17/07/2026
b"ያልዘሩት አይበቅልም!" — የአማራ ክልል የጠቅላላ ሀኪሞች እጥረትና የጤናው ዘርፍ መጪው ፈተና
©©©
ሰሞኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮና የተለያዩ ሆስፒታሎች ጠቅላላ ሀኪሞችን (GPs) ለመቅጠር ደጋግመው ማስታወቂያ ቢያወጡም፣ የሚወዳደር ቀርቶ "ለምን?" ብሎ ጠጋ የሚል ሀኪም ማግኘት አልተቻለም። ይህ ክስተት ለብዙሃኑ አስገራሚ ሊሆን ቢችልም፣ የጤናውን ዘርፍ ህመም ቀድመው ለታዘቡና በተደጋጋሚ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ለነበሩ ባለሙያዎች ግን "ቀድሞ የተተነበየና የማይቀር የደረሰ መቅሰፍት" ነው።
"የተዘራው እንክርዳድ ሲሆን ፍሬው ስንዴ ሊሆን አይችልም" እንደሚባለው፣ ለዓመታት ችላ የተባለው የሀኪሞች ብሶት ዛሬ የጤና ተቋማቱን ባዶ አስቀርቷቸዋል።
ሀኪሞች ለምን ጥሪውን አልቀበል አሉ? — ዋና ዋና ምክንያቶች
1.የዱቲ (የትርፍ ሰዓት) ክፍያ መድረቅና ማነስ፡
አንድ የጤና ባለሙያ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥቶ፣ በከባድ ውጥረት ውስጥ አድሮ የሚከፈለው የዱቲ ክፍያ ከአንድ የጉልበት ሰራተኛ የቀን ውሎ እንኳን የሚያንስበት፣ አልፎ ተርፎም "በጀት የለም" በሚል ሰበብ ወራትን የሚዘገይበት ሁኔታ ሀኪሞችን ክፉኛ አስመርሯቸዋል።
2."ወደ ህክምና የሚገባ የለ" —፡
ሀኪም ሳይንስና እውቀቱን ተጠቅሞ ሰውን ለመርዳት የሚጥር ባለሙያ እንጂ ተአምረኛ አይደለም። መሠረታዊ የሆኑት የህክምና ግብዓቶች (ጓንት፣ መርፌ፣ ኦክስጅን፣ አልፎ ተርፎም የህመም ማስታገሻዎች) በሌሉበት ሆስፒታል ውስጥ መስራት፣ በባዶ እጅ ወደ ጦር ግንባር የመግባት ያህል ነው። ይህ ደግሞ በታካሚና በሀኪም መካከል ያለውን እምነት አጥፍቶ ለግጭት ዳርጓል።
3.የሙያዊ መብትና የደህንነት ስጋት፡
በክልሉ ባለው ወቅታዊ የሰላም እጥረት ምክንያት ባለሙያዎች በስራ ገበታቸው ላይ ያላቸው ደህንነት ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ አይደለም። ከዚህ ባለፈም የሆስፒታል አስተዳደሮች ለባለሙያው መብት መቆም ሲገባቸው፣ አላስፈላጊ ጫናዎችንና አስተዳደራዊ በደሎችን ማብዛት ምርጫቸው አድርገውታል።
4.የደመወዝና የኑሮ ውድነት አለመመጣጠን፡
የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት ጣሪያ በነካበት በዚህ ዘመን፣ የሰባት ዓመት የህክምና ትምህርትን ተፈትኖ ያለፈ ባለሙያ የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ መሰረታዊ የቤት ኪራይና የምግብ ወጪን እንኳን ለመሸፈን የማይበቃ መሆኑ፣ ሙያውን ጥለው ሌሎች አማራጮችን (ፍሪላንስ፣ የግል ድርጅቶች ወይም ስደት) እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል።
መፍትሔው ምንድን ነው? — ምን መደረግ አለበት?
ይህንን የጤና ስርዓት ውድቀት ለመታደግ “ወረቀት ላይ ካለ ማስታወቂያ” ባለፈ የሚከተሉት መሠረታዊ መፍትሔዎች በአስቸኳይ መተግበር አለባቸው፡
1.የጥቅማጥቅምና የዱቲ ክፍያዎችን በአስቸኳይ ማሻሻል፡
የጤና ባለሙያዎችን ህይወትና ክብር የሚመጥን የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ ማድረግ ግድ ይላል። የዱቲ ክፍያዎችን በጊዜው መክፈልና መጠኑንም ከወቅቱ የኑሮ ውድነት ጋር ማመጣጠን የመጀመሪያው እርምጃ መሆን አለበት።
2.የህክምና ግብዓቶችንና መሳሪያዎችን ማሟላት፡
መንግስት ለጤናው ዘርፍ የሚመድበውን በጀት በማሳደግ፣ ሆስፒታሎች መሠረታዊ የህክምና እቃዎችንና መድኃኒቶችን እንዲያሟሉ ማድረግ አለበት። ሀኪም ታካሚውን የሚረዳበት መሳሪያ ሲኖረው ብቻ ነው በራስ መተማመን ኖሮት ሊያገለግል የሚችለው።
3.የደህንነትና የሙያዊ ከባቢ አየርን ማሻሻል፡
የጤና ባለሙያዎች በነፃነትና ያለ ስጋት የሚሰሩበት አስተማማኝ የደህንነት ከባቢ መፍጠር። እንዲሁም የሆስፒታል አስተዳደር ስርዓቱ ከፖለቲካዊ ሹመት ወጥቶ ባለሙያዎችንና የስራ አካባቢን በሚያከብሩ ባለሙያዎች መመራት አለበት።
4.ተጨማሪ ማበረታቻዎችን መስጠት (Incentives)