Talk Laws Ethiopia

Talk Laws Ethiopia ⚖️ 24 ሰዓት የሕግ አገልግሎት⚖️

13/11/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Abdi Hirpassa, Wondiye Zewude, Ferej Hassen Areshid, Abe Kebe, Tagesse Chamiso, Hijezu Hamdino, Kaleb Love, Mohamed Ahmed, Welldisha Gmrskell

28/09/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Chishu Cheno, Shegaye Mengstie, Maos Maos, Tesfaye Tadese, Fayyeeraa Ť Gabbisaa, Abrha Gebru, Tale Mamo, Chankalo Chada

24/01/2024


ሀ. የመዳረግ መብት -
ዋሱ ስለዋናው ባለዕዳ ሆኖ የከፈለውን ተገቢ የሆኑ ክፍያዎች ሁሉ በባለገንዘቡ መብት ተዳረጊ ሆኖ ባለዕዳውን ሊጠይቀው ይችላል፡፡ ይህ ማለት ዋሱ ለአበዳሪው የከፈለውን ገንዘብ በአበዳሪው ቦታ ሆኖ ከባለዕዳው ሊጠይቅ ይችላል።
ለ. ከዋናው ባለዕዳ ጋር ተከራከር የማለት መብት ፡- ይህ የተራ ዋስትና ግዴታ ያለበት ሰው የሚኖረው መብት ነው፡፡ ዋሱ እንደተከሰሰ ወዲያውኑ ከዋናው ባለዕዳ ጋር ተከራከር በማለት ባለገንዘቡን የመከራከር መብት
ይኖረዋል፡፡
ሐ. ባለዕዳው ሊያነሳቸው የሚችላውን መቃወሚያዎች ማንሳት፡- ከግዴታው ዓይነት የተነሳ እንዲቀሩ ካልሆነ በቀር (ለምሳሌ ውሉ የተፈፀመው በስህተት መሆኑን ወይም ባለዕዳው ለአቅመ-አዳም ያልደረሰ መሆኑን እያወቀ የገባበት ግዴታ) መሆኑን እና ሌሎች ባለዕዳው ሊያነሳቸው የሚችላቸውን መቃወሚያዎች እያነሳ ሊከራከርባቸው ይቻላል፡፡

  (Period of Limitation)     (በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ውስጥ የተቀመጡ አንዳንድ የይርጋ ጊዜያት)👉አንቀፅ 33 - መሰረት አንድ ሠራተኛ በአንቀጽ 32(1) የተጠቀሱትንና የስራ...
13/09/2023

(Period of Limitation)
(በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ውስጥ የተቀመጡ አንዳንድ የይርጋ ጊዜያት)
👉አንቀፅ 33 - መሰረት አንድ ሠራተኛ በአንቀጽ 32(1) የተጠቀሱትንና የስራ ውሉን ያለ ማስጠንቀቂያ የሚያቋርጥባቸውን ምክንያቶች (ሰብአዊ ክብርና ሞራል የሚነኩ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ለደህንነትና ጤና የሚያሰጉ) እና ሌሎች ነገሮች ተፈፅሞብኛል በማለት የሥራ ውሉን ለማቋረጥ ያለው መብት ድርጊቱ ከተፈጸመ ወይም ሁኔታው ከተወገደ የሥራ ቀናት በኋላ በይርጋ ይታገዳል፡፡
👉አንቀጽ 163(1) በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የመነጨ ማንኛውም ክስ የጊዜ ገደቡ በአዋጁ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሕግ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ እስከ ድረስ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
(2) ሠራተኛው የሥራ ውሉ ከሕግ ውጭ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውሉ በተቋረጠ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
(3) ሠራተኛው የሚያቀርበው የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የሌሎች ክፍያዎች ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
(4) የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛውም ሆነ በአሠሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውሉ በተቋረጠ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
👉እንዲሁም በአንቀጽ 189 መሰረት በአዋጁ የተጠቀሰው ማንኛውም ጥፋት ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ካለፈው ክስ ማቅረብ አይቻልም

🌻🌻     እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ    🌻🌻
11/09/2023

🌻🌻 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ 🌻🌻

 /2011_እና_አዳዲስ_ጉዳዮችአዲሱ አዋጅ የተለያዩ አዳዲስ ሀሳቦችን አካቶ ብቅ ብሏል፡፡ 1ኛ. ከዚህ ቀደም በነበረው በተሻረው ሕግ መሠረት   (Recruitment Process) ላይ አዋጁ ...
11/09/2023

/2011_እና_አዳዲስ_ጉዳዮች
አዲሱ አዋጅ የተለያዩ አዳዲስ ሀሳቦችን አካቶ ብቅ ብሏል፡፡
1ኛ. ከዚህ ቀደም በነበረው በተሻረው ሕግ መሠረት (Recruitment Process) ላይ አዋጁ ተፈጻሚ እንዲሆን አልተደረገም ነበር፡፡ በአዲሱ አዋጅ የአዋጁን የተፈጻሚነት ወሰን በአሠሪና ሠራተኛ በቅጥር ላይ በተመሰረተ ግንኙነትና በቅጥር ምልመላ ሂደት ላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ማለት በአዲሱ አዋጅ አንድ ቅጥርን የሚፈጽም አካል (አሠሪ) ምልመላ ሂደቱ ግልጽና ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንዲያካሂድና ከማንኛውም ዓይነት አድሎ (Discrimination) በፀዳ መልኩ እንዲያከናውን የሚያስገደድ ነው፡፡ ቅጥሩን የሚፈፅመው አካል ይህንን የቅጥር ሂደት ግልጽ ባልሆነና አድሎን በሚፈጥር መልኩ ምልመላውን ካከናወነና ሠራተኛው ላይ ቅሬታን ከፈጠረ ሠራተኛው (የወደፊት ተቀጣሪው) ቅሬታውን የሥራ ክርክር ጉዳይን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት አቤቱታውን እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲያገኝ የሚፈቅድ ድንጋጌ ነው።
2ኛ. በተመለከተ የተሻረው አዋጅና ማሻሻያ ድንጋጌዎቹ ላይ የሰፈሩት ምክንያቶች ሲሟሉ ክፍያ የሚፈፀም የነበረ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 39 (1) (መ) ስር አዲስ ሀሳብ አካቷል፡፡ ይህም ሀሳብ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ ከአሠሪው የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንዳለው የሚደነግግ ነው፡፡ በመሆኑም ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የደረሰበት ሠራተኛ በሥራ ላይ የሚደርስበትን አካላዊም ሆነ ሞራላዊ በደል ችሎ የሚሰራበት ጊዜ እንዲያበቃ የሕግ ከለላ በሀገሪቱ እንዳለ ማሳያ ድንጋጌ ነው፡፡
3.ኛው የሚመለከት ጉዳይ ነው። ይህ የሙከራ ጊዜ በተሻረው አዋጅ ከአርባ አምስት (45) ተከታታይ ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ የሚደረግ የነበረ ቢሆንም በዚህ በአዲሱ አዋጅ ግን የሙከራ ጊዜው ሠራተኛው ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከ60 (ስልሳ) የሥራ ቀናት (ከሁለት ወራት) ሊበልጥ አይችልም በማለት የሙከራ ጊዜ ቀናቱ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይህ የህጉ ድንጋጌ ለአሠሪው ሰፋ ያለ መብት የሰጠና አሠሪው ሠራተኛውን ሊመድብበት ላቀደበት የሥራ መደብ ብቁ መሆኑን በቂ ጊዜ በመስጠት እንዲመዝነው የሚረዳው ነው፡፡
4ኛው. አዲስ ዓይነት ልዩ ፍቃድ ሆኖ ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ ሲሆን ከዚህ ቀደም ያልነበረው በዚህ በአዲሱ አዋጅ የተካተተው ሠራተኛ (Married Employee) የትዳር ጓደኛ ስትወልድ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከክፍያ ጋር ፈቃድ እንዲያገኝ ሆኗል፡፡ ይህም ድንጋጌ የባል ሰራተኞችን ጥያቄ የመለሰ ነው ለማለት ይቻላል (Paternity Leave)፡፡ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ለቅድመ ወሊድ የአንድ ወር እንዲሁም ለድህረ ወሊድ የሶስት ወር በጠቅላላው የአራት ወር የወሊድ ፈቃድ ዕረፍት የማግኘት መብትን አረጋግጦላታል፡፡
5ኛው.ና የመጨረሻው ጉዳይ ነው፡፡ አሠሪው የሠራተኛውን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በአዋጅ ቁጥር 377/76 አንቀፅ 27(1) ላይ በተመለከቱት ምክንያቶች እና በህብረት ስምምነት ላይ በተገለፁት የሥራ ውል ለማቋረጥ ያስችላሉ ተብለው የተወሰኑ ጥፋቶችን ሠራተኛው ፈፅሞ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ከነዚህም ጥፋቶች ውስጥ... Comment sectio

 የዕሑፍ ማስረጃዎች በሙሉ ክርክሩን መስማትና ምስክሮችን መመርመር ከመጀመሩ በፊት ተጠቃለው መግባት አለባቸው፡፡👉 በመጀመሪያ ደረጃ ከሳሹ ከክስ ማመልከቻው ጋር ተከሳሹ ደግሞ ከመከላከያ መልሱ...
09/09/2023


የዕሑፍ ማስረጃዎች በሙሉ ክርክሩን መስማትና ምስክሮችን መመርመር ከመጀመሩ በፊት ተጠቃለው መግባት አለባቸው፡፡
👉 በመጀመሪያ ደረጃ ከሳሹ ከክስ ማመልከቻው ጋር ተከሳሹ ደግሞ ከመከላከያ መልሱ ጋር ይጠቅመናል የሚሉትንና በእጃቸው የሚገኙትን ወይም ሊያቀርቡ የሚችሉትን የጽሑፍ ማስረጃ በሙሉ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው (የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 223(1)) (ለ) እና 234 (1)፡፡
👉 በሁለተኛ ደረጃ ተከራካሪ ወገኖች ለማቅረብ የሚችሉትንና ይጠቅማናል የሚሉትን ወይም ፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ የጠየቀውንና አስቀድመው ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን የፅሑፍ ማስረጃ ሁሉ በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ማቅረብ አለባቸው (ቁ. 137 (1)
ማንኛውም አቤት ባይ ሰነዶችን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮው በፊት ወይም በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ካላቀረበ በቀር ማስረጃዬ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ጋር ይያያዝልኝ ወይም ለማቅረብ ይፈቀድልኝ በማለት ለማመልከት አይችልም (137(3)፡፡
መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች ከተከራካሪዎች ወገኖች ባንዳኛው ጉድለት ወይም በቂ ባልሆነ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ወዲያው ፍርድ ይሰጣል (ቁ. 256(1))፡፡
👉 ሶስተኛ ከላይ በ “1” እና “2” ሥር የተጠቀሱት አጠቃላይ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከአቤቱታ ጋር ወይም በመጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ የፅሁፍ ማስረጃ በሌላ ጊዜ ሊቀርብ የሚችልበት ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) አሉ፡፡ እነዚህም፡-
1. ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት ወይም በተከራካሪዎች ወገኖች አመልካችነት በሌላ ፍ/ቤት ዘንድ የሚገኝ መዝገብ ወይም የጽሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል (ቁ.148 (11))፡፡
2. ማስረጃዎቹ ሳይቀርቡ የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዳ ስለ ክርክሩ አወሳሰንና ማስረጃ ያለመቅረቡ ስላስከተለው ኪሳራ ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ በመስጠት ነገሩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል (ቁ. 256 (1)። (ማስረጃው እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል።)
3. አስፈላጊ መስሎ ከታየው ፍርድ ቤቱ የክርክሩን ጭብጥ ከመያዙ በፊት በተከራካሪዎች ያልቀረበን የፅሑፍ ማስረጃ በትዕዛዝ አስቀርቦ መመርመር ይችላል (ቁ. 149 (1) )፡፡
4. ክርክሩ በሚሰማበት በማናቸውም ግዜ ፍርድ ቤቱ በተከራካሪዎቹ ያልቀረበ ነገር ግን ለክርክሩ ጠቃሚ የሆነ የፅሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል (ቁ.164)፡፡
5. ምስክሮችን መስቀለኛ ጥያቄ ለመጠየቅ ወይም ምስክሩ ነገሩን ለማስታወስ እንዲችል የሚቀርብ የጽሑፍ ማስረጃ በመጀመሪያ በይቀርብም ክርክሩ በሚስማበት ጊዜ መቅረብ ይችላል (137 (4)) ፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Talk Laws Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category