30/06/2025
ፍርሃት
(ደሱ ፍቅርኤል)
አህያሽ ልጅ ወልዶ...
"ስም አዉጣለት" ቢሉት 'ጅቦ' ብሎ ጠራዉ
ይህን እያዬ ነዉ ነገሽን ሲገምት ልቤ የሚፈራዉ።
እናትየ ሀገሬ...
አንድ ልጅሽ እዚህ - ለሰይጣን ተልዕኮ - ያ'ምላክ ስም ይጠራል
አንድ ልጅሽ እዚያ...
"ዝምታ ወርቅ ነዉ" ብሎ ለማሳመን ያለ ልክ ያወራል
የሚወድሽ ልቤ ዛሬያቸዉን አይቶ ነገሽን ይፈራል።
Desu Fikriel