Rahwa Tesfaye, Attorney at law

Rahwa Tesfaye, Attorney at law Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Rahwa Tesfaye, Attorney at law, Lawyer & Law Firm, Addis Ababa.

18/02/2026

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት (ቄራ) ያሉት ኮንቴይነሮች ላይ አብሮ መስራት ለሚፈልግ ጠበቃ የተሟላ ቦታ አለ። ወርሃዊ ኪራይ ብር 15000፤ ለተጨማሪ መረጃ ራህዋ ብለው የጠይቁ 0923125004

03/11/2025

ከነዋስህ ታሰር፡ ፖሊስ ራሱን ዳኛ ያደረገበት የህግ ፈተና
እስቲ ራሳችሁን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉት፤ የቅርባችሁ ሰው ታሰረባችሁ እንበል። የደረሰባችሁን ድንጋጤ እና መረበሽ ወደ ጎን አድርጋችሁ ፖሊስ ጣቢያ መረጃ ፍለጋ ባከናችሁ፣ በመጨረሻም በቅርብ ቀን ፍርድ ቤት የዋስትናውን ጉዳይ ለመስማት እንደሚቀርብ ሰምታችሁ ትንሽ ተረጋጋችሁ። በተቀጠረው ቀን ቀረበ፣ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ጠይቆ፣ ዘመድ ወዳጃችሁ ቢለቀቅ ከህግ የሚሸሽ አደገኛ ወንበዴ እንደሆነ በማስረገጥ እንዲቆይ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ሳይቀበለው በመቅረቱ የዋስትናመብቱ እንደተከበረ ብስራቱ ደረሳችሁ። የዋስትናውን ግንዘብ ከፍላቸሁ ፖሊስ ጋር ስትቀርቡ ግን ጉዳዩን ይግባኝ ለማለት በመወሰኑ ትንሽ ተጨማሪ ቀናት እዛው እንደሚቆይ ተነግሯችሁ በውጥረት ጫካ ውስጥ ቆያችሁ። ይግባኝ ችሎቱ ግን የታችኛውን ችሎት ውሳኔ አክብሮ አጸናው፤ ከውጭ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል የእናንተው ሰው ተፈቀደለት። ደስታችሁ እና እፎይታችሁ ፊታችሁን እያበራው በትጋት ተገቢዎቹን ሰነዶች ሰብስባችሁ ለማስመራት መርማሪ ፊት ቀረባችሁ። በጸባይ ለመለያየት በማሰብ ፖሊሶች ስራቸውን እየሰሩ እንደሆነ እንደምታውቁ ለመንገር ወስናችሁ ነበረ። መርማሪ ፖሊስ ወረቀቶቹን ተቀበለ። ግን አልፈረመባቸውም። መሳቢያውን ጎተት አድርጎ ሰነዶቹን ውስጡ ከጨመረ በኋላ አቶ ምስለኔ በሌላ ወንጀል ሌላ ፖሊስ ጣቢያ የሚፈለግ ሰው መሆኑን፣ የፖሊስ አባላትም ሊወስዱት እየመጡ በመሆኑ የዋስትና ሰነዱን መርቶ እንደማይለቅላችሁ አረዳችሁ። ምስኪኑ ታሳሪያችሁ ሳይወጣ፣ ለዋስ ተያዥ ያደረጋችሁትገንዘብ ተይዞ፣ ለመክፈላችሁ ማረጋገጫ የሆነውም ደረሰኝ ከእጃችሁ ተወስዶ ከሁለት ቤት አንዱም ሳትሆኑ አየር ጨብጣችሁ ቀራችሁ። ምን ታደርጋላችሁ?
ለማመን ቢከብድም ከላይ የተጠቀሰው ታሪክ በሀገራችን የፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ እስረኞች ላይ በተደጋጋሚ የደረሰ፣ እየደረሰም
ያለ አሳዛኝ እውነታ ነው። በተለያዩ ምክንያቶች በእጃቸው የገባን ተጠርጣሪ ለመልቀቅ የከበዳቸው የፖሊስ አባላት እንዲያስፈጽሙት ህጋዊ ሃላፊነት ያለባቸውን የፍርድ ቤት የመልቀቅ ትዕዛዝ ‘አሻፈረኝ ሳይሉ እሺ ላለማለት’ በእነርሱ አባባል የሚጠቀሙባት የህግ ክፍተት ነች። ፖሊስ ይህንን አሠራር በመጠቀም የወንጀል መቅጫ ስነስርዓት ህጉንም ሆነ እርሱን የማስተርጎም ስልጣን የተሰጣቸውን ፍርድ ቤቶችን ያስቀመጡበትን ህጋዊ ወሰን እንደሚከተለው ሸውዶ በማለፍ እስረኞችን እስከሚመቸው ጊዜ ድረስ በማቆየት ላይ ይገኛል።
ግን የዚህ ዘዴ ህጋዊነት እስከምን ነው? የሚለው ጥያቄ አግባብነት የሚያከራክር አይመስለኝም። የተያዙ ወይም የታሰሩ ግለሰቦች መብቶች በመርህ ደረጃ በህገመንግስቱ የሚዳሰስ ሲሆን፣ በሀገሪቱም ህጎች ከእነዚህ መርሆች የተቀዱ የተለያዩ ህጋዊ እና ሥርዓታዊ መፍትሄዎች የተሰናዱለት ጥልቅ እና አባይ ጉዳይ ነው። የሀገሪቱ የበላይ ህግ በአንቀጽ 17 ላይ ማንም ግለሰብ በህግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ነጻነቱን ማጣት እንደሌለበት ግልጽ የሆነ ትዕዛዝ ያስቀመጠ ሲሆን በተለየ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ጉዳያቸውን ለሚያይ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው፣ የአካል ነጻነታቸው ሁኔታ በዚሁ ፍርድ ቤትም እንደሚወሰን እና ተጠርጣሪዎችም አካላዊ ነጻነታቸውን ለማስከበር አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በመግለጽ በማብራሪያ አጠናክሮታል። (የኢፈደሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 19(3) እና (4))።
የወንጀል መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ አቋምም ከላይ የተመላከተውን ተዋረድ የሚከተል ሲሆን በተጠርጣሪነት ነጻነታቸውን ያጡ ዜጎችን በተመለከተ የሚያስቀምጠው የምርመራ እና አፈጻጸም ስርዓት ህጉ በወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ያለውን አቋም ግልጽ የሚያደርግ ይመስላል። የወንጀል ተጠርጣሪ የወንጀል ፈጻሚ ተቀጪ ባለመሆኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለ ጊዜ በዋስ የመለቀቅ መብቱን ለማስከበር ለሁለት አካላት አቤት ማለት ይችላል። እነዚህም ፍርድ ቤት እና ጉዳዩን የመከታተል ሃላፊነት የተሰጠው መርማሪ ፖሊስ ናቸው። ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ቢለቀቅ ከፖሊስ የማያመልጥ፣ በተፈለገበት ጊዜ እና ሰዓትም ቀርቦ ትብብር የሚያድረግ መሆኑን ግልጽ ካደረገ መርማሪ ፖሊስ ዋስትና አስይዞ እንዲለቀቅ ፈቃድ መስጠት ይችላል። (የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 28)። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ደግሞ የተያዘን ተጠርጣሪ ጉዳይን የሚሰማው የጊዜ ቀጠሮ ችሎትን የዋስትና መብቱን አክብሮ እንዲለቀው መጠየቅ ይችላል። በዋስ የመለቀቅ መብት በተፈጥሯቸው አስከፈ እና ከባድ ያልሆኑ፣ ረዥም የእስር ጊዜ የማያስከትሉ ወይም ተበዳዩን ለሞት ያላደረሱ ወንጀሎች የተጠበቀ በመሆኑ በጊዜው ጉዳዩን የሚሰማው ችሎት ተጠርጣሪው በዋስ ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል የማይፈጽም መሆኑን፤ ማስረጃ እና ምስክሮችን በማሸሽ ወይም በማባበል ህጋዊ እንቅፋት የማይፈጥር መሆኑን ከተረዳው መቅረቡን የሚያስተማምን የሚመስለውን የዋስትና መጠን እንዲያስይዝ አድርጎ ሊለቀው ይችላል (የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 64)። የዋስትና መብቱ ተከብሮለት የቆየ ሰው በራሱ አቅም ቢያንሰው ራሱ ተገቢ የሆነ ዋስ እንዲፈለግለት ህጉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል (የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 62)። ችሎቱ በዋስ መለቀቅ አይገባውም ብሎ ቢወስን ተያዡ ግለሰብ ሌሎች አማራጮች አሉት፤ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ይግባኝ ማለት ይችላል፣ ይህ ካልሆነለትም በወንጀል ክስ ሂደቱ በሚያልፍበት በማናቸውም ወቅት የዋስትና አቤቱታ አስገብቶ ጉዳዩን በድጋሜ ማስመርመር ይችላል (የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 63፣ 75 እና 181ን ይመልከቷል)። የዋስትና መብቱ ተከብሮለት እንዲወጣ ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈለትን ተያዥ ዋስትና አስይዞ የዋስትና ወረቀቱን ባቀረበ ጊዜ እስረኛው ወዲያውኑ መልቀቅ አለበት (የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 72)
በዚህ ጊዜ ከላይ ከተዘረዘሩት ህጎች ጥምረታዊ ንባብ ነጥረው የሚወጡ መሰረታዊ የህግ ነጥቦች ላይ አንክሮ ማድረግ ይገባል። በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው ሲያዝም ሆነ ጉዳዩ ሲመረመር በህግ የተቀመጠው መብቱ እና ግዴታው ብቻ ተፈጻሚ ሊደረግበት እንደሚገባ፤ ነጻ የመውጣት ወይም በጥበቃ ለመቆየት እንደሚገባው የመወሰን ስልጣን በህጉ የተሰጠው ለተወሰኑ አካላት ብቻ መሆኑን፤ የዜጎችን የነጻነት መብት ለማስከበር በፍትህ ስርዓቱ አተረጎጎም እና አፈጻጸም ላይም ቢሆን ስርዓታዊ ተመጣጥኖ (checks and balances) እንዲኖረው በስርዓቱ ውስጥ ያሉ አካላት ህጋዊ ሃላፊነቶቻቸውን ብቻ መወጣታቸው መሰረታዊ መሆኑን፤ በመጨረሻም ፖሊስ እስረኛን ያዥ በሆነበት ሁኔታ ከላይ ስለዋስትና ወረቀት የተቀመጠው መስፈርት ተሟልቶ በቀረበለት ጊዜ ወዲያውኑ እስረኛውን መልቀቅ አንዳለበት ነው። እዚህ ጋር ምናልባት የፖሊስ ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማሰር መብት ጥያቄ ሆኖ የሚነሳ ከሆነ ለመዳሰስ ያህል እንወያይበት። ፖሊስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 51 ስር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በተሟሉ ጊዜ ብቻ ነው አንድን ተጠርጣሪ ያለ ትዕዛዝ ማሰር የሚችለው። ዝርዝሩን አንባቢ እንዲመረምረው እያሳሰብኩኝ ፖሊስ ይህ ለየት ባሉ ሁኔታዎችን ተጠርጣሪን እንዲይዝ የሚያስችለውን መብት የሚያገኘው አንድ ግለሰብ የፖሊስን ተግባር ለማደናቀፍ ሙከራዎችን ካደረገ፤ አደገኛ ስራ ፈት የሆነውን ወይም የህዝብን ጸጥታ የሚበጠብጠውን፣ ቤት ለመበርበር ወይም አደገኛ ስራ ለመስራት ተገጋጅቶ የተገኘውን ወይም እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲሰራ የተያዘውን ሰው ስለሆነ በፖሊስ ጥበቃ ውስጥ የቆየን ግለሰብ አያካትትም። አሁን ከፖሊስ ጥበቃ ሊለቀቅ የተዘጋጀን ዋስትና አቅራቢ ደግሞ ወደ ሌላ ጣቢያ እንዲሄድ እና በሌላ ወንጀል ተጠርጣሪነት እንዲታሰር እውነታውን እያወቀ በመደበኛው ትዕዛዝ የሚሰጥ ፍርድ ቤት እንደማይኖር ግልጽ ነው።
ይህ በመሆኑ በቁጥር ለማይታወቁ እስረኞች መጉላላት እና ታግቶ መቆየት በየጣቢያው የፖሊስ አባላት እየተጫወቱት ያለው ሚና ሀላፊነት ያስረከባቸው ህግ ካስቀመጠው መስመር የወጣ፤ የህግ ስርዓቱን እና ተሳታፊ አካላትን ስልጣን የሚያዋርድ እና በተግባር የሚስት ልምዳዊ እንጂ ኢ-መደባዊ አሰራር እንደሆነ በድፍረት መናገር ይቻላል። በዚህ ሁኔታ ማብቂያ ለሌለው እስር የተዳረጉትን ወገኖቻቸውን ነጻነታቸውን ለማግኘት ቤተሰብ ወዳጆች ፍትህ ሰጪነት የስራቸው አካል የሆኑትን ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ አካላትን በመተው ራሳቸውን ህጉን ወደአጣመሙት የፖሊስ አባላት እንዲዞሩ ይህ የአደባባይ ሚስጢር የሆነው ሲስተም አስገድዷቸዋል። በዋስ የተለቀቀ እስረኛን ‘አንለቅም፣ ምን ታመጣላችሁ’ የሚሉ፤ ይህንን አሰራር እንደማስፈራሪያ አድርገው ባለጉዳዮች የትም ቢሄዱ ከፖሊስ እጅ እንደማያመልጡ በመግለጽ ቅስም ለመስበር እና የግለሰቦችን ጭንቅ በመጠቀም ለሙስና እና ብልሹ አሰራር እጃቸውን ለማሰጠት የሚጠመዝዙ አባላትም እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል። ከእንደዚህ እይነት አጣብቂኝ ለማምለጥ የመጨረሻ ቀዳዳን ለመጠቀም ለፖሊስ ኮሚሽን የሚገቡ አቤቱታዎችም ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም። ከምንም ነገር በላይ ግን በፍትህ ስርዓቱ ነጻ ተብለው በእውነታ ታግተው የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ እጅጉኑ አሳዛኝ ነው።
ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለማበጀት ከሁሉም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አባላት ማበርከት የሚችሉት ሚና አለ። ከማንም በፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፖሊሰ አባላት ለህግ የበላይነት እና ለህሊናቸው ሃላፊነት ቅድሚያ ሰጥተው ይህ ስራ ህገወጥ መሆኑን በመረዳት ተሳትፎን ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል። ዳኞች እና የፍትህ አካላት የጊዜ ቀጠሮ ውሳኔያቸው በዚህ መልኩ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ተረድተው የዋስትና ውሳኔያቸው ትዕዛዝ መተግበሩን መከታተል፣ ቅሬታዎችን በቀረቡላቸው ጊዜ ይህንኑ በፍጥነት መመርመር ይገባቸዋል። የእስር ትዕዛዝ የሚሰጡ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ከመጻፋቸው በፊት የተጠርጣሪዎችን መገኛ ትክክለኛ መረጃ ለማጣራት ጥረት ቢያደርጉ ትልቅ አስተዋእጾ ይኖረዋል። የተያዙ ግለሰቦች ህጋዊ ወኪሎችም ቢሆኑ ማድረግ የሚችሉት ነገር አለ። የዋስትና ወረቀት ሲያወጡ ለማስረጃ እንዲሆናቸው የደረሰኙም ሆነ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ግልባጭ መያዝ፤አጠራጣሪ ሃሳብ ይዘው ለሚቀርቧቸው ግለሰቦች እነዚህሰዎች ፖሊሶችም ቢሆኑም ጊዜ እና ቦታ አለመስጠትን ይጨምራል። ከላይ የተጠቀሰው አሰራር ህገወጥ በመሆኑ ለጉዳዩአግባብነት ያለውን መፍትሄ ለመስጠት ሊረዷቸው የሚገቡ የህግ አማካሪዎችን መያዝም መላ ያለው ነው። ግን ስለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥሁሉም ሰው በዚህ ጉዳይ በመወያየት አደባባይ ቢያወጣው ነገሩን ለመቋጨት ሩቅ የመጓዝ ብቃቱ ቀላል አይደለም።

02/09/2025

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ ቁጥር 25/2017 ጸድቋል
*********************************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ በማውጣት ከቀጣይ መስከረም 23 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ስራ ላይ ማዋል ይጀምራል ተብሏል።

Via Ale Hig and MikiasMelakአጭር ሥነሥርዓት🟰🟰 (summary Procedures)🟰ከፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ላይ አቤቱታ ለማቅረብ የምንጠቀምባቸው ሶስት መንገዶች አሉ፡፡...
19/12/2024

Via Ale Hig and MikiasMelak
አጭር ሥነሥርዓት
🟰🟰 (summary Procedures)🟰
ከፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ላይ አቤቱታ ለማቅረብ የምንጠቀምባቸው ሶስት መንገዶች አሉ፡፡

እነዚህም🟰 👇👇👇
✅1ኛ/ በደበኛ ሥነ-ሥርዓት
✅2ኛ/ አጭር ሥነ-ሥርዓት
✅3ኛ/ የተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት ሲሆኑ

ከእነዚህ ውስጥ🟰👇👇👇
✅2ኛውን የክስ አቀራረብ እንመለከታለን፡፡

1. ከፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ/ 284 እስከ 292 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡
2. በዚህ ሥርዓት መሠረት ክስ ሊቀርብ የሚችለው በቁ. 284 ሥር በተዘረዘሩ ጉዳዮች ብቻ ነው፡፡ ምንጩ ግልፅ ውል፣ የሃዋላ ሰነድ፣ ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ ወይም ቀላል ውል የሆነ ልኩ የታወቀ ገንዘብን የሚመለከት ክስ በሆነ ጊዜ ነው።
3. ማመልከቻው በመኃላ ቃል ተደግፎ መቅረብ አለበት (284(ለ))፡፡ የመኃላ ቃለ ተከሳሹ ለነገሩ ምንም ዓይነት መከላከያ እንደሌለው ከሳሽ የሚያምን መሆኑን መግለፅ አለበት
4. ፍ/ቤቱ ማመልከቻውን ከተቀበለ በኃላ ለተከሳሹ መጥሪያ እንድደርሰው ያዛል (ቁ. 285(1))
5. ተከሳሹ ቀርቦ ለመከላከል እንድፈቀድለት ፍ/ቤቱን ጠይቆ ካላስፈቀደ በቀር መከላከያ ሊያቀርብ አይችልም (ቁ. 285(1))፡፡
6. ተከሳሹ ቀርቦ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ለፍ/ቤቱ ካላመለከተ ወዲያው ፍርድ ይሰጣል(ቁ. 285(2))፡፡
7. ለመከላከል ፈቃድ እንዲሰጥ የሚቀርበው ማመልከቻ በቁ. 286 መሠረት በመኃላ ቃል ተደግፎ መቅረብ አለበት፡፡
8. ተከሳሹ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ካጣ ወዲያው ለከሳሹ ይፈረዳል (ቁ. 287)፡፡
9. ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ ግን ተከሳሹ መከላከያ እንድያቀርብ ይፈቀድለታል፡፡ ክርክሩም የሚመራው ፍ/ቤቱ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ወይም እንደመደበኛው ክስ በቀጥታ ሊሆን ይችላል(ቁ. 290 እና 291)፡፡
10. ፍርድ ከተሰጠ በኃላ ለተከሳሹ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው ከሆነ ፍ/ቤቱ ፍርድ ከመፈፀም እንዲቆይ በማድረግ ተከሳሹ ቀርቦ እንዲከላከልና ስለ ጉዳዩም አፈፃፀም ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ ለመስጠት ይችላል(ቁ.292)፡፡
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ https://t.me/AleHig
የሕግ እውቀት alehig.com

AleHig attorney & Legal consult present across multiple social media platforms..

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣን ደንብ በተመለከተ ከፌደራል ጠበቆች ማህበር የተላለፈ መረጃ ፤=============የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወ...
05/12/2024

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣን ደንብ በተመለከተ ከፌደራል ጠበቆች ማህበር የተላለፈ መረጃ ፤

=============

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣን ደንብ በተመለከተ ደንቡ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት የኢት/ፌደ/ጠበቆች ማህበር ዝርዝር ትችቱ አባላቱን በመመደብ እንዲሁም በአመራር ደረጃ ክለሳ ሊደረግባቸው ይገባል ባላቸው የረቂቁ ይዘቶች ላይ ተቃውሞና አስተያየቱን ጭምር ማቅረቡ የሚታወስ ነው::

ይህም ከዳኝነት አከፋፈል ሰንጠረዡ በተጨማሪ ለአቤቱታ ፣ ለእግድ ፣ ለምስክሮች መጥሪያ እና መሰል የተጋነኑ የክፍያ አይነቶችን ላይ ጠንካራ ትችቶችን ያካተተ የነበረ ነው:: ከዚያ በኃላ ማህበሩ በመጨረሻው የደንቡ ቅጂ ይዘት ላይ ደርሶት ሃሳቡን ያቀረበበት እድል አልነበረም::

አሁንም ረቂቅ ደንቡ መፅደቁ እንደተሰማ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፀደቀው ትክክለኛ ቅጂ Authentic version እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ የመጨረሻ እርማት እና ህትመት ላይ መሆኑ ተገልፆለት እየተጠባበቀ ሲሆን ፤ በአማራጭ ማህበሩ ባገኛቸው ሰነዶች ላይ የተሟላ ምልከታ አድርጎ በተለመደው አሰራሩ እና በሌሎች ጉዳዮች እንደሚያደርገው ይፋዊ አቋሙን የሚገልፅ መሆኑን እናስታውቃለን::

በሌላ በኩል ግን ማናቸውም የማህበሩ አባል ጠበቃ በዚህ ሂደት ላይ ለመሳተፍና የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የሚፈልግ/ የሚችል ሁሉ በማህበሩ ስልክ ቁጥሮች በመደወል በመመዝገብ መሳተፍ የሚችል መሆኑን እናስታውቃለን::

መረጃውን በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::

የሊንክደን ገፃችን LinkedInn Page - https://www.linkedin.com/company/ethiopian-federal-advocates-association/

ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO

የቴሌግራም ገፅ- https://t.me/ethiopianfederalbarassociation

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ህዳር 24 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤

Ethiopian Federal Advocates Association | 991 followers on LinkedIn. Empowering 7,000+ lawyers in Ethiopia, EFAA supports legal professionals and connects with Africa’s legal community. | The Ethiopian Federal Advocates Association (EFAA) is a statutory organization dedicated to promoting the inte...

02/12/2024

Via አለ ህግ
No Fayda no service‼️
ከጥር 2017 አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ግዴታ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያስፈልጋል‼️

-ከሰኔ ወር 2017 መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትልልቅ ከተሞች ባሉ ባንኮች አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ግዴታ ነው

-በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያን ግዴታ ያደርጋሉ

-በታሕሳስ 2019 ዓ.ም ነባር የባንክ ደንበኞችም ቢሆኑ ፋይዳ ካልያዙ አገልግሎት አያገኙም።
#ዋዜማ

21/11/2024

የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
***

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

Courtesy; Daniel Fikadu law office

14/09/2024

የታዋቂዉ ደራሲ ሃዲስ አለማየሁ ወራሽ የሆኑ ሰዉ ፍቅር እስከ መቃብርን ወደ ፊልም ቀይሮ ለህዝብ የማሰራጨት እንቅስቃሴ እንዲቆም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ዋልታ ቴሌቭን ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ፍቅር እስከ መቃብርን በተመለከተ ለአንድ ዓመት የዘለቀ ክርክር እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑ ታዉቋል። በክርክሩም ሂደት ለክሱ ምክንያት የሆነዉን ፍቅር እስከ መቃብርን ወደ ፊልም ስራ ቀይሮ ለህዝብ የማሰራጨት ስራዉን እንዲያቆሙ የሚያስገድድ የእግድ ትዕዛዝ ተላልፎ ኢቢሲ ፊልሙን የመስራትም ሆነ ወደ ህዝብ የማሰራጨት ስራዉን አቁሞ ክርክሩ ቀጥሎ ነበር።
ይሁን እንጂ ጉዳዩን ለማየት የሚያስችል የዳኝነት ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነዉ ወይስ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነዉ? በሚለዉ ጭብጥ ላይ ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተለያየ አቋም በመያዛቸዉና በዚህ ነጥብ ላይ ኢቢሲ እና ዋልታ ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መነሻነት ጉዳዩ እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደርሷል። በአሁኑ ስዓት የደራሲዉ የሃዲስ ዓለማየሁ ወራሽ እና ተከሳሾች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክርክር ላይ ናቸው ።
ይህ በእንዲህ እያለ እቲቪ ያለምንም ቅድመ ማስታወቂያ በድንገት ከበአል ዋዜማ ጀምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን የፍቅር እስከ መቃብር ፊልም በዩቲዩብ እና በቴሌቭዥን እያሰራጨ ይገኛል። ባልተለመደ እና ብዙሃኑን ባስገረመ መልኩ የፊልም ስራዉን በየቀኑ በማሰራጨትን ተያይዞታል።
የደራሲው ወራሽ ይሄንን እንዳወቁ በበዓሉ ማግስት መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም ኢቢሲ ጉዳዩ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን እያወቀ ክርክሩ እንደማያዋጣዉ ሲያዉቅ ክርክሩን ከወዲሁ ዋጋ አልባ ለማድረግ በማሰብ የበዓላት ቀናትን ተገን በማድረግ የፍቅር እስከ መቃብርን ፊልም ለህዝብ በማሰራጨት እየፈፀመ ያለዉን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያቆም ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸዉ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም በአቤቱታዉ ላይ ኢቢሲ እና ዋልታ አስተያየታቸዉን እንዲሰጡበት ትእዛዝ ሰጥቶ መዝገቡን ለመስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም( ለሚቀጥለዉ ማክሰኞ) ቀጠሮ ይዟል። zewedu

06/08/2024

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ፦

➡️ አዲስ ፓስፖርት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

➡️ የፓስፖርት እድሳት ፦

1ኛ. እድሳት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

2ኛ. የፓስፖርት ገጽ ያለቀባቸው ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

3ኛ. እድሳት የሚፈልጉ እና እርማት የሚያስፈልጋቸው ፦ መደበኛ 12 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 32 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 27 ሺህ 500 ብር

4ኛ. ፓስፖርት ቀን ያለው እና ፓስፖርታቸው የተበላሸ ፦ መደበኛ 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

5ኛ. ፓስፖርቱ ቀን ያለው ፤ ፓስፖርታቸው የተበላሸ እርማት የሚፈልጉ ፦ መደበኛ 20 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

➡️ የጠፋ ፓስፖርት ፦

1ኛ. የጠፋ ፓስፖርት ፦ መደበኛው 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

2ኛ. የጠፋ ፓስፖርት እርማት ፦ መደበኛ 20 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

05/07/2024

#ተራዘሟል

በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ።

ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል።

አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል።

ነገር ግን ፦
- በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ
- ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች ስለሚሆን
- ቀኑ እንዲራዘምም ከህብረተሰብ በቀረበ ጥያቄ የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም መራዘሙን ቢሮው ገልጿል።

ነዋሪዎች ጊዜው ተራዘመ ብለው ሳይዘናጉ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ሳይጨናነቁ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251923125004

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rahwa Tesfaye, Attorney at law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Rahwa Tesfaye, Attorney at law:

Share