01/10/2022
የጠበቃ ቀልዶች
ሰጥቶ መቀበል
ጠበቃ፤ ሐኪምና የባንክ ሰራተኛ በሞት የተለያቸውን ወዳጃቸውን ሊቀብሩ ከአስከሬኑ አጠገብ ቆመዋል፡፡ በሀዘናቸው መሐል የባንክ ሰራተኛው “በኛ ባህል መሠረት ሟች ለሰማይ ቤት የሚሆነው ትንሽ ገንዘብ መስጠት ልማዳችን ነው፡፡ ስለዚህም ለምን የተቻለንን አንረዳውም?” ሲል ሓሳብ ያቀርባል፡፡ በሓሳቡ ሁሉም በደስታ ተስማምተው መጀመሪያ የባንክ ሰራተኛው ከኪሱ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ የሬሳ ሳጥኑ ስር ሸጎጥ አደረገ፡፡ ሐኪሙም እንደዚሁ ድፍን መቶ ብር ለገሰ፡፡ በመጨረሻም ጠበቃው ሁለቱም የሰጡትን 200 ብር ሰብስቦ ኪሱ ከከተተ በኋላ የሶስት መቶ ብር ቼክ ጽፎ ሳጥኑ ስር በመክተት ‘የቻለውን ያህል’ ረድቷል