እንዳላማው አለልኝ የህግ ቢሮ

እንዳላማው አለልኝ የህግ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እንዳላማው አለልኝ የህግ ቢሮ, Legal Service, Addis Ababa.

ጠበቃና የህግ አማካሪ እንዳላማው አለልኝ በፍትህ ሚኒስቴር በዐቃቤ-ህግነት ከዚያም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዳኝነት አገልግሏል። በተመ የሰፈራ ፕሮገራም/UN-Habitat/ የህግ ኤክስፐርት ሆኖ ሰርቷል። በህግ የመጀመሪያና 2ኛ ዲግሪ አለው። በጽንሰ-ሃሳብና በልምድ በዳበረ የህግ እውቀትና ክህሎት በመታገዝም በአሁኑ ሰዓት የራሱን ቢሮ ከፍቶ በጠበቃነት እና የህግ አማካሪነት እየሰራ ይገኛል።

08/05/2026
28/04/2026

አስቸኳይ የጥንቃቄ ማሳሰቢያ
************************************
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ በበላይነት የመቆጣጠር እና ኢንቨስተሮችን ከሕገ-ወጥ አሰራር የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።

ባለሥልጣኑ ባደረገው ክትትል ባይራ አክሲዮን ማህበር "የውሃ ፋብሪካ አቋቁማለሁ” ወይም ”አርባምንጭ ውሃ" በሚል በባለሥልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለሽያጭ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ እና ከባለሥልጣኑ ማግኘት የሚገባውን የቅድመ-ማስታወቂያ ፈቃድ ሳያገኝ በተለያዩ ሚዲያዎች ማህበራዊ ሚድያን ጨምሮ የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ላይ የሚገኝ መሆኑን ደርሶበታል።

በባለስልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለሽያጭ የማቅረብ ድርጊት በሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለሕዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 አንቀፅ 4 መሠረት ሙሉ በሙሉ የተከለከለ እና በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 አንቀፅ 106 መሰረት በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ሲሆን የባለስልጣኑን ይሁንታ ሳያገኙ የሰነደ ሙአለ ንዋዮች ሽያጭን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችንም ማሰራጨት በመመሪያ ቁጥር 1030/2017 አንቀጽ 53 መሰረት የተከለከለ እና የሚያስቀጣ ተግባር ነው ።

በመሆኑም በአክስዮን ማህበሩ ላይ የተጀመረው አስተዳደራዊ ምርመራ የሚቀጥል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ህብረተሰቡ አክስዮን ማህበሩ አክስዮኖቹን በባለስልጣኑ ያላስመዘገበ እና የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ለማሰራጨትም የባለስልጣኑን ይሁንታ ያላገኘ መሆኑን ተገንዝቦ ያልተመዘገቡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች/አክስዮኖችን ከመግዛት እንዲቆጠብ እና ለማንኛውም የሽያጭ ወኪልም ሆነ ለአክስዮን ማህበሩ ክፍያ እንዳይፈጽም ባለሥልጣኑ በጥብቅ ያሳስባል።

ባለሥልጣኑ የኢንቨስተሮችን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚወስደውን ቁጥጥር አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ሕዝቡም መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት ከባለሥልጣኑ ጋር እንዲተባበር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ጥቆማ ለመስጠት ስልክ +251115576123
ኢሜይል፦ [email protected]

13/04/2026

ቶርቸር? FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር

09/04/2026
15/02/2026

Celebrating my 3rd year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

25/01/2026

ጋዜጣዊ መግለጫ | ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ዋጋን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251912771896

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እንዳላማው አለልኝ የህግ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to እንዳላማው አለልኝ የህግ ቢሮ:

Share

Category