የሚመልሱ . . . ሰነፍ እረኞች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ከቤተ ክርስቲያን ወጭት እያጠቀሱ ግን ደግሞ ምእመናንን የሚያሳፍሩ፤ የሚያስቆጡ፤ የሚያስከፉና የሚገፉ . . . ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ከዘመኑ ጋር የማይሔዱ፤ የምእመናን ሁለንተናዊ እድገትና መሻሻል ግድ የማይሰጣቸው፤ ምንም ርዕይ የሌላቸው፤ ዛሬ ብቻ እንጂ ነገ የማያሳስባቸውና የማይገዳቸው ብዙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
“የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ብሒል እንጀራ የሚበሉበትን መሶብ የሚገለብጡ፤ ወርቅ ያለበሰቻቸውን ቤተ ክርስቲያን የሚያራቁቱ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ነገዋ ግድ የማይሰጣቸው ብዙ “አገልጋዮች” ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ እናታችን ናትና! በእናት እንዴት ይኮረፋል!!!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ የነውራችን ክዳን፤ የዕርቃናችንም ልብስ ናትና!!!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ ፍጽምት የምትሆን የክርስቶስ አካሉ ናትና!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም የአገልጋዮች ድካም የክርስቶስን ጸጋ አያስቀርብንምና፤ መስዋዕቱ እንዳያርግ፤ ምሥጢራቱም እንዳይፈጸሙ አያግዳቸውምና!!!

በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . .

በኤዶም ኃይሉ

08/11/2025
06/11/2025

🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 👇 👇 👇 https://bit.ly/3C2YHGpአዲስ ዝማሬ " ምስክሩ ነኝ " ዘማሪ ዲያቆን ግርማ ንጉሤ

 "አዳምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱ...
06/11/2025


"አዳምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"


“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡”
ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››


‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ››


‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››


‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡››
_ዘቂሳሪያ

 የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ በዓል የሚከበርበት ታላቅ ዕለት ነው:-መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድ...
05/11/2025


የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ በዓል የሚከበርበት ታላቅ ዕለት ነው:-መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?-ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው-ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር-በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት-በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ-አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ-በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልን ዛሬን የበዓሉ መታሰቢይ በሁሉም የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይከበራል።

ስለ ሰው ልጆች ስጋው ቆርሶ ደሙን አፍስሶ መድኃኒት የሆነን የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው ቸሩ መድኃኔዓለም ዳግም ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ሲመጣ በቀኙ ከሚቆሙት ጋር ይደምረን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን አሜን።

Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii    🙏 Du'uun ni gaha 🙏Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii    🙏 Du'uun ni gaha 🙏
04/11/2025

Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii
🙏 Du'uun ni gaha 🙏
Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii
🙏 Du'uun ni gaha 🙏

04/11/2025

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው:: ከቀናት በፊት የተገደሉትን ተናግረን ሳናበቃ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ አምስት እንደተገደሉ እየሰማን ነው::

ሰሞኑን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሔሮድስ ስላሳደዳት እመቤታችን "ሰቆቃወ ድንግል" እያልን እያዘንን ነው:: ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም:: የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው:: የቦታ ለውጥ እንጂ በእነርሱ የደረሰው በእኛም ሊደርስ ይችላል::

ቤተ ክርስቲያን ምሕላ እንድታውጅ ፣ ለተሠዉት ተገቢውን ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርግ እንጠብቃለን:: ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ቦታ የንጹሐን ደም ዳግመኛ እንዳይፈስስ እንደ ራሔል ዕንባዋን የምትረጭበት ጊዜ አሁን ነው::

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትኩረት ያልሠጠውን ችግር ሌላ አካል ሊጨነቅበት አይችልም:: ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅርዋ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት የምትሠራበት ጊዜም አሁን ነው:: ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ ሌላ ቀን ቢጣራ የማይሰማውን ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል:: ሐዋርያዊትዋ ቤተ ክርስቲያንም በክህነት የማትመራ የመሆን አደጋ ይገጥማታል:: ክህነት ከሌለ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ምሥጢራትም የሉም::

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ይህንን ጊዜ ለመካሰስ ፣ አባቶችን ለመሳደብ ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን ለጸሎት ለምሕላና ለሰብአዊ ሥራና መሬት ላይ ቢወርዱ ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት ብናደርገው የተሻለ ነገር ማምጣት እንችላለን::

የሌላ እምነት ተከታዮች ሆነው ይህ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለው ጉዳዩን በተቋምም በግልም ያወገዙ ሰዎችን እናከብራለን:: "ይበላችሁ" ብለው የተሳለቁትን እና በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩን ደግሞ እውነተኛ ማንነታቸውን ስላሳዩን እያመሰገንን "አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ “እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ፡” ያሉአትን" ብለን ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል:: መዝ. 137:7



  እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይኾን፥ እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።
04/11/2025

እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይኾን፥ እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን”   ሮሜ 8፥ 36   የህጻናቱን እና የኦርቶዶክሳዊያኑን ደም እግዚአብሔር ይበቀላልና ለሞቱት ሰማዕታት ገነትን በተአምራት ለ...
03/11/2025

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” ሮሜ 8፥ 36
የህጻናቱን እና የኦርቶዶክሳዊያኑን ደም እግዚአብሔር ይበቀላልና ለሞቱት ሰማዕታት ገነትን በተአምራት ለተረፉት ጽናትን በሐዘን ለተጎዱት መጽናናትን እግዚአብሔር ያድልልን😭😭😭

ወረብትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ/፪/ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/ትርጉም፦ማርያም ! የዓለም ፀሓይ የሆነ ክርስቶስን እና ጽጌ የተባልሽ አንቺን የወ...
01/11/2025

ወረብ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

ትርጉም፦
ማርያም ! የዓለም ፀሓይ የሆነ ክርስቶስን እና ጽጌ የተባልሽ አንቺን የወለደች እናትሽ ሦስተኛዋን እና አራተኛዋን ቀን ትመስላለች ።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ አርሲ...
30/10/2025

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ

የተሰጠ መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በጉና፣ በመርቲ፤ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ጥቅምት 14 ለ15 ቀን 2018 ዓ.ም በጉናና መርቲ ወረዳዎች 17 ክርስቲያኖች፣ ጥቅምት 17 ለ18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸርካ ወረዳ 3 ክርስቲያኖች እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 5 ክርስቲያኖች በድምሩ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ብቻ 25 ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አገራችንና ምድራችን ብለው በሰላም በተኙበት በድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉና ግድያውም ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መሆኑን የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የላከውን ሪፖርት ቋሚ ሲኖዶሱ የተመለከተው በከባድና ጥልቅ የኃዘን ስሜት ነው ፡፡

በመሆኑም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት እንዲህ ዓይነቱ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም የቆየው በተደጋጋሚ እንደመሆኑ መጠን እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በቅዱሳት መጻሕፍት ሆነ በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ በነጻነት የማምለክ ሕገ መንግሥታዊ መብትን የሚጋፋ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር መንፈሳዊ ዕሴቶቻችንን የሚያጠፋ፣ ክብረ ነክና ሊወገዝ የሚገባው ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል።

በመሆኑም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላትም ይህን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር በጽኑ በማውገዝና በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና የእምነት ነጻነት መብትን እንዲያስከብሩልንና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን ሕገ ወጥ ግለሰቦች ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪም በቀጣይ እንዲህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ ተግባር እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በመጨረሻም በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ከፍተኛ ኃዘንበድጋሚ እየገለጽን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን በመመኘት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችንም እግዚአብሐር አምላክ ዕረፍተ ነፍስን እንዲያድልልን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትፀልያለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ቋሚ ሲኖዶስ

ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

Address

Ortodoks Tewahido Zemari
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deacon Girma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Deacon Girma:

Share

Category